ጎንደር እና ጎንደሬዎች

ከ በቃሐኝ አንተነህ

ጎንደር የሚለው ሥርወ-ቃል ከአገው ቅማንት ከሚመደበው ከመንትነይ ቋንቋ የተገኘ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ አንዳንድ ፀሀፊዎች ግን የቃሉን ትርጉም አዛብተው ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ትርጉሙንም በ(ጎን እደር) ማለት ነው ይላሉ፡፡በሰሜን ምዕራብ አካባቢ ጥንታዊ የሆኑት ህዝቦችም የኩሽ አካል የሆኑት የአገው ህዝቦች በተለይም የቅማንት እና ራሳቸውን ከ13ኛው ክፍለ-ዘመን በኋለ ከእስራኤል በመጡ የአይሁድ እምነት አራማጆች ራሳቸውን ከቅማንት ህዝብ የገነጠሉት የአይሁድ እምነት ተከታዮች ህዝቦች ነበሩ፡፡
በ15ኛ ክፍለ-ዘመን ግራኝ አህመድ ወደሰሜን ኢትዮጵያ የእስልምናን ሀይማኖት ለማስፋፋት ከአደረገው ጦርነት ጋር ተያይዞ ‹‹ቅማንቶች እና ቤተ-እስራኤሎች ከግራኝ አህመድ ጎን ተሰልፈው ክርስቲያኖችን ወግተዋል›› በሚል የተሳሳተ ክስ ምክንያት በፖርችጋሎች የጦር እገዛ ግራኝ አህመድ ጎንደር አካባቢ ደንቀዝ በሚባል አካባቢ ከተገደለ በኋላ በቅማንቶች እና በቤተ እስራኤሎች ላይ ከባድ የሆነ የማጥመቅ ዘመቻ ተካሄደባቸው፡፡ ቤተ-እራኤሎች (ስሜነኞች) ክርስትናን ላለመቀበል ከባድ ተቃውሞ በማሳየታቸው ከ15ኛ አስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የዘለቀ ከባድ የማጥመቅ እና ያልተጠመቁትን ደግሞ ከመሬታቸው እንዲፈልሱ ተደረገ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹‹ፈላሻ›› የሚል ስም ተሰጣቸው፡፡ በተለይ በወገራ፣ በጠለምት በጃናሞራ እና በበየዳ አካባቢ የነበሩ ቤተ እስራኤሎች ከባድ ጦርነት ተካሂዶባቸዋል፡፡ የዘር ማጥፋት ወንጀልም ተፈፀመባቸው፡፡
በቋራ፣ በአለፋ፣ በደንቢያ፣ በኢንፍራዝ፣ ጎንደር ዙሪያ በከፊል ጭልጋ ይኖሩ የነበሩ ቅማንቶች እና በኋላ ራሳቸውን ቤተ-እስራኤል ያሉት በሰሜን አካባቢ የተካሄደው የዘር እልቂት መረጃው ስለደረሳቸው እና ከመሬታቸው ላለመፍለስ ያለማንገራገር ክርስትና ሀይማኖትን በቀላሉ በመቀበላቸው ከመሬታቸው ሳይፈልሱ የመሬት ባለቤት በመሆን ቀጥለዋል፡፡ ለእነዚህ ህዝቦች ከጥምቀቱ ጋር አብሮ የሚሰበከው ‹‹ክርስትናን የተቀበለ ህዝብ ቅማንትኛ ከተናገረ ሀይማኖቱ ይረክሳል›› ስለሚባል እምነቱን ከተቀበለ ማግስት ጀምሮ የራሱን ቋንቋ ላለመናገር ውግዝ አለ፡፡ ሲናገር ከተገኘ ይንቋሸሽ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ራሳቸውን አማራ ብለው በሚጠሩ ህዝቦች የሚኖሩባቸው ቦታቸው ዛሬም ድረስ በቅማንትኛ ቋንቋ በመጠራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ኳራ (ቋራ፣ አለፋ፣ ጣቁሳ፣ ደልጊ ጫን ድባ፣ ጨው ድብ፣ ቆላ ድባ ወዘተ) መዘርዘር ይቻላል፡፡
በአርማጭሆ፣ በጭልጋ እና በወገራ አካባቢ የነበሩ ቅማንቶች ክርስትናን ቢቀበሉም ሙሉ በሙሉ ከህገ-ልቦና (ኦሪት) እምነታቸው መላቀቅ አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ቦታዎች የቅማንት ወንበሮች (የሀይማኖት እና የፖለቲካ መሪዎች) የነበሩባቸው አካባቢዎች በመሆናቸው የክርስትና ሀይማኖቱን የተቀበሉ ቢመስሉም እስከቅርብ ድረስ የራሳቸውን እምነት ያንፀባርቁ ነበር፡፡ ከዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት መሰረቷ ከህገ-ልቦና ተነስቶ ወንጌል ሲደረስ የኋለኞችን የእምነት ሥርዓት ሙሉ በሙሉ በመሻር ሳይሆን በላዩ ላይ እየጨመረች ነው፡፡ በኦርቶዶክስ እምነት የተለያዩ የኦሪት እና የህገ-ልቦና ኢለመንቶች በስፋት ይታያሉ፡፡ በቤተ-ክርስቲያን ዙሪያ የሚታየው ዛፍ ከከቅማንት እና ከቤተ እስራኤሎች የጾለት ቦታ ተምሳሌት የተወሰደ ነው፡፡ በአብዛኛው ቤተክርስያኖች በተራራ አካባቢ የሚሰሩትም ከአብርሀም የእምነት ተምሳሌት ጋር ይያዛል፡፡ ይህ የቅማንቶች የመፀለያ ቦታ ከጎንደር አልፎ አስከበጌምድር አስቴ ቆማ ፋሲለደስ ድረስ ይደርስ ነበር፡፡
ይህ በግልፅ የሚያሳየው የሰሜን ጎንደር ህዝብ በተለይ የበጌምድር እና የጎጃም ህዝብ በአጠቃላይ ምንጩ አገው ለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃ አያስፈልግም፡፡
በመሆኑም የሰሜን ጎንደር ህዝብ በአንድም ሆነ በሌላ ከአንድ የዘር ሀረግ የሚቀዳ ህዝብ ነው፡፡ ይህን ህዝብ ገዥዎች በማናናቅ፣ አንዱን ከፍ ሌላው ዝቅ በማድረግ ለዘመናት አቆራቁሰውታል፡፡ በተለይ ቅማንትነቱን ጠብቆ ለማቆየት በፈለገው እና ቀድሞ በተቀየረው የአገው ህዝብ መካከል ከባድ የጥላቻ መርዝ ተረጭቷል፡፡ ለዚህ ገዥዎች እና የገዥዎች የቀኝ እጅ የነበረችው የ‹ቤተክርሰቲያን› (ኦርቶዶክስ) እምነት መሪዎች ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ያም ሆኖ ህዝቡ ግን በፍቅር ተጋብቶ፣ ተዛምዶ መኖሩን እስካሁን ድረስ አላቆራጠም፡፡ ይሁን እንጅ የዚያ የተዛባ አመለካከት ዛሬም ድረስ ዘልቆ በሁለቱ ህዝቦች (በቅማንት እና ራሱን አማራ በሚለው የጎንደር ህዝብ) (ሌላ አካባቢ ራሱን አማራ የሚለው አላልኩም) መካከል እነዚህ የግፍ ወራሽ አመራሮች ለማቆራቆስ ሞክረዋል፡፡ በ2008 ዓ.ም በቅማንት ህዝብ ላይ የተደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀል የባለፈው ሥርዓት ውርስ ውጤት ነው፡፡ ሁለቱ ህዝቦች ግን በግልፅ ጦርነቱን ለአወጁት የክልሉ አመራሮች ‹‹እኛ አልተጣላነም›› ነበር ያሏቸው፡፡
የክልል አመራሮች እነዚህን ህዝቦች በማጋጨት ከሚያገኙት ቡድናዊ ጥቅም ይልቅ እነዚህ ህዝቦች አንድ መሆናቸውን በመስበክ የጎንደርን እና አካባቢዋን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ቅማንትን የገነጠለ ልማትም ሆነ ኢኮኖሚ እድገት በጎንደር አካባቢ ማረጋገጥ አይቻልም፡፡ የተለያዩ የፖለቲካ አመራሮች እና ድርጅቶች ይህን ተገንዝበው መሥራት ካልቻሉ መቸም ቢሆን ጎንደርን ሰላም ማድረግ አይቻልም፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች (በግልፅ መጥቀስ እፈልጋለሁ እንደሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢአድ በውጭ የሚገኘው ጎንደር ህብረት ተብየው እና የእነሱ ሚዲያ ኢሳት እና ቪኦኤ) በቅማንት ህዝብ ላይ የሚደርስን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ በደል ዝም ብሎ በማለፍ የሌላውን በደል ብቻ በማራገብ ጎንደርን መቸውንም ሰላም ሊያደርጓት አይችልም፡፡ የቅማንት ህመም፣ ሞት እና መፈናቀል የሌላው ጎንደሬ እና ኢትዮጵያዊ በደል ተደርጎ ካልታየ ጥፋቱ እየሰፋ ሄዶ ነገ ሊመለስ ወደማይችል የህዝብ ለህዝብ ጥላቻ ሊከቱት ይችላሉ የሚል ስጋት አለኝ፡፡
የቅማንትን ህዝብ ያስጨፈጨፉት የጎንደር ህብረት፣ ከኢሳት ጋር እንዲሁም ፅንፈኛ ዳያስፖራዎች ከአንዳንድ የትምህክት የክልሉ አመራር ጋር ሆነው እንደሆነ የቅማንት ህዝብ በግልፅ ያውቃል፡፡ እንደ እነመሳይ መኮንን አይነት የኢሳት ጋዜጠኛ አይነት ግለሰቦች ከድርጊታቸው ካልተቆጠቡ በደም የተሳሰሩ ህዝቦች በጠላትነት የማይተያዩበት ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል ነው እና፡፡
የኢሳቱ መሳይ መኮንን እና ጎንደር ህብረት ተብየው ዘመነ መሳፍንት አራማጁ ድርጅት በቅማንት ህዝብ ላይ ያላቸውን የተዛባ እና የተንሸዋረረ አተያይ ካላስካከሉ በስተቀር የጎንደር ህልውና አደጋ ላይ መጣላቸው አይቀርም፡፡
ጎንደር ህብረት ተብየው እና የኢሳቱ መሳይ መኮንን የቅማንት ህዝብ የራሱ የሆነ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና ኢኮኖሚያዊ እድገት የማይፈልግ ነገር ግን ከኋላ በሚደረግ ውጫዊ ገፊ ሀይል በመገፋት የሚንቀሳቀስ ግዑዝ አካል አድርጎ መመልከት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ለጎንደር እና ለጎንደሬዎች የከፋ ይሆናል፡፡ ለአብነት የአንዱዓለም ተፈራን ጹህፍ በጎንደር ህብረት አማካኝነት (ኢትዮሜዲያ?) ‹‹የማይለቀን የቅማንት ጉዳይ——›› በሚል ርዕስ የፃፈውን እና ሌሎቹን መመልከት ለአባባሌ አብይ መሳያ ነው፡፡ እንዲህ አይነት የወረደ አመለካከት ለቅማንት ህዝብ ይበልጥ ጉለበት ሰጠው እንጅ ከትግሉ ወደኋላ እንዲል አላደረገውም፡፡
የቅማንት ህዝብ የጅምላ የዘር ማጥፋት ከዲያስፖራው በተላከ ገንዘብ አማካኝነት በተገዛ መሳሪያ በ2008 ሲጨፈጨፍ ጎንደር ህብረት እና ኢሳት ግን ጉደዩን የተዛባ ስዕል እንዲይዝ ለማድረግ የራሳቸውን ፕሮፓጋንዳ እንዲህ በማለት ዘገቡ፡፡ ‹‹ወያኔ የጎንደርን መሬት ለመውረር ባለው ግልፅ አጀንዳ የቅማንትን እና የአማራውን ህዝብ ወደ ጦርነት እንዲገባ አደረገ›› ነበር ያሉት፡፡ ሲጀመር ቅማንት እና አማራ እንደህዝብ ጦርነት አላደረጉም፡፡ ሲከተል ደግሞ የጦርነቱ አበጋዞች የክልሉ አንዳንድ አመራሮች እና ትምህክት አስተሳሰብ ያቀንጨራቸው ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡ ምን አልባት ‹‹የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ መነሳት የለበትም›› የሚሉ አካላት ካሉ ለምን የሌሎች ብሔር ብሄረሰቦች የዞን እና የክልል አስተዳደርን ተቃውመው አልተነሱም፡፡ ለምን የቅማንት የራስ አስተዳደር ጎንደር ህብረትን እና የኢሳቱን መሳይ መኮንን አንገበገባቸው? የዚህ ሁሉ የተዛባ አመለካከት ምንጩ በቅማንት ህዝብ ላይ ለዘመናት ጭንቅላታቸውን የሞሉት የወረደ አተያይ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡
የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር በማንም ህዝብ ላይ መብት ላይ ምንም ነገር እንደማያስከትል እያወቁ ጎንደር ህብረት ‹‹ቅማንት አማራ ስለሆነ ራሱን ለማስተዳደር አይችልም›› ብሎ ይሞግታል፡፡ ይሁን እንጅ ጎንደር ህብረት እና ኢሳት ስለወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ላይ ግን ቀን ከሌት በመልፈፍ ያደንቁራሉ፡፡ የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነትን ከደገፉ የቅማንትን ቅማንትነት ለምን መቃወም ፈለጉ? ለዚህ አባባላቸው ምክንያታቸው ግልፅ ስለሆነ ቃሉን መጥቀስ አልፈልግም፡፡ ግን የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ህገ-መንግሥታዊ የመብት ጥያቄ ላይ ጥያቄ ላይ ሥርዓቱን ተከትሎ አስከሄደ ድረስ ተቃውሞ የለኝም፡፡ ግን ይህን ሽፋን በማድረግ በህዝብ እና በየህዝብ ሀብት የሚደረግ ጥፋት አጥብቄ እቃወማለሁ፡፡ የቅማንት የማንነት ጥያቄ አስተባበሪ ኮሚቴዎች ህጋዊ ጥያቄ በማንሳታቸው እንግዛት አብዩ እና ደሴ አሰሜ በጀምላ በዳባት እና በደባርቅ አሰረዋቸዋል፡፡ የቅማንት ህዝብ ግን ወኪሎቹ ታስረውበትም ወደጦርነት ሳይሆን ያመሩት ‹የህግ ያለህ› ነበር ያሉት፡፡ የቅማንት ህዝብ ሌሎች እንዳደረጉት ጎንደርን የማተራመስ አቅም አይደለም ያጣው፤ ጥያቄው ህጋዊ ስለነበር በህግ እና በህግ ብቻ ስለሚተማመን በህግ ተስፋ የማይቆርጥ መሆኑ ብቻ ነው፡፡ የዚህን ህጋዊ አካሄድ ውጤት በቅርቡ አብረን እናየዋለን፡፡ ውሾቹ ይጮሀሉ ግመሉ ግን መንገዱን ቀጥሏል!
ዞሮ ዞሮ የቅማንት እና ሌላው የሰሜን ጎንደር ህዝብ ከአንድ የዘር ሀረግ ስለሚመዘዙ መቸም ሊለያዩ እንደማይችሉ ተገንዝባችሁ እነመሳይ ጉንጭ አልፋ ቱሪናፋችሁን ብታቆሙ መልካም ነው፡፡ የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር እና የማንነት ጥያቄ ሙሉ መብቱ የቅማንት ህዝብ እንጅ የማንም ግፊት እንደሌለበት ልትገነዘቡ እውዳለሁ፡፡ ቅማንትን መቸም ቢሆን ቅማንት ከመሆን የሚያግደው አንዳችም ሀይል እንደሌለ ልትገነዘቡ አወዳለሁ፡፡
ቸር ይግጥመን

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

3 Responses to ጎንደር እና ጎንደሬዎች

 1. Kebede Kassa says:

  Have you forgot it as you are in the 21st century? …… Stupid ….. you will be disappeared. Take care of!!!!!

 2. Bekahegn Anteneh says:

  The stupid is the one who spites stupid words and feeble to dialogue with reasons.

  • The name Begiemendr came from Beja Midir (Agow). There is no question about the historical facts of the past. The problem of the Ethiopian history diverting from the history of Agow. I remember in 1997 the talking about our origin with an old man from Southern Ethiopia that claimed the Amhara speaking people came from Agow. His statement came after I told him that came from Agow background the Zague Dynasty. He was angry that I claimed my decent. he said the Amhara speakers are the only Agow decent.
   God bless the Agow people.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s