Amhara Regional Government Launches Military Campaign against Judaio-Pag Kemants

Find the following links: https://doro.com/news/post.php

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

One Response to Amhara Regional Government Launches Military Campaign against Judaio-Pag Kemants

 1. Birtu W says:

  ይድረስ ለጭልጋ ወረዳና ለሌሎች አካባቢ የቅማንት ህዝብ በሙሉ
  የቅማንት ህዝብ ሆይ!
  ለዘመናት በማንነትህ ምክንያ ማለትም ቅማንት በመሆንህና ‹‹ቅማንት ነኝ›› በማለትህ ብቻ ለሰው ልጅ አይደለም ለተራ እንሰሳ የማይታሰብ ግፍና መከራ ተፈፅሞብሀል፡፡ ያንተ አባቶችና እናቶች ለባለፉት 800 ዓመታት ያክል በሀሳዊው (በውሸት) ሰሎሞናዊ ዳይናስቲ ተብየው አገዛዝ ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን በመግፈፍና የሌላ ማንነት በላያቸው ላይ ለመደረብ ሲባል ከባድ መከራን ቢያሳልፉም ያን ሁሉ መከራና ግፍ ተቋቁመው ማንነትህ በተጓደለ መልኩም ቢሆን አሁን ያለህበት አድርሰውልሀል፡፡ በዚህ ሁሉ የመከራና የሰቆቃ ሂደት ግን የጥንት አባቶችህ ማንነታቸውን ለማስቀጠል ሲሉ የደምና የአጥንት ዋጋ ከፍለውልህ አልፈዋል፡፡
  ግፉን መቋቋም ያቃታቸውና መከራው የጠናባቸው አብዛኛው ወገኖችህ ደግሞ ሳይወዱ በግድ የሌላ ማንነት ተጭኖባቸው ግማሾቹ ‹‹ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ›› በሚል ቢሂል ውስጣቸው እየበገነ የሌላ ማንነት ታቅፈው አሁነም ድረስ ተቀመጥዋል፡፡ ገሚሶቹ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን አጥፍተውና የድሮ ማንነታቸውን ደምስሰው ሥርዓቱና የሚከተሉት የተዛባ የእምነት ስብከት ባላባሳቸው አስተሳሰብ ምክንያተ አንተን እንደዝቅተኛ ፍጡር እንዲያዩህና እያንቋሸሹህ የሚያደርግ ስብዕናን በአገዛዙ ተላብሰው ዘመናትን ተሻግረው አስካሁኗ ሰዓት ደርሰዋል፡፡
  በዚያ የሰሎሞን ተብየው ሥርዓት የደረሰው ግፍና መከራ በአንተና በአንተ ብቻ የተፈፀመ ሳሆን ጠባሳው በሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረቦችና ህዝቦች ላይም ቢሆን አለ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ብሔረሰቦች ያ ሁሉ የግፍ ፍላፃ አርፎባቸው አልፏል፡፡ ይሁን እንጅ በአንተ ላይ የደረሰው መከራ በሌሎቹ ከደረሰው መከራ ለየት የሚያደርገው አንተ መከራውን ከምንጩ መጋትህና አስካሁኗ ሰዓት ከዚያ የበሰበሰ አስተሳሰብ አለመላቀቅህ ብቻ ነው፡፡
  ዛሬ እነዚህ የኢትዮጵያ ህዝቦች በስማዕታቶች ደምና አጥንት የመከራውን ቀንበር ለአንዴና ለመጨረሻ ቢሰባብሩትም አንተ ግን እንዳላመታደል ሆኖ የምትገኘው ይህ መከራ ከሚመነጭበት አካባቢ በመሆኑ ከባለፈው የስቃይና የመከራ አገዛዝ መላቀቅ ተስኖህ አስካሆኗ ደቂቃ ድረስ በጥይት አረር እየተቆላህ ትገኛለህ፡፡ ያ በአገሪቱ በሙሉ ከሰሜን አስከ ደቡብ ከምዕራብ አስከ መሥራቅ ተበትኖ የነበረው የግፍ አገዛዝና የትምህክት አስተሳሰብ ስማዕታቶች በከፈሉት መስዋትነት ተጠራርጎ ከየአቅጣጫው ቢወገድም በአንተ ላይ ግን የዚያ የግፍ አተላ በላይህ ላይ ተደፍድፎ እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡ በአገሪቱ ተበትኖ የነበረው የግፍና የጭቆና አገዛዝ ተጠረቃቅሞ የግፍ በትሩን ባንተ ላይ በማሳረፍ ላይ ይገኛል፡፡
  የተከበርከው የቅማንት ህዝብ!
  ይህን መከራ እንደሌሎች ኢትዮጵያዊያን ከላይህ ላይ አሽቀንጥረህ ለመጣል በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ትግልና መስዋትነት የፀደቀውን ህገ-መንግሥት መሰረት አድርገህ የእኩልነት መብት ለመጠየቅ አንተ በመረጥካቸውና በወከልካቸው ልጆችህ አማካኝነት ብትጠይቅም አለመታደል ሆኖ ጥያቄህ የተያዘው በእነዚያ የግፍ አገዛዝ ወራሾች እጅ በመሆኑ ለባለፉት አመታት ሲውገረገር መቆየቱን ለአፍታም አትዘነጋውም፡፡ይሁን እንጅ የታገሉለትን የብሔር በሔረሰቦች እኩልነት በፅናት ለማሰከበር በሚተጉ የቁርጥ ቀን ልጆችና ህገ-መንግሥቱ ሳይሸራረፍ አንዲተገበር በሚተጉ፤ ያልተንበረከኩ የኢህአዴግ ታጋዮች አማካኝነት በጊዜ ሂደትም ቢሆን ትግልህ ፍሬ አፍርቷል፡፡ ‹‹ቅማንት የለም›› ያሉ የትምህክት አመራሮች እሬት እሬት እያላቸውም ቢሆን ማንነትክን ተቀብለው በቁራሽ መሬት ሊወስኑህ ውሳኔ አስተላለፈዋል፡፡ አሁን እያደረሱብህ ያለው የግፍ ግድያና ሰቆቃ የጠየከው መብት በተሟላ መልኩ እንዳይመለስና ጉዩን ወደሚመለከተው አካል አንዳታደርስና እንዳታነሳ ለማድረግና የቀጨጨ የቅማንት አስተዳደር ለመመስረት ካላቸው ግልጽ ፍላጎት የመነጨ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ምንም ህገ-ወጥ ሥራ የሰራኸው ነገር እንደሌለ እነሱም ያውቁታል፡፡ አንተን ለመግድልና ባላቸው ዓላማ መሰረት በረቀቀ ዘዴ የራሳቸውን የፖሊስ አባል እራሳቸው አቁስለው ኮሚቴውን ለመወንጅል ሞከሩ፡፡ ያንተ ልጆች ግን እንኳን ጥይት ተኩሰው የሰው ልጅ ለማቁሰል ቀርቶ እንዲት ጠጠር እንኳ በማንም ላይ እንዳልወረወሩ እነሱም ቢሆን ያውቁታል፡፡
  ይህ የአንተን ውክልና ይዞ መብትህን ለማስከበር ሲንቀሳቀስ የነበረ የቅማንት ኮሚቴ አነሰም በዛም አብዛኛው የራሱ የሆነ መተዳደሪያ ያለው አንዳንዶቹ ቢፈልጉ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው በእውቀታቸውና በችሎታቸው (ምንም እንኳ ችሎታና እውቀት ለሥልጣ ባያበቃም) አስከሚኒስተርነት ማዕረግ ሊደርሱ የሚችሉ፣ ቢፈልጉ በሙያቸው የፈለጉበት ቦታ ተቀጥረው ወይም የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው መኖር የሚችሉ፣ አለያም ቢፈልጉ በአገር ውስጥ ቢፈልጉ ከአገር ውጭ ወጥተው የተቀናጣ ህይወተ መምራት የሚችሉ ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ አንተ በማንነት ቀውስጥ ውስጥ እየተረመጠመጥክ፣ በማንነትህ እየተናቅህና እየተሰደብክ፣ በድህነት ውስጥ እየማቀክ ስትኖር የራሳቸው ምቾት ምንም እንዳልሆነ በመረዳት አገሪቱ ያፀደቀችውን ህገ-መንግሥት በመጠቀም መብትህን ለማስከበርና ከዚህ ዘመን ተሻጋሪ ግፍ አንተን ለማላቀቅ አንተ የሰጠሀቸውን ሀላፊነትን በመሸከም ወደሰላማዊ ትግል እንዲገቡ ተገደዋል፡፡ በዚህ የሰላማዊ ትግል ሂደት ምንም እንኳ የሰፊው ህዝብ ድጋፍና ሞራል ወሳኝ ቢሆንም አነዚህ የኮሚቴ አባላት በትምህክት አመራሩ ለባለፉት ዓመታት የተለየ መከራ እና እንግልት፣ አስርና ስቃይ፣ ሞትና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሁላችሁም ቋሚ ምስክሮች ናችሁ፡፡
  ይህ ኮሚቴ በህግ ሳይሆን በሀይል፣ በእኩልነት ሳይሆን በበላይና በበታች በሚያምኑ የወረዳ፣ የዞንና የክልል አመራሮች እጅግ ከባድ መከራን ተቀብሏል፡፡ ይህን መከራ የተቀበሉት አንተ የወከልካቸው ትምህክቶች እንደሚሉት ነገ ከሚቋቋመው የቅማንት የራስ አስተዳደር የሥልጣን ፍርፋሪና ሌላ ጥቅም ጠብቀው ሳይሆን ያንተ መከራና ስቃይ እንዲያበቃ በመወሰናቸውና አንተ የሰጠሀቸውን አደራ ከዳር ለማድረስ ነው፡፡ የአንተ አንገት መድፋት፣ በማንነትህ ምክንያት በሚደረስብህ መድሎና መገለል ለአንዴና ለመጨሻ ነፃ እንድትወጣ ቃል-ኪዳን በመግባታቸው ብቻ ነው፡፡ ሥልጣንና ዝናን ለራሳቸው ቢፈልጉ ኑሮ የትምህክት ቡድኑ ዛሬም ጥያቄውን ርግፍ አድርገው ትተው የእነሱ አሽከር እንዲሆኑ አሁንም ድረስ እያባበሏቸው ይገኛሉ፡፡ ለዚህ ማሳያ ከአንተ አብራክ የተገኙ ቅጥረኛ የቅማንት ባንዳዎች በወገናቸው ላይ የግፍ ግድያ እንዲፈፀም እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህ የአንተን አደራ የተቀበሉ የቁርጥ ቀን ኮሚቴ አባላት የግል ጥቅም ቢያሸንፋቸው ይህን ማድረግ ይሳናቸው ነበር ትላለህ?
  በእነዚህ ጥቂት ባንዳ ልጆች እገዛ የትምህክቱ ርዝራዥ ከአራቱም አቅጣጫ ሀይሉን በማሰባሰብ በሌሎች ላይ ያጣውን የተራ የባላይነት አመለካከት በአንተ ላይ ለመጫንና ኢትዮጵያን ወደነበረችበት የብሔረሰብ አስር ቤት ለመመለስ አንተ ይዘህ የተነሳኸውን የእኩልነት መብት ዳር እንዳታደርስ የግፍ የብረት ቃታውን ከፍቶ፣ ምላጭ ስቦና አነጣጥሮ ተኩሶ በአደባባይ ላይ እየጨፈጨፈህ ይገኛል፡፡ ለገበያ የወጡ እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች ጥዋት ደህና ዋሉ ብለው ከቤታቸው ወጥተው በግፈኞች በተተኮሰባቸው የጥይት አረር ሞተው አስከሬናቸው በቃሬዛ ተመልሷል፡፡ የዚህ ሁሉ መከራ ምንጩ አንተ ወይም የወከልካቸው ኮሚቲዎች ጠበንጃ አንግበው ህዝብ ሲያሸብሩና ሥርዓቱን ለመናድ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተው ሳይሆን ያንተን ነፃነት ለማስመለስ በሰላማዊ የትግል አግባብ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አንተ በሰጠሀቸው ሀላፊነት መሰረት ህዝብ ለሰላማዊ ሰለፍ ሲቀሰቅሱ በመገኘታቸው ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጅ የትምህክት አመራሩ አንተ የወከልካቸውን ኮሚቲዎች ‹‹ህገ-ወጥና በህዝብ ውክልና የሌላቸው ናቸው›› ብሎ በአንተ ላይ ዘብተውብሀል፡፡ ለ24 ዓመታት ማንነትክን ያልመለሰና በግፍ አገዛዝ አድርጎ የኖረ የትምህክት ቡድን ‹‹ጥያቄውን እኔ ነኝ›› የመለስኩልህ ብሎ አፌዘብህ፡፡
  ‹‹ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል›› እንደሚባለው በአደባባይ ላይ የንፁኃንን ደም ከአፈሰሱና ከረሸኑ በኋላ ‹‹የዚህ ሁሉ ድርጊት ምክንያቱ የቅማንት ኮሚቴዎች ናቸው›› እያሉ የቅማንትን ኮሚቴ ከፊሉን በግፍ አስር ቤት ሲያጉሩት ከፊሉን ደግሞ ከሚኖርበት አካባቢ በግፍ እንዲሸሹ ተደርገው በመከራ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ህገ-ወጥ ግለሰቦች የግፍ ግድያ ድርጊት እንደምክንያት ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመከልከል የተወሰደ እርምጃ ሳይሆን ያንተን ደም በከንቱ ለማስፈሰስ ለዘመናት ሲቋምጡና ሲያቅዱ ለነበረው ዕቅዳቸው የወሰዱት ድርጊት ነው፡፡ ይህ ሰልፍ ተደረገም አልተደረገም በማንኛውም ጊዜ እነዚህ ግፈኞች የግፍ ብትራቸውን በአንተ ላይ ከማሳረፋቸው አይመለሱም ነበር፡፡ ልዩነቱ የጊዜ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ከአንተ አብራክ የወጡት እነጠገነ ወለላው ከእርሻ ቦታቸው ላይ በግፍ የተረሸኑት ሠላማዊ ሰልፍ በመጥራታቻው ወይም እነሱ በሀሰት እንደሚከሷቸው የአሸባሪ ድርጅት አባል ሆነው አልነበረም፡፡ ምክንያቱ የቅማንት ቁርጠኛ ልጆች መሆናቸውን ስለሚያውቁና አንተን እየከፋህ እያዩ ዝም የማይሉ ጀግኖች መሆናቸውን ስለሚያውቁ በቅድሚያ በግፍ እንዲረሸኑ ተደርገዋል፡፡ ይሁን እንጅ እነሱን ያስገደሉ የመንግሥት አካል የነበሩ የትምህክት ስብስብ ግለሰቦች ግን ንፁሀን የመከላከያ ሰራዊት በግፍ ገለው ገንዘብ በመዝረፋቸው ዛሬ በህግ ቁጥጥር ውስጥ ውለዋል፡፡ ልብ በል ዛሬም የሚያስገድሉህ የእነዚህ ቅሪቶች ናቸው፡፡
  የተከበርከወ የጭልጋ የቅማንት ህዝብ!
  እነኝህ ግፈኛ አመራሮች በንፁኃን ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ አልበቃቸው ብሎ ዛሬ በየመንደሩና በየቀበሌው እየዞሩ ደርግ ሲያደርግ እንደነበረው ‹‹ሰኔ 6 ቀን በግፍ የተገደሉ ሰዎች ያስገደሏቸው የቅማንት ኮሚቴዎች ናቸውና በጥፋተኛነት አንተ እንድትፈርጅላቸውና አሳልፈህ ለእነዚህ ግፈኞች በራስህ ፍርድ እንድትወስንላቸው ሲያስገድዱህ ይውላሉ፡፡ እነዚህ ዘረኛ አመራሮች ሥርዓቱን ከእነሱ እኩል እያገለገሉ የሚገኙ የቅማንት ልጆች የፖሊስ አባላት ላይ በተጠናወታቸው የዘረኝነት ተግባራቸው ምንም ሳያደርጉ ቅማንት በመሆናቸው ምክንያት ትጥቃቸውን በማስወረድ ላይ ይገኛሉ፤ የቅማንት የመንግሥት ሰራተኞች ያለበቂ ምክንያት እያገዱ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ አመራሮች አንተን በግፍ የገደለውን ልዩ ሀይል በመኖሪያ ቀየህ አሰማርተው እንድትቀልበው፣ ገንዘብና ጉልበትክን አውጥተህ ካምፕ እንድትሰራለት እያስገደዱህ መሆኑን ለአንተ መናገር ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡

  ይህ ሁሉ እየሆነ በአይንህ እያየህና እያወቅህ በጭልጋ ወረዳ በተለይ በአንዳንድ ቀበሌዎች ጥፋቱን የፈፀመው ራሱ ግፈኛው የመንግሥት አመራር መሆኑን በግልጽ ቢያስቀመጡም በአንዳንድ ቀበሌዎች ግን (የቀበሌዎችን ስም መጥቀስ አልፈልግም) ‹‹ጥፋተኞች የኮሚቴ አባላት ናቸው ለፍርድ ይቅረቡ›› የሚል ውሳኔ በስብሰባ እንደደረሱ ተሰምቷል፡፡ እነዚህ ግፈኛ አመራሮች እያደረጉ ያሉት እውን ለሞቱት ወገኖችህ አዝነው የሟች ወገኖችን እንባ ለማበስ ሳይሆን ያነሳኸው የማንነት ጥያቄ ተዳፍኖ እንዲቀርና እጅህን በእጅህ እንድትቆርጥ የተጠነሰሰ የትምህክት ሴራ መሆኑን ምንጊዜም ላፍታም ቢሆን ልትዘነጋው አይገባም፡፡
  እነዚህ ኮሚቴዎች እናንተ በምትወስኑት ውሳኔ ጥፋተኛ ቢባሉ ቢበዛ ከሥር ያለፈ ቅጣት አይጠብቃቸውም፡፡ የአንተ የቅማንት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ግን ዳግም ላይነሳ ይዳፈንና ለዘላለም ወደነበርክበት የበታችነት ራስክን አሳልፈህ ትሰጣለህ፡፡
  ለአንተ ነፃነት የሚታገሉት በግፍ ልጆቸህን፣ ወንድሞችህን፣ አባትህን በግፍ እንዲገደል ያደረጉና የገደሉ የትምህክት አመራሮች ስብስብ ሳይሆኑ ከአንተ በመገኘታቸው ብቻ ያለምንም ልዩ ጥቅም፣ ያለምንም ክፍያ ጊዜያቸውን ፣ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን በመሰዋት ለአንተ ክብርና እኩልነት እንዲታገሉ የወከልካቸው ኮሚቴዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም በመካከልህ ያለውን ሆድ አደርና ባንዳ የቅማንት ግሳግስ ጨምረህ መንጥረህ በማውጣት ማንነትክን ለማስመለስ ሲታገሉ ለእስር የተዳረጉ የኮሚቴ አባላት፣ ከግፈኞች የግፍ እስርና ግድያ ለማምለጥ ሲሉ በመከራ ላይ የሚገኙ ልጆችህ ተፈትተውና ወደ ቤታቸው ተመልሰው አንተ የሰጠሀቸውን ኃላፊነት ከዳር እንዲያደርሱ መተባበሩ አማራጭ የሌለው ውሳኔህ ሊሆን ይገብል፡፡
  ይህን በመጠየቅህ ምክንያት ግፈኞች ሊያደርሱብህ የሚችሉትን ሁሉ መከራና ስቃይ በፀጋ ሳትፈራ ተቀበል፡፡ ነፃነትን ከፈለክ መስዋትነትን አትፍራ፣ ለማንም ባንዳ በመሆን ወገንክን ወደ ባርነት አትመልሰው፡፡ የትግራይ ህዝብ ነፃነቱን የተጎናፀፈው የደርግን የግፍ ጭፍጨፋ በመፍራትና በመሸሽ ሳይሆን የግፍ ጭፍጨፋው በበዛ ቁጥር ይበልጥ በመተባበርና እንደብረት በመጠንከር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቹን ገብሮ ነው፡፡ በልመና እና በፍርሀት ነፃነት እንደማይገኝ ከእዚህ የነፃነት ፋና ወጊ ወገኖችህ ልትማር ይገባሀል፡፡ የጉዳት ደረጃውና መጠኑ ይለያይ እንጅ በትግራይ ህዝብ በሀውዜን ከተማ ነዋሪ ላይ በገበያ ቀን የተፈፀመው የግፍ ጭፍጨፋና በአንተ ላይ በአይከል ከተማ በገበያ ቀን የተፈፀመው የግፈኞች በትር በዓላማ አንድ ናቸው፡፡ ይኸውም ዓላማውም ትምህክቶች የሚያደርጉት የመብትና የነፃነት ጥያቄን በሀይል መድፈቅ ዕድሜ ጠገብ አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡
  የአንተ ወገኖች ቅማንት በመሆናቸው ምክንያት ከእርሻ ሥራቸውና ከንግድ ሥራቸው ተፈናቅለውና ንብረታቸው ተዘርፎ እነሱ በመታደን ላይ ይገኛሉ፡፡ በተቃራኒው አንተ እንድተገደልበት በየቀኑ የሚዶለትበት ሆቴል፣ አንተ እንደተገደል ጠበንጃ እየገዙ የሚያስታጥቁና መረጃ የሚያቀበሉ ግለሰቦች ግን አንተ በምትኖርበት ከተማና ቀየ በነፃነት ሥራቸውን እያከናወኑና እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
  አንተ ቅማንት ነኝ ስላልክ ብቻ ‹‹ለምን ቅማንት ራሱን ቅማንተ ብሎ ለመጥራት ደፈረ›› ብለው ከውጭ አገር አስከ አገር ውስጥ ራሳቸውን አደራጅተው ባንተ የነፃነት መብት ላይ የሚዘምቱ ግለሰቦች ሳያፍሩና ሳይሸማቀቁ በየከተማው ራሳቸውን አደራጅተው እየዘመቱብህ እያየህ እና እየሰማህ አንተ ግን ‹‹መብቴ ይከበር›› ባልክ አንገትክን እንድታቀረቅርና ዳግም ተመሳሳይ ጥያቄ እንዳታነሳ ለማድረግ በይፋ ጦርነት ተከፍቶብሀል፡፡ ይህን የግፍ ድርጊት በፍርሀት ቆፈን ተሸብበህ እጅና አግርህን አጣጥፈህ የምትመለከት ከሆነ ነገ የበረትህ መንጋ ከብት በግፍ ላለመነዳቱ፣የእርሻ በሬህ ከማሳህ ላይ ከቀንበሩ ተፈትቶ ላለመታረዱ፣ ነገ ከአብራክህ የወጣች ሴት ልጅህ በግፍ አንተ እያየህ ላለመደፈሯ፣ ነገ የሰማንያ ሚስትህ በአንተ አልጋ ላይ አንተ እያየህ ላለመደፈሯ ምን ዋስትና አለህ? አላደረጉትም እንጅ ለወሬ ማድመቂያቸው ‹‹ቅማንትን አጋድመን የጠላ ጋን እንቀዳበት ነበር›› ሲሉ እንደነበረው የጉራ ቱሪናፋቸው ይህን ያለፈ ምኞታቸውን ባንተ ላይ በቀጣዩ ላለመፈፀማቸው ምን ዋስትና አለህ?
  ምን አልባት የወርና የሁለት ወራትን የትምህክቶች አስርንና እንግልት ፈርተህ እነዚህ ወኪሎችህን አሳልፈህ ለጠላትህ ከሰጠህ ነገ ባንተ ላይ ለሚከሰተው ዳግም ግፍ በየትኛውም ዘመን በትኛውም ትውልድ ተነስቶ ነፃ ያወጣኛል ብለህ እንዳታስብ፡፡ የወከልካቸው ኮሚቲዎች ሙሴ የአስራኤልን ህዝብ ከፈርኦን የ400 ዓመታት ባርነት እንዳወጣቸው ሁሉ አንተን ነጻ ለማውጣት የተሰባሰቡ መሆናቸውን ተገንዝበህ እጅህን ለመጠምዘዝ ለሚሞከር ቅጥረኛ የቅማንት ባንዳና የትምህክት አመራር እንዳትሸነፍ፡፡
  ‹‹ዛሬ እምቢ ለነፃነቴ›› ብለህ ራስክን ነፃ ካላወጣህና ይህ የጀመርከው ትግል በራስህ ደካማነት ወደኋላ እንዲንሸራተት ካደረከው መቸም፣ የትም ቢሆን በማንኛውም ትውልድ ሊመለስ እንደማይችል ልትገነዘብ ይገባል፡፡ አንተን እያንገላቱህና ግፍ እያደረሱብህ ያሉ የትምህክት ርዘራዦች እንጅ በጭቁኖች መስዋትነት እየተተገበረ ያለው ሥርዓት እንደሥርዓት አለመሆኑን ተገንዝበህ ራስክን እንደቀድሞው በማደረጃት የፌደራል ሥርዓቱን ለሚያስቀጥሉና ላልተነበረከኩት የሥርዓቱ አገላይ አቤቱታህን አሰማ፡፡ አንተ ብትታሰር ሌላው ጥያቄህን በሰላማዊ መንገድ ሳይፈራና ሳይሸማቀቅ እንዲቀጥል ራስክን በጎጥ፣ በመንደር፣ በቀበሌ በወረዳ አደራጅተህ ለሚመለከተው አካል ሳትታክት አቤቱህን አሰማ፡፡ እየደረሰብህ ያለውን ግፍ በዓለም ሁሉ ከጫፍ አስከጫፍ እንዲሰማ ያላሰለሰ ጥረት አድርግ፡፡ ይህን ስታደርግ ግን በእነዚህ ግፈኛና ትምህክት አመራሮች ድርጊት ተነሳስተህ አንተን ወደባርነት ሊመልሱህ ከሚታገሉ ፀረ-ሠላም ኃይሎች ጋር በፍፁም እንዳትተባበር፡፡
  እነሱ የአንተን የቅማንትነት ጥያቄ ላለመስማት ከዋሽግተን አስከ አንተ መንደር ድረስ የተዘረጋ የቀቢጸ-ተስፋ መዋቅር ዘርግተው በመውተርተር ላይ እንደሚገኙ ልብ ልትል ይገባል፡፡ ዛሬ የአንተን ማንነት ለማስጣል በአውሮፓ፣ በአሜሪካ በግልፅና በህቡዕ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ፀረ-እኩልነት ሀይሎች ሳያፍሩና ሳይሸማቀቁ እየተንቀሳቀሱ እያየህ አንተ ማንነትክን ለማስከበር ላነሳኸው ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ የተንቀሳቀሱ የኮሚቴ አባላት ወንጀለኛ አለመሆናቸውን ተገንዝበህ በዚህ ጉዳይ ላይ ለሚደረግ ውይይት ከትምህክተኛ አመራሩ ጋር ምንም አይነት ነገር ላለማድረግ ለራስህ ቃል ግባ፡፡ አሁን ያለህበት ተጨባጭ ሁኔታ በትምህክተኞች የሀይል እርምጃ ውስጥ ቢሆንም ከሞትና ከስር ለማምለጥ ብለህ የምታደርገው የፍርሀት ድርጊት ለዘላለም ባርነት እንደሚዳርግህ አውቀህ ወጣት፣ሽማግሌ፣ ሴት ወንድ ሳትል ለመብትህ ተንቀሳቀስ፡፡ ተራ በተራ ከምትሞትና ከምትታሰር በአንድ ላይ ታስረህና ሞትህ ቀሪው ትውልድ የዘላለም ነፃነቱን እንዲጎናፀፍ አድርግ፡፡
  በመሆኑም በየቀበሌው ወርዶ በኮሚቴዎች ላይ የጥፋተኛ ውሳኔ እንድታስተላልፍ ለሚወተውትህ ቡድን በመጠራው ስብሰባ ባለመገኘትና ከተሰበሰብክም ጥፋተኞች ኮሜቴዎች ሳይሆኑ ግፈኛ ነብስ ገዳዮች ራሳቸው መሆናቸውን አስረግጠህ ያለፍርሀት ንገራቸው፡፡ ፍርሀትህ ለባርነት እንጅ ለነፃነት አያበቃህም፡፡
  በመጨረሻም ሁላችንም ቢሆን በግልፅ ቅማንትን ለማጥፋት በመንቀሳቀስ ላይ ያለውን ሙከራ እስርንና ሞት ሳንፈራ ግንባራችን ለጥይት እጃችንን ለእስር አዘጋጅተን እንታገል፡፡ የምንሞተው አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን አውቀን ሳንፈራ ይህ የነፃነት ትግላችን የሚቀጥልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርብናል፡፡
  በመሆኑም ይህ ጹህፍ የሚደረሰን ሁሉ እያባዛን ለዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች፣ ለሁለተኛና መለስተኛ ደረጃ ተማሪዎች በማድረስ በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እንጅ እንዲገባ በማድረግ ወላጆቻችንና ቤተሰቦቻችንን ለሰላማዊ ትግሉ ትግሉ የበለጠ ወደፊት እንዲቀጥሉ እናድርግ፡፡
  ሊነጋጋ ሲል ይጨልማል በመሆኑ እንጅ ትግላችን ፍሬ ለያፈራ የመጨረሻው ደረጃ ደርሰናል፡፡ የትምህክት አመራሩ ለመጨረሻ እና ለአንዴ ያለ የሌለ ሀይሉን በማሰባሰብ የአንንተን ተወካዮች ከስራ ውጭ በማድረግ የራሱን የአሻንጉሊት አመራር በቅማንት የአስተዳደር ክልል ለመሾም የሚያደርገው እኩይ ተግባር መሆኑን ተገንዝበህ ራስክን እንደገና አደራጅተህ የትምህክቶችን ሴራ ለማፍረስ መንቀሳቀስ ይኖርብሀል፡፡
  ሌላውና ዋነኛው ማድረግ የሚገባህ ነገር ይህን ግፍ የሚፈፅሙ ነብሰ-ገዳዮችን ስም ዝርዝር፣ የአዛዦችን ስም፣ የፈፀሙትን በደል አይነት፣ ድርጊቱ የተፈፀመበት ቀንና ቦታ ብትችል በምስልና በድምፅ ባትችል ደግሞ በማስታወሻ በማሰፈር ለሁሉም ወገን ዕለት በዕለት እንዲደርስ አድርግ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ዛሬ ፍርዳቸውን ባያገኙ ጊዜውን ጠብቀው ወደ ፍርድ መምጣታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ከደርግ የቀይ ሽብር ተዋናኞች የፍርድ ሂደት ብዙ ልንማር ይገባል ፡፡ መረጃ ሀይል መሆኑን ተገንዘብ፡፡
  ይህ የትምህክቶች የመጨረሻ እድላቸው በመሆኑ ምንም አይነት እድል አትስጣቸው፡፡
  ይህን ዶክሜንት ለአርሶ አደሩ በሚመች መንገድና በሚገባው ቋንቋ በማዘጋጀት እንዲደርሰው በማድረግ ለመጨረሻው ምዕራፍ እንነሳ፡፡ ይህን ስታደርግ ትምህክቶች ሊያስሩህ ሊያንገላቱህ እንደሚችሉ አትርሳ፡፡ የጀመርከው የነፃነት ትግል ነውና ሳታመነታ ተቀበለው፡፡ የባለፉ የነፃነት ታጋዮች በትግል ውስጥ የከፈሉትን መስዋትነት አስታውስ፡፡
  ይህ ግፍ በጭልጋ ወረዳ የሚታይ ቢሆንም ከእኔ ስላልደረሰ አያገባኝም ሳትል ከጫፍ ከጫፍ እስከጫፍ አንድ ሆነን ወገኖቻችን ከመከራ እንታደጋቸው፡፡
  ሁሉም ሰው ከሞት አይቀርም፡፡ ለነፃነት ሲታገሉ መሞት ግን ዘላለማዊነት ነው!
  ድል ለጭቁን ህዝቦች!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s