Drama of 42-Kebele Administration: in Violation of Resolution by House of Federation

by Tilahun Jember

አላስፈላጊ ትችቶች፣ የቅማንት አሻንጉሊት ልዩ ወረዳ ምስረታ ሲከሽፍ እና በጠባብ አዕምሮ ሰፊ ክልል መምራት አይቻልም!

እንዴት ሰነበታቹህ፡ እኔ ሰሞኑን የበኩሌን ፅሑፍ ባላስበብብም ብዙዎች እህቶቻችንና ወንድሞቻችን የምትለቁትን ፅሁፍ እያነበበብኩ ነኝ፡፡ በጣም ማመስገን እወዳለው፡፡ ከዚህ በመቀጠል እንደ አርዕስት በተጠቀምኩት “አላስፈላጊ ትችቶች፣ የቅማንት አሻንጉሊት ልዩ ወረዳ ምስረታ እና በጠባብ አዕምሮ ሰፊ ክልል መምራት አይቻልም” በሚሉት ሐሳቦች ዙሪያ አጭር መግለጫ መስጠት እፈልጋለው፡፡
አላስፈላጊ ትችቶች፡- አላስፈላጊ ትችቶች በስሜት ስንገልፃቸው ከውስጣችን ሲወጡ ደስ እያሉን በሌሎች አይን ሲታዩ ግን ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዘናል፡፡ እነዚህ ትችቶች ከዋናው መሰረታዊ ጉዳይ በማስወጣት ወደ ማንፈልገው አቲካራ ውስጥ ያስገባናል፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን ወደ ማያስፈልግ ቁርሾ ውስጥ ያስገባናል፡፡ አንዳንድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ስለ ቅማንት ማንነት እየታገሉ ስለ አማራ ማንነት በማያገባቸው እየገቡ ይዘበዝባሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ሰዎች በክርክርና በስድብ ጊዜያቸውን ያጠፋሉ፤ ከመዋደድና ከጓደኝነት ይልቅ ወደ ባላጣነት ይሔዳሉ፡፡ ከዚህ ምን ትርፍ ተገኘ? መንሳችን ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ ነው፡፡ ስለዚህ ለምን በማይጠቅመን ነገር ጊዜያችንን እናጠፋለን? ከዛ ባለፈ ሳንሳዊ ምርምር ከሆነ ስርዓቱን በጠበቀ እንደ እነ ፕሮፌሰር መስፍንና ሌሎች በመፅሀፍ አስደግፋቹህ አስነብቡን፡፡ ከዛ ውጭ ግን የቅማንትን ጥያቄ አጋዥ በሆኑ የውይይት ፔጆች በመፃፍ አታጨቃጭቁን፣ ጊዚያችንን አታባክኑብን ወደ አላስፈላጊ አቲካራም አታስገቡን፡፡
ሌላው ዋናው ጉዳይ አላስፈላጊ ትችቶችን አስመልክቶ አስተያየት መስጠት የፈለኩት ምክንያት አዛኩና አደራ ሰሞኑን ባስነበበችን/ባስነበበን ፅሑፍ ላይ ነው፡፡ አንዛኩና በጣም ደስ የሚሉ ሐሳቦችንና ሐቆችን በማምጣት ለትግሉ አጋዝ የሆኑ ቁም ነገሮችን አስጨብጦናል/አስጨብጣናለች፡፡ አብዛኛው ፅሑፍም ስድብ የሌለበትና ጥሩ ስነ-መግባርን የተላበሱ ናቸው፡፡ በዚህ ልናደንቅና ልናመሰግን ይገባናል፡፡ ከሰሞኑ ፅሑፍ ያየውት ችግር ግን 42 ቀበሌዎችን አስመልክቶ በቀረበው ፅሑፍ ላይ አንድ የኮሚቴያችን አባልን ይነቅፋል፡፡ አቶ ተስፋሁን የቅማንት ጥያቄ መሳካት የማይፈልጉ አመራሮችን ተልዕኮ በመቀበል 42 ቀበሌዎች በልዩ ወረዳ እንዲዋቀሩ ግፊት ያደርጋል ተብሎ ቀርቧል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ አቶ ተስፋሁን (የአባቱ ስም ስላልተጠቀሰ ሰውየውን ማወቅ ያልቻልን ቢሆንም) ጥያቄው በጥሩ ሁኔታ እንዳይሳካ ጥረት የሚያደርጉ ትምክተኛ አመራሮችን ሐሳብ ተቀብሎ ጉዳይ ፈፃሚና አስፈፃሚ ሆኗል ወይ? 42 ቀበሌዎች ተዋቅረው ሌሎች ቀሪ ቀበሌዎች በሒደት ይካተታሉ የሚል የግል አመለካከት እንዳለውስ በምን እናውቃለን? እነዚህን ጥያቄዎች በአግባቡ መረዳትና ትክክለኛ መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ማንኛውም ሰው ከአዕምሮው የመጣለትን ሐሳብ በነፃነት የመግለፅ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ የሐሳብ ልዩነቶች በሚኖሩ ጊዜ በመወያያ መድረኮች ላይ በመከራከርና በመወያየት ወደ አንድነት መምጣት የሚቻልበት መንገድ በጣም ክፍት ነው፡፡ በመድረክ ውይይት ወደ አንድ የማይመጣ ልዩ አቋም ከሆነ በግል ግለሰቦችን የማሳመን ስራ መስራት ይጠበቃል፡፡ በግል ተመክረው ለድርጅቱ የማይጠቅምና የማይስተካከሉ ሆኖ ከተገኘ ድርጅቱ የራሱን አስተዳደራዊ እንምጃ የመውሰድ መብት አለው፡፡ እንዚህ ሁሉ ነገሮች ሳይታዩ ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ ታጋዮችን ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ ማብጠልጠል ፍፁም ስህተት ነው፡፡ አቶ ተስፋሁንን ጨምሮ ሁሉም የቅማንት አስተባባሪ ኮሚቴዎች በመድረክ ውይይትና ክርክር ያምናሉ፡፡ በመረጃ ላይ የተመሰረተና ገዥ ሐሳብ ያመጡት ኮሚቴዎች ሐሳብ ተቀባይነት አግንቶ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ይህ ጠንካራ አሰራር ለዚህ ደረጃ ያበቃን መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ጥያቄው ሲጀመር አንዳንዶች ማንነት እንጅ የራስ አስተዳደር አያስፈልግም ሌሎች ደግሞ የማንነት ጥያቄ ማንሳት አያስፈልግም የራስ አስተዳደር ጥያቄ ብቻ ነው መቅረብ ያለበት ብለው ይከራከሩ ነበር፡፡ ይህ የአስተሳሰብ ልዩነት ነው ሊወገዝ አይችልም፡፡ ነገር ግን ህዝቡ ማንነቱ ስላልተከበረና ራሱን የማስተዳደር መብት ተነፍጎት ስለቆየ ሁለቱንም ጉዳዩች በመጠየቅ ከፍተኛ የህዝብ ትግል ተካሂዶበት ምላሽ አግንቷል፡፡ አሁን ደግሞ 42 ቀበሌ ይዋቀርና ሌሎች ቀበሌዎች በሂደት ይካተታሉ ተብሎ ሐሳብ ቢቀርብ አይገርምም፡፡ ሰዎችም ሊወቀሱ አይገባም፡፡ በዚህ ወቅት ያለማጋነን 95% በላይ የሚሆነው የቅማንት ብሔረሰብ ተወላጅ በ42 ቀበሌ አሻንጉሊታዊ ልዩ ወረዳ አስተዳደር እንዲመሰረት አይፈልግም፡፡ ስለዚህ የ42 ቀበሌ መዋቅር ሐሳቡ ቢመጣም ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ሰዎችን ያለ መረጃ ለምን አንወቅሳቸዋለን፡፡ ለምንስ ያለ አግባብ ለጠላት ራሳችን በር እንከፍታለን? አቶ ተስፋሁን የቅማንት ጥያቄ ከተጠነሰሰበት ወቅት ጀምሮ ለዚህ ድል እስከበቃነበት ሰዓት ድረስ በየሔደበት በአቋም ተከራክሮ አሳምኖ የሚመጣ ምርጥ ታጋያችን እንደሆነ ሁላችንም ልናውቀው የሚገባ ሐቅ ነው፡፡ ስለዚህ አዛኩና ለዚህ ስህተት ይቅርታ እንደምትይ/እንደምትል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ከዚህ በመለስ ስለጥያቄው አፈታት ሒደትና የሚጠብቁብንን ትግሎችና የምናስመዘግበውን አመርቂ ድል እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራለው፡፡
የክልሉ ም/ቤት መጋቢት 2 ቀን 2007 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፎ ሐምሌ 04/2007 ዓ.ም ያፀደቀው 42 ቀበሌዎችን በአንድ ልዩ ወረዳ ማቋቋም የሚለው ሴራ በህዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለገጠመው ወደ ትግበራ ይገባል ተብሎ አይታሰብም፡፡
የ42 ቀበሌዎች ውሳኔ ሲተላለፍ በወገራ ወረዳ የሚገኙት ኮሶየ አምባራስ፣ ጉንዳ ጩጊ፣ ከልተው እና አዲስጌ አርባጫን ቀበሌዎች እንዲሁም በጎንደር ከተማ የሚገኙት አባእንጦኒዎስ፣ አንቸው ሚካኤል፤ ሰቢያ ሳይና እና ድባ ደፈጫ ቀበሌዎች እንደ አርባ ሁለቱ ቀበሌዎች የመንግስት ካቢኔዎች ተመድበው ሁሉም ተግባራት ያለቀለትና በቀበሌው ህዝብና በቀበሌው ም/ቤት የፀደቀ ስለነበረ በዛው ዕለት/መጋቢት 02 ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ነገር ግን አስተዳደሩ ተለጥጦ ወደ ዞን ያድጋል በሚል ስጋት በሞሽኑ ቀርበው ውሳኔ እንዳይተላለፍባቸው ተደርጓል፡፡ ይህ እንግዲህ አገርን ከሚመራ አመራር የማይጠበቅ ርካሽ የሆነ የበሸቀጠና የገማ ተራ አስተሳሰብ ነው፡፡ አንዳንድ አመራሮች የአመራርነት ሚናቸውን መወጣት ሲያቅታቸው በተራ ተንኮል ይጠመዳሉ፡፡ ከመንግስትነት ተራ ወርደው በተዋረዱና ጥቅም በሌላቸው ተንኮሎች ይተበተባሉ የተበተቡት ተራ ተንኮልም በመጨረሻ ራሳቸውን ጠልፎ ይጥላቸዋል፡፡ በህዝብና በመንግሰት ዘንድም ተቀባይነትና ክብር ያጣሉ፡፡ ምክንያቱም አስተሳሰባቸው ትንሽ ነው፡፡
ይህን ከመንግስት አመራሮች የማይጠበቅ አይን ያወጣ ቅጥፍና የቅማንት ህዝብ እያወቀ የሚቀበል ከሆነ የሰሜን ጎንደር ዞን እና የክልል 3 ውስን አመራሮች ሊቀብሩት ሲነሱ በፈቃደኝነት ወደ ግባተ መሬት እንደመግባት ይቆጠራል፡፡ ከማንኛውም ቦታ በተለየ ሁኔታ ቅማንት ከሚኖርባቸው ቦታዎች በግምባር ቀደምትነት የሚታወቁት ታሪካዊ ቦታዎች አይከልና ከርካር ሲሆኑ በነዚህ አመራሮች አስተሳሰብ አይከል በቅማንት ስር አትገባም፡፡ ቅማንት አይከልን ተነጥቋል፡፡ ምክንያቱም አይከል ከአካባቢው ካሉ ከተሞች በእድገት የተሸለችና ለኑሮ አመች ከመሆኗ በተጨማሪ ውስን አማራዎች(እነ አማረ ሰጤ፣ አገኘው ተሻገር፣ ደሴ/የቤሩት ሆቴል ባለቤት እና ሌሎች/ የአለፋ ጣቁሳ፣ የቋራና መተማ ቀጠና የግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር/የአማራ ተወላጆች ህብረት ማደራጃና ማዣ ጣቢያ ስለሆነች ለቅማንት አትገባም፡፡ ከርከር እንደ አይከል ከተማ ስላላደገች ከ42 ቀበሌዎች መካከል አንዱ ሆና ተካታለች፡፡ እነዚህን ቦታዎች ለአብነት ያህል ልጥቀሳቸው እንጅ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ቀበሌዎች፣ የደምቢያ ወረዳ ቀበሌዎች፣ በርካታ የጭልጋ ቀበሌዎች፣ የመተማና የቋራ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ አልተካተቱም፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ነው እንግዲህ የቅማንት የራስ አስተዳደር ከሐምሌ 01/2007 ዓ.ም ጀምሮ በጀት ተመድቦለት በወረዳ ደረዳ መተዳደር ይጀምራል የተባለው፡፡ የዚህ ተግባር ዋና ቀያሾች ደግሞ ከሰሜን ጎንደር ዞን አቶ አማረ ሰጤ እና ግዛት አበዩ ሲሆኑ በክልል ደረጃ ደግሞ አቶ አገኘው ተሸገርና መርሐፅድቅ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ዋናዎቹ ይሁኑ እንጂ ብዙ የደመነ ነፍስ ደጋፊ አላቸው፡፡ ደመነ ነፍሶች ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት ስለቀረበላቸው ብቻ ይቀበላሉ፡፡ የቅማንት ህዝብ ጥያቄ በትክክል ከመመለስ ይልቅ ሊጎዳ የሚችልበትን የውሳኔ ሐሳብ ይዘው ሲቀርቡ በርካታ የም/ቤት አባላት የተሳሳተ መሆኑን አጥብቀው የተከራከሩና ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም በም/ቤት አባላት የተጠየቁትን ጥያቄዎችን ሳይመልሱና በቂ ውይይት ሳይደረግበት በም/ቤቱ አብላጫ ድምፅ ተደግፏል በማለት ተዘጋ፡፡ ሐምሌ 04 ቀን 2007 ዓ.ም በአዋጅ እንዲፀድቅ የቀረበው የቅማንት የራስ አስተዳደር ጉዳይ በአብላጫ ድምፅ መወሰኑ በጣም አስገራሚ ጉዳይ ነው፡፡ 42 ቀበሌዎችን አካቶ በአንድ ልዩ ወረዳ እንዲቋቋም የቀረበው የቅማንት የራስ አስተዳደር የማቋቋሚያ አዋጅ በበርካታ የም/ቤት አባላት ተቃውሞ ገጥሞት ምንም ድጋፍ ሳያገኝ መጨረሻ በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ፡፡ በርካታ ተቋውሞ ገጥሞት የድጋፍ ሐሳብ ሳይሰጥ ለምን በአብላጫ ድምፅ ተወሰነ? ይህ ጥያቄ በሁሉም ሰዎች አዕምሮ መመላለስ ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ ቅማንት ብቻ ሳይሆን አማራውስ ምን አይነት ሰዎችን ወክሎ ነው እየተመራ ያለው? ጥያቄ ቀርቦለት ጥያቄ ሳይመልስ ተቀዋውሞ ቀርቦበት ተቋውሞውን በተሻለ ሐሳብና ተጨባጭ ምክንያት ሳያሳምን ለምን በአብላጫ ድምፅ ወስኖ ያልፋል? ይህ ጥያቄ ለቅማንት ህዝብ ብቻ ሳይሆን ይህ ትውልድ ሊመልሰው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ‹‹ወደ የት እየሔድን ነው?›› ልንል ይገባናል፡፡
ከላይ የቀረበው የቅማንት ማዳካሚያ የተንኮል ሰነድ ወደ ተግባር ሳይለወጥ ወደ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ አንዲገባ ለማድረግ የተለመደውን ትግል ማካሔድ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የሚደረገው ትግል የቅማንትን ጥያቄ እንዳያይሸራረፍ ብቻ ሳይሆን የተከበረው የፌዴሬሽ ም/ቤት በቅማንት ጥያቄ ላይ ያስተላለፈው የመጨረሻ ውሳኔ እንዲተገበርና የአገራችን ህገ-መንግስት በትክክል እንዲተገበርም ጭምር ነው፡፡ ከላይ መንግስት ውሳኔ ሲያስተላልፍ የታችኛው ኪራይ አስብሳቢ የመንግስት አካል ላለማስተግበር ሲሞክር በህዝቡ ዘንድ ተቋውሞ ሲገጥመው በትክክል ይተገበራል፡፡ በአንድ ወቅት የድሮው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ለህዝቡ ያስተላለፉትን መልዕክት ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ብልሹ አስራርን ለማስወገድ ብልሹ አስራርን የሚከተሉ አመራችን ከታች ህዝቡ ከላይ መንግስት በመሆን ሳንዲዊች እናድርጋቸው ነው ያሉት፡፡ ይህ ንግግር በጣም መሰረታዊና ዘመናትን ተሸጋሪ ነው፡፡ ከላይ መንግስት የፈለገውን ያህል ትክክለኛ ፖሊሲና መመሪያ ቢወርድም ከታች የማይፈፀም ከሆነ ዋጋ የለውም፡፡ ለማስፈፀም ደግሞ የበታቹ የመንግሰት መዋቅር የማያስፈፅም ከሆነ የህዝቡ ትብብር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የቅማንትን ጉዳይ ስናይ በክልሉ መንግሰት በትክክል መወሰን ስላልቻለ ለፌዴሬሽን ይግባኝ ቀርቦ ስለነበር የተከበረው ፌዴሬሽን ም/ቤት ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም በቀረበለት ይግባኝ መሰረት ሁሉንም ቀበሌዎች ባካተተ መልኩ ጥያቄው እንዲፈፀም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ይህንን ተከትሎ የክልሉ ም/ቤት ‹‹የግላችንን ውሳኔ እንናስተላለፍ›› እያለ የፌደራሉን ውሳኔ ከመጻረር ይልቅ የተወሰነውን ውሳኔ ይዞ ማስፈፀም ብቻ ነው የሚጠበቅበት፡፡ የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ ክልሉ መመለስ አቅቶት በይግባኝ ቀርቦ ፌደራል ከወሰነ በኋላ በሰው ውሳኔ ጣልቃ መግባት አያስፈልግም፡፡ የበላይን ውሳኔ መቀበል ደግሞ ብስለት እንጂ ሽንፈት አይደለም፡፡ እንደዚህ ያለ የፌደራልን ውሳኔ በታችኛው አካል አልፈፀም ሲል ወይም በታችኛው አካል የበላይ ህግ ሲጣስ/Anarchism ሲፈጠር ከታች የህዝቡ እገዛ ያስፈልጋል፡፡ መንግሰትም የራሱን መስመር እንደሚፈትሽ ጥርጥር የለውም፡፡ መንግስት የሚያደርገው የራሱ ትግል እንዳለ ሆኖ ህዝቡ የራስን ጥቅም በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ለማስጠበቅ ትግል ማካሔድ ግዴታ ሆኖበታል፡፡ ይህ የትውልድ ጥያቄና አሁን ያለው ትውልድ የማስፈፀም ግዴታ ስላለበት ካሁን በፊት ከተካሔዱት ሰላማዊ ትግሎች በተሸለ ደረጃ የተደራጀ ትግል ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ከአዋቂ እስከ ህፃን፤ ከሙህር እስከ አርሶ አደሩና የቀን ሰራተኛው፤ ከወታደር እስከ ተማሪውና የሐይማኖት አባቶችና ተቋማት፣ የግልና በአካባቢያችን የሚገኙ የመንግሰት ተቋማት የተደራጀ ትግል ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የተደራጀ ሰላማዊ ትግል በማድረግ የቅማንት ህዝብ በቂ ተሞክሮ አለው አሁን ማድረግ የሚጠበቅብን በአደረጃጀትና በስፋት የሻለ ማድረግ፡፡ ይህን ስናደርግ ከክልል እስከ ዞን በመደራጀት ተራ ተንኮል ብቻ የሚጎነጉነውን ትምክተኛ እራቁቱን እናስቀረዋለን፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ተቋማትና የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ተደራጀ ሰላማዊ አመፅ ሲገቡ የፌደራሉን መንግስት ውሳኔ የሚጻረረው፣ ሰውን በገበያ ላይ የሚጨፈጭፈው ትምክተኛ፣ ህገ መንግሰትታዊ ጥያቄን ያነሳ የህዝብ ተወካይ ኮሚቴን የሚያስርና ከቦታ ቦታ የሚበታትንን የለየለት ትምክተኛ ብቻውን እንዲያወራ እናደርገዋለን፡፡ እነዚህ ትምክተኞች ችግር መፍጠርና መግደል እንጂ ህዝብ ሊስመራ የሚችል እውቀትና ቁመና የሌላቸው መሆናቸውን በደንብ እናሳያቸዋለን፡፡ ያን ጊዜ ጥያቄው ሳይውል ሳያድር ይመለሳል፡፡

በጠባብ አዕምሮ ሰፊ ክልል መምራት አይቻልም(የግሌ አስተያየት)

ትምክት ባጠበበው አዕምሮ እንዴት ሰፊ ክልልና ህዝብ መምራት ይቻላል? ከክልል እስከ ዞን ያሉ አመራሮቻችን አንዲት አስቂኝ ንግግር ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ ‹‹አንድም አማራ ቢሆን እንዲቀየመን አንፈልግም›› የሚሏት፡፡ የአማራ ህዝብ ቅማንትን በማፈን እና መብቱን በመንጠቅ ደስ ይለዋልን? የአማራ ህዝብ ለብዙ ዘመናት አብሮት የኖረው የቅማንት ህዝብ ገበያ ላይ በጥይት ሲጨፈጨፍ ደስ ይለዋልን? የአማራ ህዝብ አብሮት የኖረው የቅማንት ወገኑ መኖሪያ አጥቶ ከስራው እየተፈናቀለ ሲሳደድ ማየት ደስ ይለዋልን? እንግዲህ እነዚህ አሳፋሪ አመራሮች ናቸው አንድም አማራ እንዲቀየመን አንፈልግም የሚሉት፡፡ እነዚህ አመራሮች ለአማራ ህዝብ ለትውልድ የሚቆይ ቁርሾ ከማስተላለፍ ባለፈ ምን ፈይደውለታል? አይዞህ አብሮህ የኖረ ጎረቤትክን እየገደልነልህ ነው ደስ ይበልህ እያሉ እያስደሰቱና ስለመረጣቸው ወረታ እየሰሩ እያለፉ ነው እንድትቀየመን አንፈልግም የሚሉት፡፡ የአማራን ህዝብ ልማት በማልማት ከድህነት አለቃችሁት? ወይስ የአማራ ህዝብ ልማት ስታመጡለት ይቀየማቹሀል? ሌላውን ልተወውና አቶ ግዛት አብዩ በሰሜን ጎንደር ዋና አስተዳደሪነትህ ለሰሜን ጎንደር ዞን በተለይም በተደጋጋሚ በድርቅ ለሚጎዳው ተወልደህ ላደግክበት የበለሳ ህዝብ ምን ልማት አመጣህለት? ምን ያህን ወንዞችን ጠልፈህ አዝዕርት አስመረትክ? ህብረተሰቡን ምን ያህል ሊለውጥ የሚችል ትምህርት አስተማርከው? ወይስ ወደሐ ክር ወይም ስንዴ ትንሽ ጥሬ በጣሳ በእርዳታ መልክ መቸርቸር ዘላቂ መፍትሔ ነው ብለህ ወሰድከው? የምትቸረችረው የእርዳታ ጥሬስ ምን ያህል ከሙስና የፀዳ ነው? እንግዲህ እናንተ ናቹህ አንድም አማራ እንዲቀየማቹህ የማትፈልጉ ምርጥ አመራሮች የምትባሉት፡፡
የአማራ ህዝብ የራሱን መብት የሚስከብርለት እንጂ የሌሎችን መብት በመደፍቅ መጥፎ ቁርሾ ለመጭው ትውልድ የሚያስተላልፍለት አመራር አይፈልግም፡፡ እናንተ አመራር ነን ብላቹህ ራሳቹህን የቆላላቹህ አንዳንድ ትምክተኞች ግን ለህዝቡ ጥሩ ነገር ከማምጣት ይልቅ ስልጣናቹህን መከታ በማድረግ ችግር ነው የምትፈጥሩ፡፡ ጅል አመራር ስለትርፍ ሳይሆን ስለኪሳራ ነው የሚያስበው፡፡ ከፍተኛ ኪሳራ በህዝቡ ሲከሰት ከፍተኛ ድል እንዳስመዘገበ በማወቅ መኮፈስ ይጀምራል፡፡ አቶ ግዛት በርካታ ቅማንት ባሰረና በገደለ ጊዜ ትልቅ ግርማ ሞገስ ይሰማዋል፡፡ ለነ አቶ ግዛት እሒን ያህል የእርዳታ እህልና ገንዘብ አከፋፈልን በኩራት የሚያቀርቡት ሪፖርት ነው፡፡ እሒን ያህል ለመስኖ የሚሆኑ ወንዞችን ጠለፍን አይታሰብም፡፡ ሰዎች አዕምሮቻውና ጉልበታቸውን ተጠቅመው ያመረቱትን ስንዴ ለምኖ ግማሹን በሙስና በልቶ ማሰራጨት ትልቅነታቹህ ነው፡፡ ርስ በርሱ ሲጋደል የነበረን የህብረተሰብ ክፍል ትምህርት በመስጠት ቀየርነው ከማለት ይልቅ በድብቅ ለመጋደያ የሚሆን መሳሪያ ማሰራጨት ትልቅ ጀብድ ሆኖ ተወስዷል፡፡ ይህ በግዛት ምሳሌ ስለቀረበ ሌላህን የክልል ትምክተኛ አመራር የማይመለከትህ እንዳይመስልህ፡፡ አደረጃጀትህና አስተሳሰብህ ተመሳሳይ ነው፡፡
በጠባብ አዕምሮ ሰፊ ክልል ማስተዳደር አይቻልም የሚለውን ሐሳቤን ሌላ ጊዜ በሰፊው በክልላችን ያሉ እውነቶችን በምሳሌ አቅርቤ እመለስበታለሁ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ስለ ክልል አመራሮች የቀረበው ሁሉንም አመለከትም፡፡ በክልላችን ተፈጥራቹህ ለህዝቦች እኩልነትና እድገት መስዋዕትነት የከፈላቹህ አመራሮችን እጅግ በጣም እንኮራባቹሐለን፡፡ ምንም ታጋይ ባትሆኑም የአዲሱ ትውለልድ አስተሳሰብ ተላብሳቹህ ለህዝብ የምተትታገሉ አመራሮችን እንዳንቃለን፡፡ ትምክተኛና ቆርፋዳ አስተሳሰብ ያላቸውን ሸክም አመራሮችን ግን እስከመጨረሻው እንታገላቸዋልን፡፡

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

One Response to Drama of 42-Kebele Administration: in Violation of Resolution by House of Federation

  1. Aleba says:

    Andim Amara endayiqeyem ymilew nigigir qelid new:: Doron sitalelut bmachegna talot enidemalt new::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s