Urgent Call Regarding Kemant Self-Rule Implementation Process

The Kemant Self-Rule Implementation Watch (KSRIW) has posted urgent call to the public on facebook.  The KSRIW has complained that the Regional Government, especially Mr. Gedu Andargachew’s faction has employed two tactics to exclude Kemant kebeles in Quara and Mateme. According to the post, the tactics are:

  • Harassment and intimidation against the Kemant Committee members sign to exclude these kebeles from Kemant Self-Rule.
  • An attempted bribe to some committee members to create a division within and ultimately influences their decision.

The KSHRIW warned the committee members not accept such conditions and call on the Kemant public to be vigilant. The KSRIW has also called the Federal Government to keep its constitutional promises and take immediate measures to assure the Kemants’ the constitutional rights. Here is the full post in Amharic:

በጣም አስቸኳይ! Share…Share…. and comment!!
ዘመቻ 42 ተጠናክሮ ቀጠለ!
$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$$
እንደሚታወቀዉ ላለፉት 25 አመታት የቅማንት ህዝብ ህገ-መንግስታዊ መብቱን ለማስከበር እሰከ ዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የሚደርስ ግፍ ተፈጽሞበታል አሁንም እየተፈጸመበት ይገኛል፡፡በተለይም ባሁኑ ሰአት ሁሉም ቀበሌዎች በሚባል መልኩ የህዝበ ዉሳኔ የተካሄደ ሲሆን በመተማና በቋራ የሉ ቀበሌዎች ወደ ቤህሩ አስተዳደር እንዳይካተቱ የክልለሉ አንባ ገነን መንግስት የቻለዉን ሁሉ እንቅፋት በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ህዝቡም መብቱን ለስከበር ከመረጣቸዉ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ክልሉ ይህን የሚያደርገዉ አካባቢዉ ለምና የተፈጥሮ ሃብት የሚገኝበት በመሆኑ፤በተጨማሪም ቅማንት አካባቢዉን ነቅቶ በመጠበቅ ከኤርትራ ትምክት በማሰልጠን ሃገር እንዲያተረራምሱ የሚልካቸዉን ታጣቂዎች መተላለፌያ በመንፈጉ፤ አስተዋዩና ጀግናዉ የቅማንት ህዝብ ትምክት ባደራጀዉ በጎንደሩ ብጥብጥ እራሱን በማግለሉና ሃገሩን በማስቀደሙ፤ የትምክት ሃይሎች በቅማንት ላይ ጥርሳቸዉን እንደነከሱ የሚታወቅ ነዉ፡፡ ትምክት ቅማንትን ከናካቴዉ ለመደምሰስ ከጽንፈኛ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት ይመቸረሻዉን ትግል በቅማነት ለይ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የመተማና የቋራ አካባቢ ከኢኮኖሚያዊዉ ጠቀሜታዉ ባሻገር ሃገራችን ለማተራመስ የትምክት ሃይሎች ከግብጽና ከኤርትራ እያሰለጠኑ የሚልኳቸዉን ሃይሎች ያለምንም እንቅፋት ሰተት አድርጎ ለማስገባት ቅማንትን በተለያየ ሁኔታ በማዳከም አካባቢዉን ከቅማን አስተዳደር ዉጭ በማድረግና ለማጽዳት ስዉርና ግልጽ አጀንዳ ተነድፎ በመተግብር ላይ ይገኛል፡፡
ባለፈዉ አመት ህዳር ወር መተማና ቋራ ላይ ከ 100 በላይ የቅማንት ተወላጆች በግፍ የታረዱት እጅግ በዙዎት የቆሰሉት፤ግምቱ ከ 42ሚሊዩን ዶላር በላይ የሚሆን የቅማንት ህዝብ ሃብትና ንብረት የተቃጠለበትና የተዘረፈበት፤ማዉራ ላይ ከ40 በላይ የሚሆኑ ህጻናት፤አራስ እናቶች፣ነብሰጡር እናቶች፤አቅመ ደካማ አዛዉንቶች በገጀራ የታረዱት እንስሳት በጥይት ተደብድበዉ ያለቁት፡፡እንዲሁም አይከል ገብያ ላይ ቅመንት በመሆናቸዉ ብቻ በጠራራ ጸሃይ በስናይፈር ተደብድበዉ ያለቁት ከ12 በላይ ተወላጆች፤ቅማንተ የሚኖረዉ ከ128 ቀበሌዎች በላይ በመሆኑ መብታችን ተረግጧል በማለታቸዉ ብቻ እንጅ ወንጀለኛ ስለነበሩ አይደለም፡፡
ችግሩንም ከናካቴዉ ለመፍታት ብአዴን ታድሻለሁ ሙሉ በሙሉ የህዝቡን ጥያቄ እመልሳለሁ በማለቱ ከብአዴንና ከቅማነት ኮሚቴዊች ተወጣጥቶ የራስ አስተዳደሩን ለመመስረት ስራ በመጀመሩ ህዝቡ እፎይታ እናገኛለን የሚል ተስፋ አሳድሮ በትግስት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
ሆኖም ግን የክልል 3 መንግስት አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ እያለ ይገኛል፡፡ ማሞኛዉም መጀመሪያ በ42 ቀበሌዎች አስተዳደሩ ይቋቋምና ከዚያ በኋላ የቀሩት ቀበሌዎች ይጠቃለላሉ የሚል ማሞኛ ነዉ፡፡ ይህማ ዱሮ ገና ዱሮ ከላይ የተጠቀሰዉ መከራ ና ግፍ በህዝባችን ላይ ከመድረሱ በፌት የትምክት ምክር ቤት ወስኖ ነግሮን ነበር እኮ፡፡ታዲያ ብአዴን የታደሰዉ ምኑ ላይ ነዉ፡፡
ስለሆነም ባሁኑ ሰአት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የቅማንት ህዝብ ተወካችን በተለያየ ሁኔታ በማስፈራራት አስገድደዉ ለማስፈረም ሙከራ እየተደረገ ስለሆነ መላዉ የቅማንት ህዝብና ወጣት ይህ የህዝባችን መብት የሚጎዳ ዉሳኔ እንዳይወሰን ከኮሚቴዉ ጎን በመቆም አሁን ክልሉ የሚያደርሰዉን የዘመቻ 42 ጫና ለህዝባችን በማሳወቅ መብቱን እንዳይነጠቅ የበኩላችንን የምንወጣበት በጣም መስቀለኛ መንገድ ላይ የምንገኝ መሆኑን መገንዘብና ማሰገንዘብ ይኖርብናል፡፡ኮሚቴ አባላትም በጫናና በማስፈራራት ታሪካዊ ስህተት እንዳይፈጽም ይሀንን ጉዳይ ለህዝብ አሳዉቃለሁ ባለዉ አቋሙ በመጽናት ጉዳዩን ለመላዉ ህዝብ በማዉረድና ዉይይት እንዲካሄድበት በማድረግ ታሪካዊ አደራዉን ሊወጣ ይገባዋል፡፡
ጉዳዩ በጣት የሚቆጠሩ የቅማንት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ብቻ ሳይሆን የ1.5ሚሊዮን የቅማንት ህዝብ ጥያቄ ነዉ፡፡ኮሚቴዎችን ማስፈራራትና ማወከብ ዉጤቱ የዜሮ ድምር ይሆናል፡፡
ክልሉ ይህን እያደረገ የሚገኘዉ ከዚህ ቀደም 42 ቀበሌ ብቻ ብሎ የወሰነ በመሆኑ የክልለሉን ከፍተኛ ጨቋኝና እጃቸዉ በቅማንት ደም የተጨማለቁ ባለስልጣናት ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ የተሸረበ ሴራ መሆኑን በመገንዘብ፤የክልሉ ትምክት ም/ቤት ያስተላለዉን የ42 ቀበለ ዉሳኔ እንዲሽር ሁላቸንም በያለንበት እንደ አንድ በመሆን ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል ይገባናል፡፡
በተጨማሪም የፌዴራሉ መንግስት እጅግ የተንዛዘኣዉን የቅማንትን የመብት ጥያቄ መቋጫ ያገኝ ዘንድ ድርሻዉን በመወጣት ቃሉን ሊያከብር ይገባል፡፡የሃገራችን ንነህዝቦችም ይህን ዘር ተኮር የሆነ የክልል 3 ጨቋኝ መንግስት በቅማንት ህዝብ ላይ የሚፈጸመዉን ወንጅል፡ግፍና በደል በመገንዘብ ከህዝባችን ጎን ትሰለፉ ዘንድ ታሪካዊ ግዴታ አከባችሁ፡በቅማንት ህዝብ ላይ ዘር በማጥፋት እየተለማመደ ያለዉ ትምክት ሃይል ነሚኒሊክን አስተሳሰብ በመመለስ እናንተም ላይ ግፉ አለመድረሱ ማረጋገጫ የላችሁም፡፡
በተለይም ኮሚቴዎችን ለመከፋፈልና በገንዘብ ለመደለል እየተደረገ ያለዉ፤የማስፈራራትና እንቅፋቶችን መፍጠር ሴራ መንግስት ሊያስቆምና የህዝባችንን ድምጽ ሊያከብር ይገባዋል፡፡ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ከዉጭ ከጎ/ህብረትና ከሌሎቸ ጽንፈኛ ቡድኖች በሚለካ ዶላር ያሚያደርገዉን ጫና ሊያቆም ይገባል፡፡
በክልሉ መንግስት የቅማንት ጥያቄ እንደማይመለስ ህዝቡ በግልጽ አስረድቷል የክልሉ መንግስት ዴሞክራሲያዉዊ ጥያቄዎችን የመፍታት ሞራሉም ብቃቱም የለዉም፡፡ይህንንም በተግባር ለሃገራችን ህዝቦች አሳይቷል፡፡ይሁን እንጅ የፌዴራሉ መንገስት ጣልቃ በመግባት ባስቸኳየይ የማይፈታዉ ከሆነ ከዚህ ቀደሙ የከፋ የዘር ማጥፋት ለመፈጸም የገዱ አንጃ እያሴረ እንደሆነ እያየን ነዉ፡፡
ህገ-መንግስቱ ለቅማንት ህገ መንግስታዊ መብት ለማስከበር ሲሆን እንዴት ጥርስ የሌለዉ አንበሳ ሊሆን ይችላል? ጎበዝ ሃገሪቱ ወደየት እያመራች ነዉ?
ድል ለመላዉ የአገዉ ነገድ!

 

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

One Response to Urgent Call Regarding Kemant Self-Rule Implementation Process

  1. Demeke says:

    You guys, don’t worry. I have information. Everything is under control..

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.