The Ethiopian Federal Government is Primarily Responsible for Agaw Kemant Genocide and Current Unrest in Metema, Quara and Negade Bahir following Disrupted Referendum (ተሞክሮ የከሸፈውን ሪፈረንደም ተከትሎ ) on September 15, 2017

የቅማንት-አገው ህዝብ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ያለአግባብ ለመዘግዬቱ ዋናው ተጠያቂ ማነው?

ከጠላታችን ድቁርና

—————————————-////——————————————
የቅማንት-አገው ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ያለአግባብ ለመዘግዬቱ “ዋናው” ተጠያቂ የአማራ ክልል መንግስት አይደለም። የአማራ ክልል መንግስት ተጠያቂ አይደለም እያልኩ አይደለም። በዋናነት ተጠያቂነቱን የሚወስደው የፌዴራል መንግስቱ ነው። እንዴት ባለ መልኩ ተብዬ ብጠየቅ ምክንያቶቼ የሚከተሉት ናቸው፤
1) የአማራ ክልል መንግስት የቅማንት-አገው ህዝብ ያነሳውን የማንነትና ራስ አስተዳደር ጥያቄ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመመለስ ፍጹም ፍላጎቱና ዝግጁነቱ እንደሌለው የፌዴራል መንግስቱ ግጥም አድርጎ ያውቅ ነበር። በምን መንገድ ከተባለ ደግሞ ግልጽ ነው። ባለው መንግስታዊ መዋቅሩ በኩል (ስራ አስፈጻሚው፣ የደህንነት መረቡ፣የቅማንት ተወካዮች በሚያቀርቡት ቅሬታ፣ ጥያቄው ለክልሉ መንግስት ከቀረበ አዋጅ ቁጥር 251/1993 ከሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ ማለትም ከሁለት አመት በላይ አልፎት ነበር፣ ለክልሉ መንግስት የቀረበው የመብት ይገባኛል አቤቱታ በተመሳሳይ በግልባጭ የፌዴራል መንግስቱ እንዲያውቀው ተደርጎ ነበር፣ ወዘተ)፤
2) የህገ-መንግስቱ ማስፈጸሚያ አዋጅ ቁጥር 251/1993 በሚደነግገው መሰረት የክልሉ መንግስት በሚሰጠው ዉሳኔ ቅሬታ ሲኖር ይግባኝ ለፌዴራሉ መንግስት ማቅረብ የሚቻል ሲሆን የቅማንት ህዝብ ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ህጉን ተከትሎ የይግባኝ ቅሬታ አቤቱታውን አቅርቧል። ይህ በሆነበት ወቅት የፌዴራል መንግስት በቀረበለት የይግባኝ አቤቱታ መሰረት ጉዳዩን አይቶ ውሳኔ ማስተላለፍና ማስፈጸም ሲገባው የክልሉ መንግስት እንደገና እድል ይሰጠኝና በቀረበው ጉዳይ ላይ ድጋሜ የተሳሳተ ውሳኔ ልስጥበት ወይም ጉዳዩን እያዘገየሁ ጊዜ ልግዛበት ብሎ ጥያቄ ሲያቀርብ ስለህዝቦች መብት፣ስለህግ የበላይነት፣ስለዴሞክራሲያዊና ፌዴራላዊ ስርአትና ሰላም ሲባል ፈቃደኛ ሁኖ አስተላልፎ መስጠት አልነበረበትም።
3) አሁንም የክልሉ መንግስት ከእጁ ወጥቶ በድጋሜ ያገኘውን እድል ተጠቅሞ የቅማንትን ህዝብ ጥያቄ አበላሽቶ በ42 ቀበሌ አስተዳደር የህዝቡን እጣ-ፈንታ ሲወስን ተወካዮች የተለመደውን ህጋዊ ስርአት ተከትለው ለፌዴራሉ መንግስት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ነበር። የፌዴራሉ መንግስትም በቀረበው ይግባኝ ቅሬታ ላይ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ህጉ በሚለው አግባብ ሙሉ ሓላፊነቱን አልተወጣም ነበር። የክልሉ መንግስት በጀመረው አግባብ ከቅማንት ህዝብ ተወካዮች ጋር በመግባባት ጉዳዩን ይፍቱት ብሎ ከደሙ ንጹህ ነኝ በሚያስብል መልኩ አፈጻጸሙን አስተላልፎ መስጠቱ ትልቅ ስህተት ነበር።
4) ከዚህ በላይ በተገለጸው የተሳሳተ ውሳኔና አካሄድ ሳቢያ የክልሉ መንግስት እንደተጠበቀው የቀረበውን ህዝባዊ ጥያቄ በህጋዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም አዳፍኖ ማስቀረት ካልሆነ ደግሞ በ42 ቀበሌ አስተዳደር ማዋቀር ላይ ብቻ ቆርቦ ቁጭ አለ። ይባስ ብሎ የቅማንት ህዝብ ተወካይ የሆነውን ኮሚቴ ድራሹን ማጥፋት አለብኝ በሚል ጦርነት ከህዝብ ጋር ገጥሞት እርፍ አለ። ብዙ ኪሳራ ደረሰ። የፌዴራል መንግስቱም ጉዳዩን የማያውቅ መስሎና የተቃዋሚዎች መግቢያ እድል እንዳይፈጠር ለመከላከል በሚል አላማ ገላጋይና ሸምጋይ መስሎ ገባ። እነዚህ ሁሉ በስህተት ላይ ስህተት እየተደራረቡና እየተጨማለቁ የመጡና ወደል-ግብዳ ስህተትን እየወለዱ ቀጠሉ።
5) የክልሉ መንግስትም መንግስትነቱን ረስቶት ወይም እመራዋለሁ ከሚለው ህዝብ ጋር ጦርነት ገጥሞ በደረሰበት ከፍተኛ ሽንፈትና ኪሳራ ሳቢያ ግራ ተጋብቶና ተደነጋግሮ “መንግስት” የሚለውን ቃል ትርጉም ረስቶት እንደወንበዴ አደረገውና ቅማንትን ከመሬት ላይ ጠራርጎ ገሎ ለመጨረስ የዘር ማጥፋት የክተት አዋጅ ባደባባይ አሳውጆ አረፈው። የፌዴራል መንግስቱም ፍጹም የማይመለከተው መስሎ ታዛቢ ሁኖ ሱዳንና ኬንያ ደንበር ላይ ሁኖ ጉዳዩን ይከታተል ነበር። የአገር መከላከያ ሰራዊት እንኳ የዘር ፍጅቱን ጣልቃ ገብቶ እንዲያስቆም ሲጠየቅ “ከበላይ አካል ትእዛዝ” አልተሰጠኝም እያለ ምላሽ ይሰጥ ነበር። ወይ ነዶ! ገና ስንት የተበላሸ የሚጻፍ ታሪክ አለ መሰላችሁ። በዘር ፍጅት ጦርነቱ ሳቢያ እጅግ ብዙ ኪሳራ ደረሰ።
6) የዘር ፍጅቱን ተከትሎ ለደረሰው ኪሳራና ተጎጅዎች የክልሉም ሆነ የፌዴራሉ መንግስት ምንም አይነት እርዳታ አላቀረቡም። ቀይ መስቀል የተባለ አለማቀፍ ድርጅት ትንሽ ከሞከረው እርዳታ ውጭ መንግስት መንግስትነቱን ትቶ ሸፍቶ ድምጽ-አልባ “እምቢ” አሸክሞን ቀረ።
7) መንግሥታዊ የፌዴራል መንግስት ተቋም የሆነው “የሰብአዊ መብት ኮሚሽን” በቅማንት ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍና ኪሳራ አስመልክቶ የጥናት ሪፖርት አለኝ ብሎ ቀርቦ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ አደረገ። ተጠያቂ የሚሆኑ የአማራ ክልል መንግስት ባለስልጣናትን ሁሉ ሳይቀር ለይቶና ፈርጆ ቀርቦ ነበር። ቅሉ ግን ምንም አይነት ህጋዊ እርምጃ ሳይወሰድ የዉሃ ሽታ ሁኖ ቀረ።
8) በዘር ፍጅት ደም እጃቸው የተጨማለቀው የክልሉ ባለስልጣኖችም እርምጃ ባለመወሰዱ ምክንያት የጀመሩትን ተንኮል አጠናክረው ቀጠሉ። የቅማንት-አገው ህዝብ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄን የበለጠ የሚያዳፍኑበትን ስልት ውስጥ ለውስጥ ነድፈው መንቀሳቀሳቸውን ቀጠሉበት። ለዘመናት ተዳፍኖ የኖረውን “የወልቃይት” ጉዳይ መዘው አመጡና ከውስጥ እስከአገር ውጭ እንዲጦዝ አደረጉ። “አማራና ቅማንት አንድ ነው! ወልቃይት የአማራ ነው! የቅማንትን ጉዳይ የሚያነሱ የወያኔ ተላላኪዎች ስለሆኑ እርምጃ እንወስድባቸዋለን! ወዘተ” የመሳሰሉትን መፈክሮች በአደባባይ አስነበቡ። ቀጥሎም ህዝባዊ ማእበል ተቀጣጠለና ከባድ ኪሳራ ደረሰ። ለሁለተኛ ጊዜ በቅማንቶች አገር-ጎንደር የዘር ፍጅት ተፈጸመ። በታሪክ ታይተው የማይታወቁ ሰውን ማቃጠል ጨምሮ ዘግናኝ ዘግናኝ ወንጀሎች ተፈጸሙ። ሱዳንና ኬንያ ደንበር ላይ ቁሞ ይታዘብ የነበረው የፌዴራል መንግስትም መከላከያ በሚባለው መሳሪያው ግባና “እጨድ” የሚል ትእዛዝ አስተላለፈ። በርካታ የጎንደር ወጣቶች ተቀጠፉ። ወይ ነዶ! ገና ስንት የተበላሸ የሚጻፍ ታሪክ አለ!
9) ሁሉም ነገር የሆነው ሆነና የፌዴራሉም መንግስት አስቸኳይ አዋጅ በማወጅ ለአንድ አመት ገደማ አንድ የረባ የህዝብ ጥያቄ ሳይመልስ ሲደናበር ቆዬ። የቅማንት ህዝብ ጥያቄም አንዱ ነበር። ጊዜን ጊዜ እየወለደው ኪሳራዎችና ህዝባዊ በደሎች እየተከማቹ አንድ ቀን ልክ እንደአዲስ አበባው “ቆሼ” ተደርምሰው አገር እስከሚያጠፉ ድረስ “መከመራቸውን” ቀጥለዋል።
10) እንደው ሌላውን ሁሉ ነገር እንተወውና የሰሞኑን (መስከረም 7/2010) ተሞክሮ በከሸፈው “ህዝባዊ ምርጫ” ወስደን እንኳ ብናዬው የፌዴራሉ መንግስት ሀጥያት እጅግ ግርም የሚል ነው። “ምርጫ ቦርድ” ልክ እንደመከላከያ ሰራዊቱ፣ እንደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ፣ ወዘተ ሁሉ በህገ-መንግስቱ ቋንቋ መሰረት የፌዴራል መንግስት ተቋም ነው። ስለሆነም ምርጫ ሲያስፈጽም የፌዴራል መንግስቱን መዋቅርና የጸጥታ ሀይል ይዞ መሆን እንደሚገባው ምንም ክርክር የሚያስነሳ ጉዳይ አልነበረም። የፌዴራል መንግስቱ ህገ-መንግስታዊ ስልጣን ተሽሮ የክልሉ መንግስት በተገላቢጦሽ ለምርጫ ቦርድ ምርጫ እንዲያስፈጽም ትእዛዝ የሰጠው በሚያስመስል መንገድ ነገሩ ሁሉ ተጨመላልቆ፣ ቅዘን በቅዘን ሁኖ፣ ትዝብት በትዝብት ሁኖ፣ ወዘተ አለፈ።

የምርጫ ቦርዱን አሰፋሪ ምግለጫ አገው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሁኔታ የሚከታተሉ የውጭ አካላት ጭምር በአገው ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በትዝብት ተመልክተውታል፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን እንግዲህ የፌዴራሉ መንግስት ሱዳንና ኬንያ ደንበር ላይ ሁኖ የማይመለከተው መስሎ መታዘቡን ቀጥሏል። ሺ ተምሊዬን የቅሬታ ደብዳቤዎች ወደፌዴራሉ መንግስት ቢጎርፉም ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ተቀደው እየተጣሉ መሰለኝ ወይም ደግሞ የፌዴራል መንግስቱ ዳር ቁሞ የሚመለከትበት “ድብቅ አጀንዳው ስለሚይዘው” መሰለኝ እስካሁን የምንፈልገው የጥያቄ መልስ እውን አልሆነም።
11) የክልሉ ቀበሮ መንግስትም “ሰውን ማመን ቀብሮ ነው” እንዳለችው ቀበሮዋ “የቅማንት ህዝብ ጥያቄ የሚፈታው ‘አስተባባሪ ኮሚቴው’ መቀበሩን ሳረጋግጥ ነው” ያለ በሚያስመስለው መንገድ እያደባና እያለዛለዘ መዳከሩን ቀጥሏል። የቅማንት-አገው ህዝብ ደግሞ “አስተባባሪ ኮሚቴው ውስጤ ነው!” ማለቱንና በአደባባይ ማወጁን ቀጥሏል። የፌዴራል መንግስቷም ድሮም ዳር ሁና መመልከቷን አብዝታው ነበርና አሁን ላይ ግራ ተጋብታ ድንግርግር ብሏት መላው ጠፍቷት “መጽሁፉም ዝም ቄሱም ዝም” እንዲሉ ዝምታን መርጣ ቀጥላለች። የተለያዬ አጀንዳ ያላቸው ነገር ግን “ለኢትዮጵያ ህዝብ” ግልጽ ፍንትው አድርገው “አጀንዳቸውን” ያላሳወቁ በርካታ ቁጥር ያላቸው “ተቃዋሚዎች” ደግሞ ድብቅ አጀንዳቸውን ለማሳካት በቅማንት-አገው ህዝብ፣ በክልሉ መንግስትና በፌዴራሉ መንግስት መካከል የተፈጠረውን ውጥረትና ተፋጦ መተያዬት እንደትልቅ መግቢያ ቀዳዳ በመሻት “ትርምስና ቀውስ” ለመፍጠር “ሌት ተቀን” ከበሮ ድለቃና ፋኖ ተሰማራ ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። የመጨረሻው ውጤት በትክክል ምን እንደሚሆን ደግሞ የሚያውቀው “እግዚአብሄር” ብቻ ነው!
በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ለቅማንት-አገው ህዝብ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ያለአግባብ መዘግዬት “ዋናው” ተጠያቂ “የፌዴራሉ መንግስት” ነው ብዬ እከራከራለሁ።

“ብልሹ የመንግስት አሰራር እስካለ ድረስ የነጻነት ትግሉ ተፋፍሞ መቀጠሉ የማይቀር ነው!”
ቸር ወሬ ያሰማን! አሜን!

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.