Lack of Professional Ethics in Media (e.g. VOA Amharic Service)

by Britu W
ወገንተኛ ሚዲያ እና የሙያ ሥነ መግባርን የጣሰ ጋዜጠኛ

የአንድ ብዙኃን መገናኛ ለህዝብ የሚያስተላልፈው መረጃ ከሁሉም በፊት እውነተኛ፣ትክክለኛ፣ ከአድሎ የፀዳ፣ ሚዛናዊና እና በእውነተኛ መረጃ የተደገፈ ሊሆን ይገባዋል፡፡ የሚተላለፉ ዜናዎችም በቡድንም ሆነ በግለሰብ እንዲሁም በጎረቤት አገሮች መካከል በማንኛውም መልክ ግጭትንና ጥላቻን የሚያነሳሱ መሆን የለባቸውም፡፡ ምን አልባት ይህን ሥነ-መግባር ከእኔ በተሻለ ባለሙያዎች የሚገነዘቡት ይመስለኛል ፡፡ ይህን ስል ለሙያው ክብር ያላቸውን ማለቴ እንጅ ዘረኞችን አያካትትም፡፡
ይሁንእንጅ የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ክፍል (ምን አልባት በሌሎች ቋንቋዎች የሚተላለፉት ዜናዎች አልሰማቸውም) ብዙውን ጊዜ የጋዜጠኛ ሥነ-መግባርን ባልተከተለ መልክ ለአንድ ወገን ያጋደለ በሚመስል መልኩ ዜናዎችን ሲሰራና የአንድ ወገንን መረጃን በመያዝ ዜናዎቸን ለህዝብ ሲያደርስ ይስተዋላል፡፡
ለዚህ አባባሌ መነሻ የሆነኝ ከባለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በአማራ ክልላዊ መንግሥት የአድማ በታኝ ፖሊስ አማካኝነት በቅማንት ህዝብ ላይ የተፈፀመውን የግፍ ጭፍጨፋ በሁለቱ ውንድማማች ህዝቦች ማለትም በቅማንት እና በአማራ መካከል የተደረገ በዘር ላይ የተመሰረተ ጦርነት አድርጎ ማቅረብ ከአንድ ዲሞክራሲያ ተብላ በምትታይ አገር አሜሪካ ህግ የተቋቋመ የህዝብ መገናኛ ነው ብሎ ማሰብ እጅግ ይቸግራል፡፡ በባለፈው ከጎንደር አቶ ገዳሙ ዳርጌ የሚባሉ ግለሰብ በአቶ አዲሱ አበበ ጎንደር አካባቢ ስለተከሰተው ግጭት ሲጠየቁ የሰጡት መልስ እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ ለዚህ እንደመነሻ መሪ ጥያቄ ያቀረበላቸው ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ ለኝህ ግለሰብ ያቀረበላቸው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፡፡ ‹‹በቅማንትና በአማራ ህዝብ ሰሞኑን ብሄርን መሰረት ያደረገ ግጭት ተነስቷል፤ እውነት ነው?›› የሚል ነበር፡፡ ግለሰቡም ‹‹አወ››ብለው ነው የጀመሩት፡፡ ሲያብራሩም ከጎንደር ከተማ በቅርብ ዕርቀት በምትገኘው ማውራ እና ወራንገብ በሚባል አካባቢ በቅማንትና በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ተከፍቶ ብዙ ሰዎች እንደተጎዱ ጠቅሰዋል፡፡ የሚገርመው ግን በዚህ አካባቢ አንድም አማራ አይኖርም፤በቦታው ሙሉ በሙሉ የሚኖረው የቅማንት ህዝብ ብቻ ነው፡፡
ትክክል ነው፤ በዚህ ቦታ በቅማንት ህዝብ ላይ የአማራ መንግሥት የፖሊስ ወታደሮች አማካኝነት ንጹኃን የቅማንት ልጆችን ጨፍጭፈዋል፡፡ በአልሞት ባይ ተጋዳይነተም ህዝቡ ራሱን ለመከላክ ባደረገው የተኩስ ልውውጥ በከክልሉ ፖሊስ በኩልም ጉዳት ደርሷል፡፡ በሁለቱም ወገን የሞቱት ግለሰቦች ክቡር የሆነውን ህይወታቸውን ያላግባብ ከፍለዋል፡፡ ሁሉም የአንድ እናት ልጆች ናቸው፡፡ በፖሊስ በኩል ተሰልፈው የነበሩ የቅማንት ልጆችም ሞተዋል፡፡
በዚህ ጹህፌ የጭፍጨፋውን መነሻ ምክንያት ለመግለጽ አልሞክርም፡፡ ይሁንእንጅ ይህን ግጭት በሁለቱ ወንድማማች በቅማንትና በአማራ ህዝቦች መካከል የተደረገ አስመስሎ መዘገብ ዓላማውና ከዚህ የሚገኘው ትርፍ ፍፁም አልገባኝም፡፡ በሩዋንዳ የተካሄደውን የሁቱና የቱሲ ህዝቦች እልቂት ከጀርባ ያባብሱ የነበሩ ዘረኛ ሚዲያዎች ነበሩ፡፡ በባለፈው የተላለፈው ዘገባ ከጦርነቱ በእርቀት ቦታ ለሚገኙ ሁለቱ ህዝቦችና ይህን የተዛባ ዘገባ ሲያደምጡ የሚፈጠርባቸው የዕርስ በዕርስ የጥላቻ ስሜት ምን ሊሆን እንደሚችል ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ የሚያጣው አይመስለኝም፡፡
በዚህ ጦርነት ላይ እኮ የፖሊስ አባል የሆኑ የቅማንት ልጆች በመንግሥት በኩል ተሰልፈው ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በተመሳሳይ በቅማንት በኩል የቆሙ የአማራ ተወላጆች በቅማንት ላይ በግፍ የተቃጣውን ጦርነት ለመከላከል ከቅማንት ጎን ሆነው የፖሊስ ሀይልን ተዋግተዋል፡፡ ታዲያ በምን መንገድ ነው ይህ ጦርነት በሁለቱ በአጥንትና በደም በተሳሰሩ የቅማንትና የአማራ ህዝቦች መካከል ነው ተብሎ የሚዘገበው?
እርግጥ ነው አንዳንድ ከወረዳ አስከ ክልል ያሉ ጽንፈኛ የአማራ ክልል አመራሮች በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት ለማስነሳት ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህ ድርጊት ምንጊዜም ከጥንት አስካሁን ህዝብን በተሳሳተ መንገድ በማሰለፍ ህዝብ ለህዝብ እልቂትን ሲፈፅሙ ኑረዋል፡፡ ዛሬም የዚያ የአለፈና ኋላቀር አስተሳሰብ ወራሽ የሆኑ የአማራ አመራሮች አማራን በቅማንት ላይ ለማዝመት ጥረት አድርገዋል፡፡ ሰፊው የአማራ ህዝብ ለውትወታቸው ጆሮ ዳባ ልበስ ቢልም የተወሰኑ ‹‹ጦር ጠማኝ›› ግለሰሰቦቸን ከዚህም ከዚያም በማሰባሰብና በማስታጠቅ በጭልጋና በመተማ ወረዳ በማሰማራት ግጭቱ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የተደረገ ለማስመሰል ሞክረዋል፡፡ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ዓላማቸው ተሳክቶላቸዋል፡፡ ዛሬ በመተማ፣ በቋራና በጭልጋ አካባቢ የሚኖሩ ሁለቱ ህዝቦች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በሸረበው ተንኮል በመጠኑም ቢሆን አልተጠለፉም ማለት ያስቸግራል፡፡ ለዚህ ተጠያቂዎች ደግሞ ከክልሉ ርዕስ-መስተዳድር ጀምሮ በተዋረድ ያሉ ትምህክት የተጠናወታቸውና ህገ-መንግሥቱን የናዱ አመራሮች ብቻ ናቸው፡፡
ይህንም ጦርነት ቢሆን የክልሉ መንግሥት ፐረዚዳንትን አቶ ገዱን ጨምሮ የሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪ አቶ ግዛት አብዩ እንዲሁም አቶ አገኘሁ ተሻገርና ሌሎች የተሳተፉበትና የመሩት ጦርነት ነው፡፡ሁቶዎቸን አናሳ በሆኑት ቱሲዎች የሩዋንዳ ህዝቦች የዘር ዕልቂት ከኋላ የመሩት የመንግሥት አመራሮችና በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የነበረው የህዝብ መገናኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የአማራ ክልል አመራሮችም በቅማንት ህዝብ ላይ ርህራሄ የሌው የዘር ማፅዳት ለማድረግ ለተወሰነ ጦር ጠማኝ የአማራ ተወላጆቸ መሳሪያ በማስታጠቅና ጥይት በማደል ቅማንትን እንዲገድሉ አዘጋጅተዋቸዋል፡፡እነዚህን ግለሰቦች ህግ ቢለቃቸው እንኳ በደሉ ከደረሰባቸው ወገኖች የሚያመልጡ አይመስለኝም፡፡ ልዩነቱ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ አንድ ቀን በሰፈሩት ቁና ልክ ይሰፈርላቸዋል፡፡ ለዚህ አብይ መገለጫ በጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማና በመተማ ወረዳ በሽንፋ ከተማ እስከአፍንጫው የታጠቀ ሀይል ሰላማዊ ሰልፍ ሲካሂድ አንድም የክልል ባለስልጣን ይህን ከኋላ ሆኖ የሚዘውረውን አመራር በህግ ሲጠይቅ እስካሁን ድረስ አልታየም፡፡
ይሁንእንጅ በተቃራኒው የቅማንት ህዝብ የአገሪቱን ህግ መሰረት ባደረገ መልኩ ሰኔ 7/2007 በጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ለጠየቀ ህዝብ ‹‹ለምን የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ አቀረባችሁ›› በማለት በጠራራ ፀሀይ ገበያ ላይ ህዝቦች በግፍ ተገለዋል፡፡ ይህን ያደረገው ‹‹ከህገ-መንግሥቱ በላይ ነኝ›› ብሎ የሚያስበው የሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪ አቶ ግዛት እና ግብር አበሮቹ ናቸው፡፡ ይህን ህገ-መንግሥት የጣሱና በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥይት ተኩሰው የገደሉና ያስገደሉ ግለሰቦች በስልጣን ላይ ተቀምጠው ህጋዊ ጥያቄ የጠየቁ የቅማንት ህዝብ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ግማሾቹ ለእስር ሲዳረጉ ግማሾቹ ደግሞ የግፈኞችን የግፍ ግደያ በመሸሽ ወደጫካ ተሰደው ይገኛሉ፡፡ አስከአሁኗ ሰዓት ድረስ የኮሚቴ አባላት በአስር ቤት ግማሾቹ ከግፈኞች በመሸሽ የሞቀ ቤታቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና ኑሯቸውን በመተው በጫካ ይገኛሉ፡፡ የቅማንት ህዝብና ኮሚቴዎች ይህ ሁሉ የደረሰባቸው ‹‹ህገ-መንግሥቱ ይከበር በማለት እና ከህገ-መንግሥቱ ጎን በመቆማቸው ብቻ ነው፡፡›› የፌደራል ሥርዓቱን በሀይል ለመናድ የሞከሩ ትምህክት አመራሮች ግን አሁንም በሥልጣን ማማ ላይ የዘር መርዛቸውን እየረጩ ይገኛሉ፡፡
ታዲያ አዲሱና ሌሎች የቪኦኤ ጋዜጠኞች በወቅቱ ይህን ግፍ ለምን አልዘገባችሁም? ይህን ጉዳይ አዲስ አበባ እና አሜሪካ ለሚገኙ የቪኦኤ ጋዜጠኞች በተደጋጋሚ ለማሳወቅ ብንሞክርም ዝንብ የሞተ ያክል ከቁም ነገር አልቆጠራችሁትም፡፡ ዛሬ ምን የተለየ ነገር ተገኘና ጦርነቱን በማሳሳት የሁለቱ ህዝቦች ጦርነት ብሎ ለመዘገብ አነሳሳችሁ? እሽ ዘገባውን ዘግቡ ግን ለምን በተሳሳተ መረጃና ከአንድ ወገን በሚመጣ መረጃ ብቻ ተመስርቶ መረጃውን ማዛባት አስፈለገ? የዚህ ድርጊት ትርፍ ህዝብን በተሳሳተ መረጃ ከማጋጨት ባለፈ ምን ያስገኛል?
አንዳንድ የተወናበዱ የዲያስፖራ አባላት እና የጎንደር ህብረት አመራር ነን የሚሉ ግለሰቦች በሚያራግቡት የተዛባ ወሬ እና በጎንደር ክፍለሀገር አንድነት ስም የገንዘብ መዋጮ ሁለቱን ህዝቦች ለማፋጀት የሚያደርጉት ድርጊት ለማንም ግልፅ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ይህን እንደወረደ ወስዶ እውነተኛ መረጃ አድርጎ ለማቅረብ የተሞከረው ሂደት እጅግ ያሳዝናል፡፡
የአማራ ክልል የአድማ በታኝ ፖለሶችን የአርሶ አደር ልብስ በማልበስና ከአንዳንድ ነውጠኛ ግለሰቦች ጋር በመቀላቀል በጭልጋና በመተማ ወረዳ በቅማንት ህዝብ ጦርነት መክፈቱ ግልፅ ነው፡፡ ለዚህ ምስክር የሚሆነው በጦርነት ልውውጥ የተገደሉ ግለሰቦች ኪስ ሲፈተሽ የአማራ ክልል አድማ በታኝ ፖሊስ የሚል መታወቂያ ተገኝቷል፡፡ ታዲያ የአሜሪካ ድምፅ ይህን ነው እንዴ የሁለት ህዝቦች ግጭት የሚለው? ይህ ጦርነት በአንድ በኩል የአማራ መንግሥት ባሰታጠቃቸው ጦረኛ ግለሰቦችና ፖሊስ በሌላ በኩል ደግሞ በቅማንት ህዝብ መካከል የተደረገ ጦርነት ነው፡፡ ይህ ጦርነት በሁለቱ ህዝቦች የተነሳ ጦርነት ቢሆን በአጭር ጊዜ መቆጣጠር ይቻል ነበር? በፍጹም አይቻልም፡፡ ይህ ጦርነት በሁለቱ ህዝቦች መካከል ቢሆን የቅማንት ህዝብ የሆነ ቤትና ንብረትና በግፍ ሲቃጠልና ሲዘረፍ የቅማት ህዝብ ተመሳሳይ ዕርምጃ ለምን አልወሰደም? ምክንያቱ ግልጽ ነው፤ ጦርነቱን በሁለቱ ህዝቦች ለማስመሰል ይሞከር እንጅ በግልፅ ግን የክልሉ መንግሥት ባስታጠቃቸው ወሮበላዎች የተፈጸመ መሆኑ ነው፡፡
ጋዜጠኛ አዲሱ እንድ እውነተኛ መረጃ ልንገርህ፡፡የአማራ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጦርነቱን መርቀውና ባርከው ለማስጀመራቸው ማሳያ ይሆን ዘንድ ግለሰቡ ያሉትን ቃል በቃል ላስቀምጥልህ፡፡ በላይ አርማጭሆ ወረዳ ማውራ በሚባል መንደር የታጠቀ ሀይል ሲያሰማሩ አንዳንድ የቅማንት ግለሰቦች ‹‹እባከዎ ክቡር ፐረዚዳንት ባልታጠቀ አርሶ አደር ላይ ጦር አዝምተው ንፁሀን ዜጎቸን አያስገድሉ›› ተብለው ሲጠየቁ የሰጡት መልስ ‹‹ አስከመቸ ፈርተን ፤ይለይ›› በማለት ነበር ለእነዚህ ሽማግሌዎች የመለሱት፡፡ እንደፎከሩትም ምንም መከላከያ በሌላቸው የቅማንት ህጻናት፣እናቶች፣ ሽማግሌዎቸን አሳርደዋል፡፡
ይህ ድርጊታቸው አይሲስ (ISIS) አንገታቸውን በግፍ ከቀሏቸው ኢትዮጵያዊያን በምን ይለያል? የቅማንት እናቶችና ህጻናት አንገታቸው በመጥረቢያ እና በሳንጃ የግፍ አገዳደል ነበር የተገደሉት፡፡ ቪኦኤ ለምን ይህን መዘገብ ተፀየፈ? በአይሲስ የተገደሉ ኢትዮጵያዊን ቁጥር 20 ብቻ ነበሩ፡፡ለዚህ የአይ ሲ ስ ድርጊትም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጭቱን ለመግለፅና አድራጎቱን ለማውገዝ ሰላማዊ ሰለፍ በመውጣት ግልጧል፡፡ በአማራ መንገሥት ግፈኛ የፖሊስ ሀይል የተገደሉ ቅማንቶች ግን ከመቶ በላይ ናቸው፡፡ የቅማንት ደምና የሌሎች ኢትዮጵያዊን ደም ይለያያል እንዴ አቶ አዲሱ? ነው ወይስ በቅማንት ህዝብ ላይ የሚፈፀም ግፍ በሌላው ህዝብ ላይ ከሚፈፀም ግፍ ያነሰ ነው? ስንት ቅማንት ሲሞትና ሲፈናቀል ነው ለቪኦኤ ዜና ሆኖ የሚቀርበው?
የቪኦኤ ጋዜጠኞች እኮ አንድ የቤት እሳር ተመዘዘ ብለው በሌሎች ህዝቦች የሚፈጸምን በደል ከወር አስከወር የሚያጮሁ ግለሰቦች የተጠራቀሙበት ነው፡፡ የቅርብ አብነት ላስቀምጥ፡፡ በጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማ በገበያ ላይ በህዝብ ላይ የጅምላ ግድያ ከተፈፀመ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምእራብ ሸዋ በናኖ ወረዳ (ቀበሌ?) አካባቢ በሚኖሩ 85 የአማራ ግለሰቦች ላይ መፈናቀል ደረሰ፣ አንድ ሰው ሞተ ብሎ ከወር አስከ ወር የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል፡፡ ይህም አይዘገብ አይደለም የእኔ አቋም ፡፡ሚዲያው ሁሉንም በእኩል አይን ሊመለከት ይገባል ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ አዲሱ ክርስትና ዘርን፣ ቀለምን ፣ቋንቋን ወይም ሌላ ነገርን መሰረት በማድረግ መድሎ አይፈፅምም፡፡ ነው ወይስ ‹‹ክርስቶስ ለሥጋው አደላ›› የሚለውን ቃል መዘህ አንተም ተገኘሁበት የምትለው ሥጋ ተጭኖህ ይሆን ይህን የተዛባ መረጃ ለመዘገብ የተነሳሳኸው? የቅማንት በደል በሰው ልጆች የተፈጸመ በደል አይደልም እንዴ? ቢያንስ ሰው በመሆንህ በቅማንት ህዝብ ላይ የደረሰውን በደል በሰውነትህ ብትዘግብ ለሥጋህም ለህሊህም ምቾትን ይሰጥሀል፡፡
ለማጠቃለል ያክል ቪኦኤ ትክክለኛ የህዝብ መገኛ ከሆነ በቅማንት ህዝብ ላይ የደረሰውን የዘር ማጥፋት ሙከራ በቦታው በመገኘት እውነቱን ለዓለም ማህበረሰብ ሊያሳውቅ ይገባ ነበር፡፡ ከዚያ ውጭ ግን ማንነታቸውን የካዱ በአሜሪካ አገር የሚገኙ ቅማንቶቸን እና የጎንደር ህብረት አመራር ነን ባዮቸን፤ ማንነታቸውን በመካድ የሚጣልላቸውን ፍርፋሪ የሚለቅሙ የቅማንት ተወላጆቸን በሚዲያ በማቅረብ የቅማንትን ትክክለኛ የመብት ጥያቄ ለማዛባት መሞከር እንደማይቻል በመገነዘብ ወደ ትክክለኛ የጋዜጠኛነት ሙያ መመለሱና ትክክለኛውን ማቅረብ ለሁሉም መልካም ይመስለኛል፡፡ ካልሆነ ግን የምትዘግቡት የተዛባ ዘገባ ከእሳት ላይ ቤንዚን ይጨምር ካልሆነ በስተቀር የቅማንትን የመብት ጥያቄ በማንኛውም መንገድ የምታስቆሙት አይመስለኝም፡፡
በቅማንት ህዝብ ላይ የተካሄደውን ጦርነት የመራውና ያካሄደው የአማራ ክልል መንግሥትና የተዋጉትም የአማራ ክልል የፖሊስ ወታደሮች እና ድሮም በቅማንት ህዝብ ላይ የተንሸዋረረ አመለካከት ያላቸው ጥቂት ግለሰቦች እንጅ በሰፊው የቅማንት እና የአማራ ህዝብ መካከል የተደረገ ግጭት አለመሆኑን ተገንዝባችሁ የሁለቱን ወገኖችን ሀሳብ በሚዲያ ለማቅረብ ብትሞክሩ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ይህን ባታደርጉ ግን ከጦረኛው የአማራ ክልል መንግሥት ጋር በመሰለፍ በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ግልጽ ጦርነት እንዳወጃችሁ ይቆጠራል፡፡ ዋሽንግተን እና አዲስ አበባ ላይ ተወሽቆ ተባራሪ ወሬ በመለቃቀም ዘገባ ከማስተላለፍ ይልቅ እንደ እውነተኛ ጋዜጠኞች ድርጊቱ በተፈፀመበት ቦታና በደሉ ደርሶብኛል የሚሉትን የማህብረሰብ ክፍል በማነጋገር እውነቱ መዘገቡ ለእናንተ ሙያ መሻሻልም ስለሚያግዝ ይህን አድርጉ፡፡ ካልቻላችሁ ደግሞ ዝም ብሉ፡፡
በተለይ ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ በተደጋጋሚ የምታስተላልፋቸው ዘገባዎች ያንተን የግል ስሜት የተጫናቸው ግለሰቦችን እየመረጥክ የምትዘግበው ተራ ዘገባ እንዳንተ ካለ ለረዥም ጊዜ በጋዜጠኝነት ሙያ ያሳለፈ እና ‹ክርስቲያን ነኝ› ከሚል ግለሰብ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ክርስትናህን በስም ሳይሆን በመግባር ለመግለፅ ሞክር፡፡ ሰው መሆንከን በእርግጥ አልዘነጋሁም እንደአምላክ ትክክለኛ ፍርድ እና ስራ ባይጠበቅብህም ቢያንስ ወደእውነቱ ለማቅረብ ሞክር፡፡ አንተ ብዙውን ጊዜ የምትዘግባቸው ዘገባዎች ለአንድ ወገን ያጋደሉ፣ በውስጥህ አምቀህ የያዝከውን ድብቅ ዓላማ የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡ ይህ ድርጊትሀ አንተን ለትዝብት ይዳርጉህ ካልሆነ በስተቀር እውነታውን ፍፁም መሸፈን ከቶም አትችልም፡፡

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

3 Responses to Lack of Professional Ethics in Media (e.g. VOA Amharic Service)

 1. To: Tilahun says:

  Mr. Tilahun Jember:
  Your article very good. Please translate it into English so that a majority of wlka visitors and audience can read your article.
  from Admin

 2. Musie Abraham says:

  From peaceful to forceful assimilation in so called Amhara region:

  Agews are living in different provinces of Ethiopia, provinces such as Gonder Weleo and Gojam. The mentioned provinces are considered as Amahara region regardless of the other nationalities living in these areas. The mentioned provinces also currently have the given name of the Amhara Regional State. It is a fact that the existence of a considerable number of Agew in this state is not mentioned. However currently Agews are experiencing an organised campaign in Ethiopia by regional state authorities and chauvinist controlled media in abroad. This is due to Agews in this area claiming identity recognition and self-rule. The agew people have been and are still living in harmony with all Ethiopia cultural groups for a long time. They also are sacrifice their own identity to please others and to live in peace. These people are not considered, by some ethnocentric individuals, to have the right to live in their land which was possessed by their ancestors. Agew people also chose hiding themselves under false identities to avoid prejudice and unfair treatment.

  Nowadays, the Kemant community have organised themselves under Kemant identity recognition and self-rule committee to restore their identity in line with the Ethiopian constitution. The Ethiopian constitution allows self-determination for cultural groups. Agew people previously were victims of systematic assimilation. Agew people are currently experiencing an extraordinary forceful assimilation and eviction by Amhara regional state cadre and supported by some chauvinist organisation.
  The Amhara regional state authority is committing genocide by killing vulnerable Kemant children and women indiscriminately and burning houses. This barbaric act is supported by some jingoistic organisation and media based in abroad. The intention of cover up the crime committed by ANDM cadre is to encourage the regional Government to terrorise innocent people to stop identity recognition and self-rule claim. On the other hand broadcasting incorrect information is to keep the barbaric crime secret which is committed by Amhara regional state. Blocking the kemant voice from reaching to Ethiopian people and international community is to isolate kemant community from international community.
  It is important that referring the news broadcasted by Mesay Kebede and Fasil Yenealemu on Kemant issue in different occasions on ESAT. The Kemant people obtaining weapons from the Tigray Regional Government and receiving refuge from this same body Government are the major reasons to make this comment on credibility of the foreign-based media. At the same time Mesay had also promised to his audience to prove to the news broadcasted by himself over kemant obtaining weapons and other facilitation support from Tigray Regional Government. Mesay’s media deliberately broadcasting misleading information to their supporters. The act of the regional government is against the Ethiopian constitution. The Kemant struggle is to restore their identity and human dignity to be equal with other Ethiopian cultural groups. Kemants are not going against the interests of fellow Ethiopians, but the media based Abroad and the authority of the Amahara Regional State are working together day and night to make the Kemant silent and to stop their struggle.

 3. Pingback: ከሙያ ይልቅ ዘረኝነትን ሰባኪዉ ጋዜጠኛ – GondarToday ጎንደር ዛሬ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s