ይድረስ፡  ለአቶ ይግዛው አጥናፉ

ካሉበት

ከበቃኸኝ አንተነህ: ጎንደር

ለወልቃይት የአማራነት የማንነት ጥያቄ የቅማንትን ቅማንትነት እንደመያዦ (collateral) አትመልከቱት

በዘ-ሀበሻ ድህረ-ገፅ ላይ ‹‹ወልቃይትን አዳፍኖ ቅማንት የዘከረው የጎንደሩ ጉባዔ›› በሚል ርዕስ ጥር 16/2009 ግላዊ ስሜትክን ማንፀባረቅህ ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው ሌሎች እነ ዳግማዊ መዐሕድ፣ ቤተ-አመራ፤ እና የእነሱ ተከታዮች አነ ዓንዱዓለም ተፈራ፣ ሙሉቀን ተስፋው እና እጅግ መረን የለቀቁ ስማቸውን ለመጥራት የሚቀፉኝ ግለሰቦች ከአስተላለፉት መልዕክት ጋር ሲታይ የአንተው በጣም ጤነኛ እና ለጎንደርም ሆነ በጎንደር አካባቢ ለሚኖሩ ህዝቦች መለካም ነው ያስብል ይሆናል፡፡ነገር ግን የጹህፈህን ተክለ-ቁማና ከማንም ጋር ሳያወዳደሩ ከተመለከቱት የእርሶዎ ጹህፍም ስሜት የተጫጫነው እና ‹‹ከባልሽ ባሌ ይበለጣል—-›› አንዳለችው ብልጥ ሴት አይነት ተረትን ያስተውሳል፡፡ ቢሆንም ያስተላለፉት ሀሳብ ከመንሳዊ ቅናት ጋር የተያያዘ ሊሆን ስለሚችል ብዙም አያስብልም::

ለዚች አገር እና ህዝቦች በሠላም እና በፍቅር አበረው በመኖር መፃኢ እድላችን ይበልጥ ለማሳመር ለአንድ የእኛ ለምንለው ህዝብ የምንጨነቀውን ያክል ለሁሉም ብንጨነቅ አገራችን የምድር ገነት ትሆነ ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊያን የልዩነታችን ምንጭ የደም እና የአጥንት ልዩነት ሳይሆን የአስተሳሰብ ቀና ካለመሆን ብቻ የሚመነጭ ነው፡፡ኢትዮጵያዊያንን አካባቢን፣ ሀይማኖትን እና ጠባብ ጎሰኝነትን መሰረት በማድረግ ለዘመናት አንድነታችን ሳይሆን ልዩነታችን ስንሰብክ ኖረናል፡፡ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርን የአንድ  የአዳም ልጅ መሆናችን ዘንግተን እና የፈጣሪን ድንቅ ሥራ ባራከሰ መልኩ አንዱ ከእንጨት እና ከሰሳ፤ ሌላው ከሌላ እንሰሳ ሌላው ደግሞ ከዛፍ ላይ አውርደን ያላመድነው እንሰሳ ያከል ስም ሰንሰጠው፣ ስንንቀው፣ ስናበሻቅጠው መጥተናል፡፡ ያ ለዘመናት የተከማቸ እና ብሶት የወለደው የንቀት አተላ ኢትዮጵያዊያን የጎሪጥ እንዲተያዩ በር ከፍቶላቸዋል፡፡ ለጊዜው በተለዩ ህዝቦች የደረሰውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሀይማኖታዊ ሰቆቃዎችን መዘርዘር አልፍለግም፡፡ ግን ይህን ያለፈ የተሳሳተ መንገድ በመዘንጋት በዘመነ ወያኔ(ኢህአዴግ) ተዘርቶ ያደገ ሴራ ተደርጎ ሲታይ እጅግ አዝናለሁ፡፡ እኔ ኢሀአዴግ ይህችን አገር ከማስተዳደሩ በፊት በቅማንትነቴ ብዙ መከራን አሳልፊያለሁ፡፡ ወገኖቸ ከእነሰሳ ያነሰ ክብር ተሰጥቷው ቅማንትን ከገደለ አረመኔ ይልቅ የዱር እንሰሳ ለገደው ሌላኛው ጨካኝ ክብር ይጎናጸፍ ነበር፡፡ ይህ በቅማንት ህዝብ ላይ የተፈፀመ የቅርብ ዘመን የግፍ ድርጊት ነው የምነግራችሁ፡፡ ይህን ለማታውቁት ቅማንት ከአማራው ህዝብ የተለየ ምን በደል ደረሰበት ትሉ ይሆናል፡፡ ይሁንእንጅ በዚያ ዘመን በነበረው የአስተሳሰብ ደረጃ በመነሳሳት በተለያዩ የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ለተፈጠረው  የተንሸዋረረ አመለካከት የየትኛውም የማህብረሰብ ክፍል ወይም በዚህ ዘመን ላለ ትውልድ ተጠያቂ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ የአሁኑ ትውልድ ተጠያቂ የሚያደርገው የባለፈው  ሥርዓት ለአገዛዙ ያመቸው  ዘንድ በህዝቦች መካከል   ያሰፈነውን የመናናቅ፣ የማጥላላት፣ አንዱን ርኩስ ሌላውን ቅዱስ እርስ በእርስ እንዲተያይ የሄደበት የተሳሳተ መንገድ  የዞረ ድምር  ለማራመድ መሞከር ብቻ የአሁኑን ትውልድ ጥፋተኛ እና ተጠያቂ ያደርገዋል፡፡ ዛሬም በልጅነቴ በማንነቴ እና በሌሎች ማንነት ዙሪያ ሲደመጡ እና ሲነገሩ የነበሩ ጸያፍ ቃላቶች እና አሰተሳሰቦች አንዳንድ የዛሬው ትውልድ ተሸክሟቸው በመዚር ላይ ይገኛል፡፡ እጅግ ያሳፍራል፡፡

ወደተነሳሁበት አርስ ለመመለስ ያክል ዳግማዊ መዐሕድ ኢትዮጵያ የብዙ ነገድ አገር መሆኗን በመዘንጋት በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ የአማራ ህዝብ አንመሰርታለን፤ ለዚህ እውን መሆን ደግሞ፣ አገው፣ ቅማንት፣ ወይጦ ኦሮሞ፣ አርጎባ ወዘተ የሚባል ህዝብ በሚቋቁመው የህልም ግዛት(Dream state) ማየት ስለማልፈልግ እነዚህ ህዝቦች ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ወደ አማራ ማንነት ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲጠቃለሉ የሚል መግለጫ በድርጅታዊ መግለጫው አውጥቷል፡፡ ለዚህ ምስክር ይሆን ዘንድ በዘ-ሐበሻ ድህረ-ገጽ ላይ ጥር 27/2009 ዳመዐሕድ “እንደ በለሴውም ሆነ እንደ ወገሬው፤ እንደ ፋርጣውም ሆነ እንደ መንዜው፤ እንደ አገውም ሆነ እንደ ወልቃይቴው – ቅማንትም አማራ ነው›› በሚል ርዕስ ባስተላለፈው መልዕክት ለቅማንት እና በሌሎች ህዝቦች የአለውን ንቀት በግልፅ አሳይቷል፡፡ እርግጥ ነው መልስ መስጠት የነበረብኝ ለዚህ ጫፍ የረገጠ ጹህፍ እና አመለካከት ነበር፡፡ ይሁንእንጅ ይህ ድርጅት ይህን የፃፈበት ህሊናው የሌሎችን ሀሳብ እና አቋም ላለመስማት በሩን ከርችሞ የዘጋ ስለሆነ መልስ አያስፈልገውም ከሚል የግል አቋም ነው፡፡ ይልቅ እንዲህ አይነት የአበደ ሀሳብ የሚያራምዱ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን ሲመጡ እንደአመጣጣቸው ለመመለስ ራስን አዘጋጅቶ መጠበቅ ይሻላል፡፡ ይህ ድርጅት (ዳመዐህድ ተብየው) ዓላማው በግልፅ ቅማንትን አማራ ማድረግ እንጅ አማራም ቅማንት ነው ለማለት ድፍረቱን አላገኝም፡፡ ዘላለማዊ ክብር እና ድል የሚመኘውም ለአንድ ህዝብ ብቻ ነው፡፡ ለዐማራ! መመኘቱ አይከፋኝም  ክፋቱ ድል ተደራጊው እኔ እና ሌሎቹ መሆናችን ሳስብ የዚህ ድርጅት የሚቆምበት ገደል ርቀት ይታየኛል፡፡

ለአርሰዎ ጹህፍ መልስ ለመስጠት የፈለኩትም ቢያንስ እርሰዎ ከእዚህኞች ስብሰብ በመጠኑ ይሻላሉ በሚል ነው፡፡ የጹህፈዎ እርስም በግልጽ  አንደሚያሳየው የቅማንትን ቅማንትነት የተቀበለ ህገ-መንግሥት ለወልቃይት አማራነትም ሊሆን ይገባል በሚል መንፈስ የተጀመረ ይመስላል፡፡ ምን አልባት የቅማንት ህገ-መንግስታዊ የራስ አስተዳደር ጥያቄ እንዴት ሥርዓቱን በጠበቀ እና ህግን ባከበረ መልኩ እየሄደ እንደሆን ያጡት አይመሰልኝም፡፡ የቅማንት ህዝብ የቅማንትነት ማንነት በማንሳቱ በገልፅ ጦርነት ታውጆበት የዘር ማጥፋት ሙከራ ተካሂዶባታል፣ ቅማንት ቅማንት በመሆኑ ብቻ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በግፍ ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል፣ የመንግሥት ሰራቶኞች ከስራቸው ተባረዋል፡፡ ይህ ሁሉ ተደርጎበት የቅማንት ህዝብ በህገ-አምላክ ከማለት ውጭ ነፍጥ እንደአማራጭ መፍትሄ አልተጠቀመም፡፡ ጥያቄውን ሳያሰልስ ገፍቶ ከብዙ የህየወት መስዋትነት በኋላ ቢሆን ጥያቄው መልስ ሊያገኝ ጫፍ የደረሰ ይመስላል፡፡ ግን እርሰዎ አንድ ትልቅ የዘነጉት ነገር አለ፡፡ ይኸውም የቅማንት የውስጥ የራስ አስተዳደር እንደኤርትራ መገንጠል አድገው የተረዱት ይመስለኛል፡፡ የቅማንትን ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትም የወያኔ ድብቅ ሴራ አድርገው እና ቅማንት ለዚህ አቅሙ የሌለው በማስመሰል ሀሳብ አራምደዋል፡፡ በዚህ አመለካከተዎ ቅድም ከሌሎች ድርጅቶች እና ግለሰቦች ይሻላሉ ካልኳቸው እኩል ወርደውብኛል፡፡ ሲጀመር የቅማንት ህዝብ በማንም የወጭ ሀይል ግፊት ተነሳስቶ የጠየቀ ሳይሆን ህገ-መንግሥቱ በገልፅ ባስቀመጠው መንገድ የተጓዘበት ሂደት ነው፡፡ የአማራ ህዝብ እና በኢትዮጵያ ያሉ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት ያላቸውን ያክል ቅማንትም ባለመብት መሆኑን ከእነከኣቴው ዘንግተውታል፡፡ እርሰዎ ለወልቃይት ህዝብ የአማራነት ማንነት የሚጨነቁትን ያክል የቅማንት ህዝብ ለቅማንትነቱ እጅግ ቀናኢ ነው፡፡ የቅማንት ህዝብ በሌላ ማንነት  በውሸት ከሚኮፈስ ይልቅ አላዋቂዎች በስሙ ቢሰድቡት ይመርጣል፡፡ ስለዚህ የቅማንት ህዝብ የትግል መነሻ እርሰዎ እና ሌሎች በተደጋጋሚ እንደሚሉት በወያኔ ሴራ ተጠንስሶ የተጠመቀ ጥያቄ ሳይሆነ በቅማንት ልጆች ተረግዞ የተወለደ የትግል ውጤት ነው፡፡

ሌላው እጅግ የወረደው እና ሌሎች ተሳስተው ሌላውን እንደሚያሳስቱ ግለሰቦች የሆንክብኝ የቅማንትን ጥያቄ በክልሉ እንዳሉ ሌሎች ብሄረሰቦች ተመልክቶ ከማየት ፋንታ ቅማንት በቀጣይ ከትግራይ ክልል ጋር ለመቀላለቀል እና የአማራን ህዝብ ለመከፋፈል የተደረገ ሴራ አድርገህ መናገርህ ለዚህ ህዝብ አንተም የተዛባ እና የተንሸዋረረ እይታ ያለህ መሆኑን በግልፅ  ያሳያል፡፡ የቅማንትን ህዝብ ዘገይቶም ቢሆን የውስጥ የራስ  አስተዳደር እንዲጠይቅ ከገፉት አብይ ምክንያቶች ዋነኛው እንዲህ አይነት የተዛባ አመለካከት እና የአማራ ክልል መንግሥጥት በዚህ ህዝብ ላይ በዘሩ ምክንያት ለባለፉት 20 ዓመታት ያደረሱበት ግፍ ጭምር ነው፡፡ የኢሳቱ መሳይ መኮንን በእየለቱ በቅማንት ህዝብ ላይ የሚረጨው የዘር ጥላቻ  ቅማንት ራሱን እንዲፈትሽ አስገድዶታል፡፡ እነመሳይ የቅማንትን ህዝብ ከጎንደር እና ከሌላው አማራ ጋራ ያጋጩ መስሏቸው በጎንደር አካባቢ በትግራይ ህዝብ ላይ በተደረገው ማፈናቀል እና የሀብት ወረራ አልተሳተፈም፣ ራሱን አግሏል በሚል የዘር መርዙን ሲረጭ ከርሟል፡፡ የቅማንት ህዝብ መቸም ቢሆን ከግፈኞች ጋር በመወገን አንድን ዘር ለይቶ ሊያጠቃ የሚችልበት፣ ሀይማኖታዊ አስምሮም  ሆነ የሞራል አስተሳሰብ የለውም፡፡ የትግራይ ህዝብ እንደሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኑ እነደሆነ አጥብቆ ያምናል፡፡ በመሆኑም ያን የግፍ ድርጊት አልተቀላቀለም ተብሎ ‹‹የወያኔ ባንዳ›› እየተባለ ሊሰደብ አይገባውም ነበር፡፡ የቅማንት ህዝብ ጠላቱን ጭምር አንደወዳጁ በማየት አብሮ የኖረ ህዝብ እንጅ ከግፈኞች ጋር በመወገን ግፈኛ ሊሆን አይችልም፡፡

በመጨረሻ ባልከው ነገር እስማማለሁ በቅማንት ህዝብ ላይ ሰፊው የአማራ ህዝብ የተለየ ግፍ አላደረሰበትም፡፡ በቅማንት ህዝብ ላይ ግፍ ሲያደርሱ የነበሩ ድሮም ዛሬም በሥርዓቱ የተሰገሰጉ የሥልጣን ጥመኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ገዥዎች ከትናት አስከዛሬ በስሙ ከመነገድ እና የግል ጥቅማቸው ከማሯሯጥ ውጭ ለዚህ ምስኪን አማራ ህዝብ ከድህነት ሊያላቁት አልቻሉም፡፡ ይህ ህዝብ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ እኩል በድህነት የሚኖር ነው፡፡ በመጨረሻ እንድታውቁልኝ የምፈልገው የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ላይመለስ ጉዞውን ቀጥሏል፣ በቅርብ ቀንም የራሱ የውስጥ አስተዳደር ይመሰርታል፡፡ ይህን ማንንም ሀይል ሊመልሰው አይችልም፡፡ ግን ይህን የቅማንትን ስኬት ከሌላ የፖለቲካ አጀንዳ ጋር በማያያዝ የእዳ መያዣ ባታደርጉት እና ጉዳዮችን በየፍርጃቸው ብትመለከተቷቸው ለወደፊት የጎንደርም ሆነ የኢትዮጵያ አንድነት ይበጃል እላለሁ፡፡

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

3 Responses to ይድረስ፡  ለአቶ ይግዛው አጥናፉ

  1. befdgwf says:

    i don’t belive this statment is from qimant because amhara/gonderian didn’t kill or strugle wiz qimant in history, but if they are interestet to regain/change or any it is their humanrights.

  2. ኪቫ says:

    በጣም ቆንጅ አመላካከትም መንገድም መፍትሔም አቀራረብም ነው።
    በተለይ አንድ የተበደለ ዜጋ ለችግሩ መፍትሔ ሲጠይቅ የእከሌ አጀነዳ ነው የሚበለው የወረደ አና የኮሰመነ ሀሰብ የሜመነጩ ግለ-ሰቦች በራሳቸው ማፈር አለባቸው፡፡ ኅሊና ከአለቸው ማለቴ ነው፡፡

  3. Pingback: ጂራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሐል – Enkoklshglobal እንቆቅልሽ አለምአቀፍ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.