አገዉ ሕዝብ ለነጻነትና ለብሔራዊ መብቱ ሊቆም ይገባዋል

ከኃይሉ

እንደሚታወቀዉ በክልል ሥስት ውስጥ 3 ብሔሮች እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡ እነሱም ኦሮሞ፤ ዐማራና ዐገዉ ናቸው፡፡ የኤትዮዽያ ሕገ መንግሥትን በተመለከተ ተቃራኒ አቋም ይንፀባረቃል፡፡ የአገዉ ብሄር የኤትዮዽን ህገ መንግሥት የተቀበለ ቢሆንም አገዎች የሕገ መንግሥቱ ተጠቃሚ አይደሉም፡፡ አገዎች በክልል 3 ውስጥ ተሪት (treat) የሚደረጉት እንደሁለተኛ ዜጋ ነው፡፡ በብአዴን አፈና የተነሣ እስከ ዛሬ ድረስ የራስ የማስተዳደር መብት አላገኙም፡ የቅማንት አከባቢ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አከባቢ ማለት ነው፤ ለልጆቻቸው የሚጠቅምና እድገትን የሚያግዝ የትምህርት ሥርዓት መዘርጋት አልቻሉም፡፡ ለምሳሌ በአዊ ብሔረሰብ ዞን ብአዴን ያስቀመጣቸው ካድሬዎች የብአዴን ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ ያገውን ሕዝብ ጥቅም ለማስከባር የቆሙ እውነተኛ አስተዳደሪዎች አይደሉም፡፡ ለዚህ ነው ሕዝቡ አሽከሮች ብሎ የሚጠራቸው፡፡ በሌላ መልኩ የአማራ ብሔር አባላት አልፎ አልፎ ሕገ መንግሥቱን የመቃወም አዝማሚያ ይታያል፡ ለዚህም ሰሞኑን የተከሰተዉ ሁከት እንደ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል፡ አገዎችና ዐማሮች በሚኖሩበት ዐካባቢ የተፈጠዉ ሁከት ለአካባቢዉ ሕዝቦች ከፍተኛ ጉዻት ማስከተሉ የሚካድ አይደለም፡፡

የሁከቱ መንስዔ ውስብስበ ቢሆንም በቅማንት ሕዝብ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፈና የወልቃይት ጉዳይ አስተዋፆኦ አድርገዋል ማለት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል በምግበረ ብልሹነትና በአገው ሕዝብ ዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠረጠረው በአቶ ገዱ የሚመራው የክልሉ መንግሥት በሁከቱ ላይ እጁን አስገቶበታል፡፡ በብዴን አማካኝንት በሕቡዕ የተደራጀዉና ክልሉን በሰላም ዕጦት የሚአተራምሰዉ ቡድን ግን ህገ መንግሥታዊ ጥያቄዉን ለፓለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ለማዋል መሞከሩ ሥህተት ከመሆኑም በላይ ጥፋት ነዉ ማለት ይቻላል፡፡

በብሔር ብሔረ ሰቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ላይ አሉታዊ ዐቌም ያለዉ ይህ ዘረኛ ቡድን፡ በዚሁ የዐመፅ ሠልፍ ባዐካሄደበት ወቅት በኦሮምያ ክልል የተቃዉሞ ሠልፍ በማካሄድ ላይ እያሉ ህይወታቸዉን ላጡት ወገኖቻችን የተላለፈዉ የሀዘን መልዕት መልካም ሲሆን፣ ነገር በሰሜን ጎንደር በአቶ ገዱ አዝማችነት በግፍ ለተጨፈጨፋት ለአገዉ ቅማንት ሕዝብ ተመሣሣይ መልዕት ዐለመተላለፋ ግን ሁከቱን የሚመራዉ ቡድን በአገዉ ህዝብ ላይ ጥላቻና ንቀት ያለዉ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች የአገዉ ብሔር አባላት በተለይም የአዊ ወጣቶች በሁከቱ በመሳተፋቸው ጥያቄ ማሥነሣቱ አልቀረም፡፡ መልሱ ግልጽ ነው፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት የአዊ ሕዝብ የሕገ መንግሥቱ ተጠቃሚ አልንበረም፡፡ የአገውን ሕዝብ አግልሎ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የፊድራል ሥርዓት በወሊዎች የሚመራው ብአዴን በአገው ሕዝብ ላይ የጭቆና ግፍ እንዲፈጽም ሕጋዊ ሽፋን ሠጧል፡፡ ስለዚህ የአዊ ወጣቶች በአመጹ ላይ ቢሣተፉ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ ዕርግጥ የአዊ ወጣቶች (ሰልፈኞች) ወልቃይት የአማራ ነው አላሉም፡ ይልቅስ የራሳቸውን ጉዳይ አንሥተዋል፡ በተረፈ ሕዋት ሌባ ነው አንገዛም እየሉ ዘፍነዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በክልል ሥስት ህገ መንግሥቱ የሕልዉና ፈተና የገጠመዉ መሆኑን በመገንዘብ የተለየ ጥበቃ ከማድረግ ባሻገር ዕልባት ላላገኙ ጉዳዮችም (የቅማንቶችን የራስ አስዳደር ጭምር) ዕልባት በመስጠት ለበለጠ ተግባራዊነቱ ቁርጠኝነቱን ማሣየት ይጠበቅበታል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ የአገው ሕዝብ የፊድሬሹን አባል እንዲሆንና እራሱን በራሱ የሚስተዳደርበት ሁኔታ በአስቸኳይ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ ይህ ካልሆነ ክልሉ የሰላም ቀጠና ሊሆን አይችልም፡፡

የአገው ሕዝብ ነፃነት የሁሉም ነፃነት ነው
ኢትየጵያ ለዘላዓለም ትኑር

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

One Response to አገዉ ሕዝብ ለነጻነትና ለብሔራዊ መብቱ ሊቆም ይገባዋል

  1. kidus says:

    This is fact on ground. Though legislation grants full right for every nation and nationalities there is no system to check and balance whether it implemented according to legislation or not. Due to this, regions make of many nations like Amhara region got a full chance to trade on the name of nations and to abuse them against constitution. When we see infrastructures development hospital, educational institutions (university, teachers training colleges, ….) and other public institutions are not equally distributed across. The three zones didn’t get equal chance to gain these basic infrastructures. Non-Nationality zones are favored. This is ongoing real discrimination in the region to mention only some. I thank the writer for raising this real fact on the ground.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s