Gedu Andargachew, Front-Runner of Genocide: His Destitute Background and His Loose Link to EPRDF

አቶ ገዱ የናት ጡት ነካሽ!

By Yimer M.

==============================
አቶ ገዱ ትዉልዳቸዉ ሰሜን ወሎ ዋድላ ደላንታ ወረዳ ነዉ፡፡ኢህአዴግ ሃገራችን ሲቆጣጠር እሳቸዉ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነበሩ፡፡እስከ 11ኛ ክፍል ድረስ ሲማሩ እንደማንኛዉም የአርሶ አደር ልጅ ተቸግረዉ እንደተማሩና በወቅቱ እሳቸዉ ካደጉበት አካባቢ የሚኖሩ የጤና ባለሙያወች የደብተርና የእስክርቢቶ እየገፈተሩላቸዉ 11ኛ ክፍል እንደደረሱ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጅ ስርአቱ ሲለወጥ የሳቸዉም ሂወት አብሮ ተለወጠ፡፡ወደ ኢህአዴግ ጠጋ በማለት የክፍለ ህዝብነት ስልጣን ተሰጣቸዉና ት/ም አቋረጡ ይሁን እንጅ ኢህአዴግ ት/ም ያልጭረሱ ካድሬዎቹንና ተዋጊ ጓዶቹን የማስተማር በጎ ፕሮግራም ስለነበረዉ ደሴ ጢጣ በትግሉ ዉስጥ የነበሩ ካድሬዎች ት/ም የሚማሩበት ትምህርት ቤት ትምህርታቸዉን እንዲጨርሱ ተደረገ፡፡
ከዚያም የስልጣን ኮርቻን አንድ ባንድ መቆናጠጥ ቻሉ፡፡
በሰሜን ወሎ ዞን ከተለያዩ የስልጣን እርከኖች እስከ ዞኑ አስተዳዳሪ ከዚያም ወደክልል በመግባት ግብርና ቢሮ ም/ሃላፊ፣የግብርና ቢሮ ሃላፌና ም/ርእሰ መስተዳድር አሁን ደግሞ የክልሉ ፈላጭ ቆራጭ ገዥ፡፡ይህ ሁሉ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪ ሲቪል ሰርቪስ የያዙት እንኳ ባ/ዳር ከገቡ በኋላ ነበር፡፡
ምን ችግር አለ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስልጣን መያዝ ወይም ህዝብን ማስተዳደር የፖለቲካ ወገንተኝነት እንጅ የትምህርትና የእዉቀት ብቃት አይጠይቅም፡፡
እንግዲህ እኝህ ሰዉ ናቸዉ ኢህአዴግ ሃገራችን ሲቆጣጠር ወደድርጅቱ የተቀላቀሉ የድርጅቱ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ ያልገባቸዉ፤ኢህዴን/ኢህአዴግ የብሄር ጭቆናን ለማስወገድ የታገለ መሆኑን ያልተረዱ ትምህርታቸዉን እንኳ ባግባቡ ያልጨረሱ ግለሰብ ከአንዲት የገጠር ቀበሌ መጥተዉ የዲሞክራሲ ስርአት በምታራምድ ሃገር መሪ እንዲሆኑ ኢህአዴግ እድል የሰጣቸዉ፡፡
ይሁን እንጅ እንዲህ አድርጋ ከመሬት አንስታ ዙፋን ላይ ያስቀመጠች ሃገር ዜጎችን ለአንድ ወገን በመወገንና ከሃገራችን ጠላቶች ጋር በመተበባር ዛሬ ኢህአዴግና ኢህዴን ያጸደቁትን ፌዴራላዊ ህገ-መንግስት ለማፍረስንና ሃገራችን ወደቀደመ ፌዉዳላዊ ስርአት ለመመለስ ኢህአዴግን ከዉስጥ ሆነዉ እንደ ግንደ ቆርቁር ወፍ በመፈርፈር እያዳከሙ የሚገኙት፡፡
ኢህአዴግ ከአፈር አንስቶ ዙፋን ላይ ያስቀመጠዉ ግለሰብ በግልጽ ድርጅቱ የታገለለትን የብሄር ብሄረሰቦች መብት ለቅማንት ህዝብ አይገባዉም በማለት በዝንጀሮ ምክር ቤት በማጸደቅ ግልጽ ጦርነት በማወጅ ህዝቡን በጅምላ በተደራጀ ጦር በመታገዝ በመፍጀት ላይ የሚገኘዉ፡፡
ኢህአዴግ ተቀምጦ የሰቀለዉን ገዱን ዛሬ ቆሞ ለማዉረድ ተቸግሮ የቅማንት ህዝብ በግልጽ ይሙት በቃ ተፈርዶበት በከባድ ጦርነት ዉስጥ ይገኛል፡፡
አንድን ህዝብ እንዲያስተዳደር በህዝብ የተመረጠ ሰዉ በመረጠዉ ህዝብ ላይ በይፋ ሰራዊት በማዝመት የዘር ማጥፋት ሲፈጽም ገዱ ባለም ላይ የመጀመሪያዉ ያደርገዋል፡፡
ኢህአዴግ ወደየት እያመራ ነዉ…?…በቅማንት ህዝብ ላይ በክልል 3 ባለስልጣናት እየተከናወነ ያለዉ ዘርን መሰረት ያደረገ ግድያ ወከባ፣አስገድዶ መድፈር፣ሃብት ንብርት ዘረፋ… ማብቂያዉ መቸ ነዉ?
በእዉነት ክልል 3 ዉስጥ እየተከናወነ ያለዉ የቅማንትን ህዝብ በጅምላ የመፍጀት ሂደት ኢህአዴግን አያሳስበዉም? …ኢህአዴግ አሁን በሃገራችን ዉስጥ የብሄር ጭቆናን ታግየ አስወግጃለሁ ለማለት ያስችለዋል? ከአፈር አንስቶ ላያችን ላይ ያስቀመጣቸዉ የናት ጡት ነካሾቹ እነገዱ አንዳርጋቸዉ መቸ ነዉ ኢህአዴግ ከቅማንት ህዝብ ጀርባ ላይ የሚያወርዳቸዉ?
አቶ ገዱ የናት ጡት ነካሹ ሰሜን ወሎ ላይ ከፍተኛ የሆነ ቡድንተኝነት መስርቶ ነዉ ክልል የገባዉ፤ይህን ማድረጉም በስልጣኑ ላይ እረጅም ጌዜ እንዲቆይ ያግዘዋል፡፡የገዱ ቡድንተኝነት ሰሜን ወሎ አያበቃም ሰሜን ጎንደርም ይሻገራል፡፡
ገዱ ለሰሜን ጎንድር አስተዳዳሪነት አቶ ግዛት አብዮን ከቀበሌ ሊቀ መንበርነት በማንሳት ትልቅ ዞን እንዲመራ እድል ሰጠዉ ዉጤቱም የቅማንትን ህዝብ በጅምላ መጨረስ ሆነ፡፡
ግዛት አብየ የገዱ አበልጅ ነዉ፤ይህ ትስስር እንግድህ አትካደኝ አልክድህም መሆኑ ነዉ፡፡ይህን ትልቅ ህዝብና ክልል እንዲመሩ ኢህአዴግ የትምርትም ሆነ ፖለቲካዊ ብስለት የሌላቸዉ ግለሰቦች እድሉን ለምን ሰጣቸዉ፡፡
ኢህአዴግ ክልል 3 ዉስጥ ደካሞችንና ሙሰኞችን ብቻ በመምረጥ የስልጣን እርካብ ላይ የሚሰቅላቸዉ ሚስጥሩ ምን ይሆን?
ይሁና እስቲ…ክልል 3 ዉስጥ ባሁኑ ጊዜ እየደረሰ ያለዉ የዘር ማጥፋትና የሰባዊ መብት እረገጣ…እንዲሁም የሌላዉን ፍለጋ የኢህአዴግን ወንበር ከመሰረቱ ሊያነቃንቀዉ እንደሚችል ምስክር መጥራት አያሻዉም፡፡

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

7 Responses to Gedu Andargachew, Front-Runner of Genocide: His Destitute Background and His Loose Link to EPRDF

 1. Wondmu says:

  Mr. Yimar, thank you for your article. People, like Gedu are desparate for survival are preoccupied for existence and they can kill you. It is not surprising that South Korean psychologists concluded that leaders who led Ethiopia for past 3-centuries back are mentally retarded. The result was destruction and poverty. Semi-retarded personality, like Gedu cannot complete high school and thirsty for power for compensation his impairement.

 2. prince says:

  Hi mr. Wondimu, yes indeed, the so called Ato Gedu’s leadership style is Autocratic in nature. Nonetheless, he is not the only guy for massacre and killing of kemant people, but also the whole ANDM elites. But, don’t hesitate that they will be in front of the court or Join their friends at Ginbot 7

 3. Kumar says:

  Hi all
  Do not think that Gedu and his accomplices are an independent thinkers. They just tried to fulfill EPDRF’s mission to cause conflicts between Kemant and Amahara to make the society too weak to stand against the government. These people are opportunists and they do not want to risk their power. I do not think they have any conflict with EPDRF

 4. Faith Abgail says:

  This Kemant genocide is well planned by EPRDF to dismantle the Amharic speaking people unity. These people are inter-married and used to live in peace as brothers and sisters. Now, fueled by EPRDF propaganda, the uneducated rural savage Amhara people are killing Kemants. So many atrocities are being commited. To me, what is interesting is to see the Amhara people being easily tricked into this savage act just like a backward, uneducated ethnic group in the jungle. They call themselves Christians but what they are doing is outrageous. Any Ethiopian should stand with the Kemant and stop this bloodshed!

 5. NATNAEL DEMILE says:

  YOU ARE STUPID RISE OUT YOUR HAND FROM OUR HERO GEDU.

  • kidus says:

   The problem is not only Gedu’s but also of all ANDM members of Agaws who are selfless (unconfident) due to identity crisis they have experienced for the last 800 years. Thier masters are all the sons of Egypt the owner and fabricators of kibrenigest to claim them selves and Amhara who is well self-denial insulting the roots of their(all Agaws) as faleshas, belabela (metie sikoye tensulgn yilal endil). Any ways Agaws should unite and have to write their true history rather than masking themselves false identity.

 6. kidus says:

  Dear Natnael your hero doesn’t necessarily be for all since it is matter of perspective as devil is god for illuminate.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s