Amhara is not Ethnic Name, But Religious Denomination: Professor Mesfin Woldemaryam 1991

By Mizigena A

የፕሮፌሰር መሥፍን ወ/ማሪያምን እውነቶች የሚክዱ ‹‹የቁልቁለት ተጓዦች››
የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ግንባር (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ) የደርግ ወታደራዊ መንግሥትን በኃይል አስወግዶ በትረ-አገዛዙን በተረከበ ማግሥት ፕ/ር መሥፍንና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር (የያኔው ፕሬዘዳንት) በቴሊቪዥን መስኮት ቀርበው በወቅቱ ስለነበረው የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ውይይት (dialogue) ማድረጋቸው አብዛኛዎቻችን የምናስታውሰው ጉዳይ ነው፡፡ በዚያ ውይይታቸው ወቅት ፕ/ሰሩ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እጅግ ለማመን የሚከብድ ነገር ተናገሩ፤ ይህ በያኔው የሽግግር መነግሥት ፕሬዚዳንትና በሳቸው መካከል በነበረው ክርክር ያነሱት ነገር ‹‹ አማራ የሚባል ብሔር የለም፣ እንዲያውም በኢትዮጵያ ጎሳ እንጅ ብሔር የሚባል ነገር የለም›› በማለት ነበር ሀሳባቸውን ያራመዱት፡፡
በወቅቱ ይህ ንግግራቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች አቧራ አስነስቶ እንደነበርና በግል ስብዕናቸው ላይ ሳይቀር ዛቻ አዘል ንግግር እንዳስከተለባቸው በቅርቡ በፋክት መጽሔት ባወጡት ጹህፍ አስነብበውናል፡፡ ይህን እምነታቸውን ወይም እውቀታቸውን ተጠቀመው ‹‹የክህደት ቁልቁለት›› የሚል መጽሐፍ በማሳተም ‹‹ አማራ የሚባል ጎሳ የሌለ መሆኑንና ‹አማራ› የሚለው ቃል ከክርስትና እና ከመጠመቅ ጋር የተቆራኘ ቃል ለመሆኑ በሰፊው አብራርተው፤ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ‹‹አማራ የሚባል ብሔር አለ›› የሚለው ፈጠራ መሆኑና ይህን በሀይማኖቱ ምክንያት ራሱን ‹አማራ› ነኝ ብሎ የሚጠራውን ህዝብ ለይቶ ለማጥቃት ካለው ድብቅ ዓላማ የመነጨ ነው በሚል ያብራራሉ፡፡
ከፕ/ር መሥፍን ሌላ ‹አማራ› የሚባል ብሔር ወይም ዘር አለመኖሩን ሌሎች የጻፉትን አንደተጨማሪ ማሳያ መጥቀስ እወዳለሁ፡፡ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ ” በሚል በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደኢየሱስ ስለአማራ ትርጉምና ትውፊት የተጻፈውን እንመልከት- “ዐምሐራ” የሚለዉ ቃል መልእክትና ትርጉም ባለዉ ምክንያት በኢትዮጵያ ምድር ለሚኖረዉ ለአብዛኛዉ የአገሪቱ ነባር ህዝብ የተሰጠ ትውፊታዊ ስያሜ ነዉ፡፡ በአጠቃለይ ቅዱስ ኪዳነ ሃይማኖት እየተማሩና እያወቁ በፈቃዳቸዉ ሲገረዙና ሲጠመቁ ‹ዐምሐራ› ወይም ‹ክርስቲያን› እየተባሉ የእግዚአብሔር ህዝብ ሆኑ ይላል፡፡
ይህም ኅብረተሰብ “አንድ ነጠላ ጎሳ ወይም ነገድ ነዉ” ተብሎ ለእርሱ መለያና መታወቂያ ይሆን ዘንድ የተሰጠ ስያሜ አይደለም ይላሉ ፀኃፊው፡፡የቃሉ ፍቺ እንደሚያመለክተዉ ዐምሐራ በኢትዩጵያ ምድር የሰፈሩ ፤ከተለያዩ ጎሳዎች፤ነገዶች፤ዘሮች፤ ቋንቋዎች፤ባህሎችና ሃይማኖቶች የተዉጣጡ ወንዶችና ሴቶች እርስ በርሳቸዉ በመጋባት በሥጋ አንድ የሆኑበት ህልዉና ነዉ” ይሉናል ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደኢየሱስ
አዎ ዐምሐራ የሚለዉ ስም ለምሳሌ አገዉ፤አርጎባ፤አፋር፤ኦሮሞ፤ጉራ፤ጋፋት፤ሓዲያ፤ ወላይታ፤ከምባታ፤ ኩናማ ወይም ትግሬ እንደሚባለዉ በየጎጣቸዉና በየክልላቸዉ በየእምነታቸዉና በየቋንቋቸዉ ተለያይተዉና ተወስነዉ በየስማቸዉ እንደሚታወቁት ብሄሮች ወይም ሴማዉያን ፤ካማዉያን ያፌታዉያን ተብለዉ በመላዋ ምድር ተሰራጭተዉ እንደሚኖ እንደ ሦስቱ የሰው ዘር የትውልድ ቅርንጫፎች ሳይሆን ሰዎ ሲጠመቁ (ኦርቶዶክስን( ሲቀበሉ ብቻ የሚሰጥ ሥም ነው፡፡

ይሁን እንጅ አሁንም ድረስ ይህ ሀቅ ያልተዋጠላቸው ግለሰቦች የፕ/ሩን ‹‹አማራ የሚባል ብሔር የለም›› አባባላቸውን የማይቀበሉ ግለሰቦች ‹‹አማራ ለመኖሩ ይኸው እኔ ምስክር ነኝ›› የሚሉና ‹አማራ› ለሚባል ህዝብ መኖር አማርኛ ቋንቋን መናገር እንደዋና መገለጫ ብለው የሚጠቃቅሷቸውን በማስቀመጥ ለመሞገት ይሞክራሉ፡፡ እኒህ የሰሜን ኮከብ የሚባሉ ጸኃፊ በሎሚ መጽሔት የነሐሴ ዕትም ባወጡት ጹህፍ የፕ/ሰሩ ሀሳብ ሲቃረኑ በጹህፋቸው ሀሳባቸውን አንዲህ በማለት ያብራራሉ፤ ‹‹ትግርኛ ተናጋሪው ትግሬ፣ ኦሮምኛ ተናጋሪው ኦሮሞ፣ ሲዳምኛ ተናጋሪው ሲዳማ — ወ.ዘ.ተ. ከተባለ አማርኛ ተናጋሪውም ‹አማራ› ነው ሊባል የሚችለው›› በማለት ያብራራሉ፡፡ በማከልም ሲከራከሩ ‹‹ሲታረድ ራሱን ያልተከላከለና ያልተፈራገጠ እንሰሳ (በግ) በቁሙ እያለ ‹በግ› ሲታረድ ግን ስላልተፈራገጠ ‹በግ› አይደለም ሊባል አይችልም ማለት ተገቢ ያልሆነ መከራከሪያ ነው›› በማለት የፕ/ሩን ‹‹አማራ የሚባል ህዝብ ቢኖር ከሚደረስበት ጥቃት በጋራ ራሱን መከላከል ይችል ነበር›› አመክኖ (logic) ውድቅ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ ልብ በሉ እኝህ ግለሰብ ቋንቋንና የዘር ሀረግን በቀጥታ ለማስተሳሰር ይሞክራሉ፡፡ እውነቱ ይህ ቢሆንማ ኑሮ በፈረንይና በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት የነበሩ በአፈሪካ ውስጥ የሚገኙ ህዝቦች ፈረንሳይኛና እንግሊዘኛ በመናገራቸው ፍረንችና እንግሊዛዊ ማንነት በተጎናጸፉ ነበር፡፡ ይህ አስተሳሰብ የቋንቋን ባህሪ ካለመገንዘብ ብቻ የተባለ የጹህፍ ማሟያ ይመስለኛል፡፡ ቋንቋ በባህሪው የሚወለድ፣ የሚያድግ፣ የሚያረጅና ብሎም የሚሞት ክስተት ሆኖ እያለ ‹‹አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ ነው›› አባባል ለተጨማሪ ስህተት የሚዳርግ ይመስለኛል፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አማርኛ ቋንቋ በተለያዩ ታሪካዊ፣ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ 80% በአፍ መፍቻም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ መግባቢያነት እንደሚናገር ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ታዲያ ይህ ማለት በኢትዮጵያ 80 እጅ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ አማርኛ በመናገሩ ‹‹አማራ ሆኗል›› ማለት ግን አይደለም፡፡ አማርኛ የፌደራል ቋንቋ እንዲሆን የተደረገበት አብይ ምክንያት በኢትዮጵያ አማርኛ ተናጋሪዎች ስለሚበዙ እንጅ ራሱን አማራ ብሎ የሚጠራ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን በቁጥር ስለሚልቅ አይደለም፡፡
ከላይ በተጨባጭ የተጠቀሱት ጥናቶች የሚያሳዩን አማራነት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ከጀመረበት 4ኛው ክፍለ-ዘመን መባቻ በተለይ ደግሞ ከ13ኛው ክፍለ ዘመን አስክ 20ኛው ክፍለ- ዘመን መጨረሻ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሀይማኖት፣ በአስተዳደር ምክንያት የተፈጠረና የተገነባ ‹ሰው ሰራሽ› ማንነት እንጅ ዘርን መሰረት አድርጎ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የህዝብ ሀረግ ላለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ዕምነት አጥማቂነት በሰሎሞናዊው ተብየው አገዛዝ ጦር ሰባቂነት አማካኝነት በኢትዮጵያዊያን ነባር ህዝቦች ላይ ባደረሱት የማንነት ገፈፋ ወቅት ህዝቦች በጦርነት ሲሸነፉ የሚቀርብላቸው የነበረው አማራጭ ‹‹አንድም የራሴ የሚሉትን እምነት በመተው ተጠምቀው ‹አማራነትን› እንዲቀበሉ አለያም ደግሞ መሬታቻውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀው እንዲፈልሱ› ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ‹ፈላሻ› ተብለው የሚጠሩትን የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ አገው ህዝቦችን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ በተለምዶ ‹‹ቤተ-ኢዝራኤል›› እየተባሉ ሲጥሩ የነበሩ የአገው ህዝቦች አማራነትን (ኦርቶዶክስነትን) አንቀበልም በማለታቸው ምክንያት ከ16ኛ እስከ 21ኛው ክፍለ-ዘመን የዘለቀ የዘር ማጥፋት ወንጀል (genocide) ተፈጽሞባቸዋል፤ በሀይል የተጠመቁት የግዳጅ አማራነትን ተቀብለው የመሬት ይዞታቸው እንደያዙ እንዲቀጥሉ ሲደረጉ አማራነትን (ክርስቲያንነትን) አንቀበልም ያሉት ግን ከዕርስተ-ጉልት እንዲነቀሉ ተደርገው ገዥዎች ‹የረከሰ› በሚሉት ሥራ ማለትም በሽመና፣ በአንጥረኛነትና በሸክላ ሰሪነት እነዲገፉ ተደርገዋል፡፡ በመጨረሻም ‹‹ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም›› ተብለው በ35 ሚሊየን ዲናር ለኢዝራኤል ተሽጠዋል፡፡ በተመሳሳይ ይህ በደል ለሰሜን ምዕራብ ኩሸ ህዝብ ለሆነው የቅማንት ህዝብ እንደ-ቤተ ኢዝራኤሎች ተመሳሳይ መከራን እንዲያሳልፍ በመገደዱ አብዛኛው አማራነት ሲቀበል የቀረው በዲፕሎማሲና ራሱን ለመከላከል ባደረገው ጦርነት ከፈላሻዎች በተሻለ ሁኔታ ማንነቱን ጠብቆ አቆይቷል፡፡ ይሁን እንጅ የራሱ የሆነውን ህገ-ኦሪት ዕምንትና ቋንቋውን ግን ሙሉ በሙሉ መከላከል ባለመቻሉና ሲደርስበት በነበረው የግፍ አገዛዝ በአብዛኛው አማራነት (ክርስቲያንነት) እንዲቀበል ተደርጓል፡፡ ይህም ሆኖ በተወሰኑ ወረዳዎች ዛሬም ቢሆን ራሱን ‹‹ቅማንት ነኝ›› የሚልና በሌሎች ‹ቅማንት› ተብሎ የሚጠራ ህዝብና ቅማንትኛ ቋንቋ በመናገር ላይ ያለ ህዝብ አለ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ለሰሜኑ የአገው ህዝቦች እምነቱን ብቻ አይደለም እንዲቀይር ያደረገችው፤ ማንነቱ፣ ቋንቋው፣ ባህሉ ጭምር ከእርሱ ተወስዶ መልሶ ለእሱ በሌላ ብራንድ (መጠሪያ ሥም) እንዲቀበል ተደርጓል፡፡ የክርስትና ዕምነቱን ወዶም ሆነ ተገዶ ሲቀበል ቋንቋውን እንዳይናገር፣ ባህሉን የእኔ እንዳይል፣ ማንነቱን ጭምር በራሱ አንድበት እንዲክድ ‹ውግዝ ከመ-አሪዎስ› በመባል የማንነት ወረራ ተካሄዶበታል፡፡ አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ህዝቦች (የኩሽ፤ የኦሞቲክና የናይሎቲክ) አንጡራ ሀብት መሆኑ ተዘንግቶ የሴም መሰረት ያለው ተደርጎ ተጻፈ፣ ተተረከ፣ተዘከረ፡፡ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗ ተዘንግቶ ይህን (አማርኛ) ቋንቋ ጭምር ይዘውት የመጡት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የሴም ዝርያ ያላቸው ህዝቦች እንደሆኑ ለኢትዮጵያዊያን ለራሳቸው ተተረከ፡፡ በዚህም ምክንያት ራስን የንጹህ ኢትዮጵያዊያን የኩሽ፣የኦሞቲክና የናይሎቲክ ዘር ነኝ ብሎ ከመቀበል ይልቅ የሴም ዘር ለመባል እሽቀድድሙ ተጧጧፈ፡፡ በመንግሥታዊና በዕምነት ተቋማት ጭምር ስለኢትዮጵያዊያን ሳይሆን ‹‹የምርጥ ዘር›› ስለሚባሉት ለኢዝራኤላዊያን ተሰበከ፣ተወደሰ፣ተዘመረ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ገዥዎች ኢትየጵያዊ መሆናቸውን ክደው ‹‹ከተመረጡት የኢዝራኤል ህዝቦች ወገን ነን›› በሚል በውሸት ማንነት በመጀቦን በተለይ የሰሜን ኢትዮጵያ ነዋሪዎች በማንነት ቀውስ ውስጥ እንዲዘፈቁ አደረጉ፡፡ ንጉሶቻችን ኢትዮጵያዊያንነታቸውንና ጥቁርነታቸውን ክደው ‹‹ሞዓ አንበሳ ዘዕም- ነገደ ይሁዳ›› ብለው የዓለሙ መፋረጃ አደረጉን፡፡ ለዚህ ማሳያ ይሆን ዘንደ አጼ ኃ/ሥላሴ በአንድ ወቅት ለጋዜጠኛ የመለሱት መልስ እንመልከት፡፡ ንጉሱ በ1940ዎቹ አካባቢ አሜሪካን ለመጎብኘት በነጩ ቤተ-መንግሥት ተገኝተው በጋዜጠኞች እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፤ ‹‹— ከጥቁር ህዝብ መሪዎች በአሜሪካ ነጩ ቤተ-መንግሥት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እርሰዎ ለመግባት በመቻለዎ ምን ይሰማወታል?›› ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ የመለሱት መልስ እንዲህ የሚል ነበር ‹‹ እኛ ከንጉስ ሰለሞን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው ቤተሰብ የምንወለድ አይሁድ ነን እንጅ ጥቁር አይደለንም››በማለት በዓለም ፊት ኢትዮጵያዊያንንና ጥቁር የሰው ዘርን በሙሉ አንገቱን አስደፉት፡፡ እውነቱ ግን ንጉሱ ቢፋቁና ትክክለኛ ማንነታቸወ ቢታይ የኩሽ ዘር የሆነው ኦሮሞነታቸው ፈጦ ይወጣ እንደነበር ጥር ጥር አልነበረውም፡፡
ዛሬም ድረስ ከዚህ የብዙ ሺህ አመታት የማንነት ቀውስ ድሪቶ መጎተት ብዙዎቻችን የተላቀቅን አይመስልም፡፡ ዛሬም ከባለፈው ዘመን የክህደት ቁልቁለት ስህተት ሳንማር ‹እንጦረጦስ› በመንደርደር ላይ እንገኛልን፡፡ የጠራ ታሪክ እንዳይኖረን አሁንም በእውቀት ሳይሆን በስሜት እየተውገረገሩ የሚጻፉ ጹህፎችና ተረት ተረቶች በተለይ በሰሜንኑ በሰሜን ምዕራቡ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የማንነት አዙሪት ውስት እንዲባዝን አድርጎታል፡፡ በተለይ ደግሞ በአማራ ክልል በሚገኙ ህዝቦች ላይ የዚያ የተሳሳተ የማንነት አሻራ ዛሬም ድረስ ጥላውን እንዳጠላ ይገኛል፡፡አማራ እንድአንድ የተለየ ህዝብ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ራሱን ከኩሽ አገው ወገን የሚመድበው በአማራ ክልል በጎንደር ክፍለሀገር የሚገኘው የቅማንት ህዝብ በክልሉ መንግሥት ተገዶ ‹አማራ ሆነሀል› ባልተባለ ነበር፡፡ አማራ ህዝብ ራሱን የቻለ የዘር ሀረግ ቢሆን ኖሮ የቅማንትን ህዝብ ማንንት በ21ኛው ክፍለ-ዘመን አስገድዶ ለማስጣል የሚደረገው ጥረት ባልኖረ ነበር፡፡ አማራ ራሱን የቻለ ህዝብ ላለመሆኑ የቅማንት ህዝብ ‹አማርኛ ተናጋሪ ሆነሀልና‹ አማራ ልትሆን ይገባል› ተብሎ በክልሉ ባለስልጣናት ባልተገደደ ነበር፡፡ ይህ የሚያሳያው አማራነት ህዝቦች ተገደው የሚቀበሉት ማንነት እንጅ በሥነ-ፍጥረት የዘር ሀረግ የመጣ አለመሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ቋሚ ምስክር ነው፡፡ አማራ የሚለው ሰው-ሰራሽ ማንነት እንዴት እንደተገነባ በቅማንት ህዝብ ላይ አሁን እየተደረገ ያለው አሰገድዶ አማራ ማድግ (foreceful Amharization) ከበቂ በላይ ምስክር ነው፡፡ ሌላው የክህደት ቁልቁለት ማሳያ በአማራ ክልል የሚገኘው የአርጎባ ህዝብ ከ1983 አስከ 1998 ዓ.ም በአማራነት ስም ተዳብሎ (annex) ለ15 ዓመታት በአማራ ማንነት ሲጠራ ከቆየ በኋላ ዛሬ አማራ ላለመሆኑ በክልሉ ም/ቤት እንደገና በአዋጅ ‹አርጎባ› ተብሎ እንዲጠራ ባልተደረገ ነበር፡፡ አማርኛ የተናገረ አማራ ቢሆን ኑሮ ዛሬ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ህዝቦች ውስጥ 80 በመቶው አማራ በሆነ ነበር፡፡
የአማራ ክልል መንግሥት የራሱን ህዝብ ታሪክ ጥርት ባለ ቋንቋና ተጨባጭ በሆነ መረጃ በማሰደገፍ ሊጽፍ የሚችል የታሪክ ተመራማሪ አስካሁን ድረስ ማግኘት አልቻለም፡፡ የአማራ ታሪክ፣ቋንቋና ባህል ለመጻፍ የሚሞክሩ ተመራማሪዎች ሁሉ የጥናታቸው ማጠንጠኛ እየተንሸራተተ ኩሽ ከሆነው የአገውና የኦሮሞ ህዝብ ከመደባለቅ ሊያድኑት ፍጹም አልቻሉም፡፡ ለዚህ ማሳያ ይሆን ዘንድ አንድ በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ‹‹የአማራ ህዝብ ቋንቋና ባህል›› በሚል ርዕስ በ2001 ዓ.ም የወጣ ጥናት በመግቢያው ላይ እንዲህ ይላል፤‹‹—– መጽሀፉን አስተውሎ የሚያነብ ሰው የአማራ ህዝብ ባህሉም ሆነ ታሪኩ ከሌላው የተለየ መገለጫ ነው ብሎ ለማመን ይቸገራል፡፡ በቋንቋው ላይ የሚታየው የኩሽና የኦሞ ቋንቋዎች ተጋቦትና ተፅዕኖ ሲታሰብም የአማራ ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ጋር እየተዋሀደ እንደመጣ ያመለክታል›› ይላል፡፡ ከዚህ መጽሀፍ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ የክልሉ መንግሥት በሸፈነው የገንዘብ ወጭ ከአዲስ አበባና ከባህርዳር ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የምጣኔ ሀብትና የአንትሮፖሎጅ ምሁራን ‹‹የአማራን ህዝብ ታሪክ፣ቋንቋና ባህል›› በሚል ርዕስ ጥናት እንዲያጠኑ ተደርገው ነበር፡፡ ምሁራኑ የጻፉት የጥናት ውጤት ከአማራው ህዝብ ይልቅ የአገው ህዝብን ታሪክ እጅግ አጉልቶ የሚያሳይ ነበር፡፡ ይሁንእንጅ ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ የክልሉ መንግሥት ይህ ጥናት እንዳይታተም ተደረገና በክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሥም ርዕሱ ከላይኛው ርዕስ በተለየ ‹ታሪክ› የሚለው ወጥቶ ‹‹የአማራ ህዝብ ቋንቋና ባህል›› በሚል አዲስ ርዕስ ተሰጥቶት በ2001 ዓ.ም እንዲታተም ተደረገ፡፡
ልብ በሉ! የዚህ ሁሉ የጊዜ፣ የገንዘብና የእውቀት ኪሳራ መንስኤው የክህደት ቁልቁለቱ የወለደው ጣጣ መሆኑን መገመት አያዳግትም፡፡ ‹አማራ› የሚባል ህዝብ አለ አንኳ ብለን ካመን በክልሉ ውስጥ ከድሮ አንስቶ አስካሁን ድረስ የሚገኙ ህዝቦችን አምኖ ተቀብሎ አማራ የሚባል ህዝብ እንዴት እንደመጣ ጥናቱ በግልጽ ቢያሳይ ምን ችግር ነበረበት? በማንኛውም የታሪክና የጊዜ ሽክርክሪት ሂደት አሁን ላይ አማራ የሚባል ህዝብ መኖሩን ካመን የመጣበትን ሂደት ጥርት ባለ ቋንቋ ለትውልድ ማስተላለፉ ስህተቱ ምኑ ላይ ነው?
በባለፈው ወር ላይ በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አማካኝነት ከሁሉም ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጣ የባህል ቡድን አማካኝነት ‹‹የአማራ ባህል ፌስቲቫል›› እንዲታይ ተደርጎ ነበር፡፡ ይህን ዝግጅት ልብ ብሎ ለተመለከተው ክልሉ የብሔር ብሔረሰቦች ክልል ለመሆኑ ሲቀርቡ የነበሩ የባህል ዝግጅቶች አብይ ማሳያ ናቸው፡፡ በርግጥ በክልሉ ውስጥ የክልሉ መንግሥት አምኖ የተቀበላቸው ሦስት የብሔረሰብ ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ቢገኝም ራሳቸውን የአማራ ዞን ብለው ከሚጠሩ አካባቢዎች የመጡ የባህል ቡድኖች ጭምር በመድረክ ሲያሳዩት የነበረው ዥጉርጉር ባህል መነሻ ምክንያቱ ምን እንደሆን መገመት ቀላል ነበር፡፡ ሌላውን እንተወውና በቅርብ እርቀት የሚገኙት የሰሜን ጎንደርና ደቡብ ጎንደር፣ የምሥራቅ ጎጃምና የምዕራብ ጎጃም የባህል ቡድኖች ሲያሳዩት የነበረው የእስክሰታ አይነት እጅግ የተለያየ ነው፡፡ የወሎንና የሰ/ሸዋ ጉዳይ ሳናነሳ ማለት ነው፡፡
በግሌ አንድ ግለሰብ ወላጆቹ ወይም አሳዳጊዎቹ በህጻንነቱ ያወጡለትን የግል መጠረያ ሥም ለአቅም-ህግ ሲደረስ የማስቀየር መብቱ የተጠበቀ ይሁን እንጅ በማንኛውም መልኩ የወላጅ አባቱን ሥም ወይም በአባትነት የሚጠራበትን የአሳዳጊውን ወይም ደገሞ የጎረቤቶቹን ሥም የመቀየር ህጋዊ መብት ያለው አይመስለኝም፡፡ በመሆኑም አንድ ግለብ ወይም ቡድን ‹‹በዚህ ስም ነው መጠራት የምፈልገው›› የማለት መብቱን አከብራለሁ፡፡ ይሁን እንጀ እኔ በዚህ ሥም ስለምጠራ ያንተንም ሥም በግድ ቀይር ብሎ ግን ማንንም የማስገደድ መብት የለውም፡፡ በአማራ ክልል ህጉን በሚዘውሩትና በትረ-አገዘዙን በያዙት አመራሮች በክልሉ በሚገኙ ሌሎች ህዝቦች ላይ እየተደረገ ያለው እውነታ ይህ ነው፡፡
በመጨረሻም ምን አልባት ይህን ጹህፍ የጻፈውን ‹አማራ› የሚባልን ህዝብ ለማዳከምና የሌላ ፖለቲካ ድርጅት አጀንዳ ተሸካሚ አድረጋችሁ ለምትመለከቱ ቢያንስ የተከበሩ ፕ/ር መሥፍን የየትኛውም ፖለቲካ ድርጀት ደጋፊም የአማራ ህዝብ ጠላትም አለመሆናቸውን ከተገነዘባችሁልኝ ይበቃኛል፡፡ስለዚህ በክህደት ቁልቁለት ተምዘግዝገን ሩቅ ከመሄዳችን በፊት ቆም ብለን ማሰቡ ለአብሮነታችን ወርቃማ መንገድ ነውና ወደ እውነተኛ ልቦናችን እንመለስ እላለሁ፡፡
ቸር ይግጠመን!
dear web manager
please do not omit the title I gave to this document and yet you can translate it for the connivance to post

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

6 Responses to Amhara is not Ethnic Name, But Religious Denomination: Professor Mesfin Woldemaryam 1991

 1. Anteneh says:

  you can ask the woyane government to change the name of the region from “Amhara region” to “agaw-kimant”.

 2. ze armachiho says:

  betam yetmtatabih tsehafi hikiminana yasifeligihal felasha bête esraelochin agew nachew bahilachewen ankeyerim bemaletachew bedel deresebachew sitil koyteh temeliseh ayhudawinet begid techinobinal tilaleh atizelabed

 3. ze armachiho says:

  felashawoch kimant woyim agew aydelu ketabote zion gar yemetu yenigus selemon zeroch nachew behuala chiristina simeta chiristian anhonim bemaletachew new yetegelelut ena gif yederesebachew kefelek yehonkukin the seal and the sign anib

 4. ze armachiho says:

  nigus lalibela agew hono eyale manim syasigedidew yanin yemesele keanede digay felfilo wekir betekiristian lemin lisera chala tegedo new chiristian yehonew. NEw woys amarawoch asegededewut new yerasun paganism emnetun tito yeseraw ? Kemetsdafih befit bedenb ewok kuntsil hasab yizeh ende hitsan atrut.

 5. getplus says:

  Amhara is not Ethnic Name, But Religious Denomination: Professor Mesfin Woldemaryam 1991
  By Mizigena A

  Part-1
  የፕሮፌሰር መሥፍን ወ/ማሪያምን እውነቶች የሚክዱ ‹‹የቁልቁለት ተጓዦች››
  የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ግንባር (ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ) የደርግ ወታደራዊ መንግሥትን በኃይል አስወግዶ በትረ-አገዛዙን በተረከበ ማግሥት ፕ/ር መሥፍንና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር (የያኔው ፕሬዘዳንት) በቴሊቪዥን መስኮት ቀርበው በወቅቱ ስለነበረው የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ውይይት (dialogue) ማድረጋቸው አብዛኛዎቻችን የምናስታውሰው ጉዳይ ነው፡፡ በዚያ ውይይታቸው ወቅት ፕ/ሰሩ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እጅግ ለማመን የሚከብድ ነገር ተናገሩ፤ ይህ በያኔው የሽግግር መነግሥት ፕሬዚዳንትና በሳቸው መካከል በነበረው ክርክር ያነሱት ነገር ‹‹ አማራ የሚባል ብሔር የለም፣ እንዲያውም በኢትዮጵያ ጎሳ እንጅ ብሔር የሚባል ነገር የለም›› በማለት ነበር ሀሳባቸውን ያራመዱት፡፡
  በወቅቱ ይህ ንግግራቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች አቧራ አስነስቶ እንደነበርና በግል ስብዕናቸው ላይ ሳይቀር ዛቻ አዘል ንግግር እንዳስከተለባቸው በቅርቡ በፋክት መጽሔት ባወጡት ጹህፍ አስነብበውናል፡፡ ይህን እምነታቸውን ወይም እውቀታቸውን ተጠቀመው ‹‹የክህደት ቁልቁለት›› የሚል መጽሐፍ በማሳተም ‹‹ አማራ የሚባል ጎሳ የሌለ መሆኑንና ‹አማራ› የሚለው ቃል ከክርስትና እና ከመጠመቅ ጋር የተቆራኘ ቃል ለመሆኑ በሰፊው አብራርተው፤ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ‹‹አማራ የሚባል ብሔር አለ›› የሚለው ፈጠራ መሆኑና ይህን በሀይማኖቱ ምክንያት ራሱን ‹አማራ› ነኝ ብሎ የሚጠራውን ህዝብ ለይቶ ለማጥቃት ካለው ድብቅ ዓላማ የመነጨ ነው በሚል ያብራራሉ፡፡
  ከፕ/ር መሥፍን ሌላ ‹አማራ› የሚባል ብሔር ወይም ዘር አለመኖሩን ሌሎች የጻፉትን አንደተጨማሪ ማሳያ መጥቀስ እወዳለሁ፡፡ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ ” በሚል በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደኢየሱስ ስለአማራ ትርጉምና ትውፊት የተጻፈውን እንመልከት- “ዐምሐራ” የሚለዉ ቃል መልእክትና ትርጉም ባለዉ ምክንያት በኢትዮጵያ ምድር ለሚኖረዉ ለአብዛኛዉ የአገሪቱ ነባር ህዝብ የተሰጠ ትውፊታዊ ስያሜ ነዉ፡፡ በአጠቃለይ ቅዱስ ኪዳነ ሃይማኖት እየተማሩና እያወቁ በፈቃዳቸዉ ሲገረዙና ሲጠመቁ ‹ዐምሐራ› ወይም ‹ክርስቲያን› እየተባሉ የእግዚአብሔር ህዝብ ሆኑ ይላል፡፡
  ይህም ኅብረተሰብ “አንድ ነጠላ ጎሳ ወይም ነገድ ነዉ” ተብሎ ለእርሱ መለያና መታወቂያ ይሆን ዘንድ የተሰጠ ስያሜ አይደለም ይላሉ ፀኃፊው፡፡የቃሉ ፍቺ እንደሚያመለክተዉ ዐምሐራ በኢትዩጵያ ምድር የሰፈሩ ፤ከተለያዩ ጎሳዎች፤ነገዶች፤ዘሮች፤ ቋንቋዎች፤ባህሎችና ሃይማኖቶች የተዉጣጡ ወንዶችና ሴቶች እርስ በርሳቸዉ በመጋባት በሥጋ አንድ የሆኑበት ህልዉና ነዉ” ይሉናል ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደኢየሱስ
  አዎ ዐምሐራ የሚለዉ ስም ለምሳሌ አገዉ፤አርጎባ፤አፋር፤ኦሮሞ፤ጉራ፤ጋፋት፤ሓዲያ፤ ወላይታ፤ከምባታ፤ ኩናማ ወይም ትግሬ እንደሚባለዉ በየጎጣቸዉና በየክልላቸዉ በየእምነታቸዉና በየቋንቋቸዉ ተለያይተዉና ተወስነዉ በየስማቸዉ እንደሚታወቁት ብሄሮች ወይም ሴማዉያን ፤ካማዉያን ያፌታዉያን ተብለዉ በመላዋ ምድር ተሰራጭተዉ እንደሚኖ እንደ ሦስቱ የሰው ዘር የትውልድ ቅርንጫፎች ሳይሆን ሰዎ ሲጠመቁ (ኦርቶዶክስን( ሲቀበሉ ብቻ የሚሰጥ ሥም ነው፡፡

  Will be continued

 6. getplus says:

  Thanks. That’s what we want. People who consider themselves AMHARA must understand that their false History is exposed. You better start looking for your identity now to live in Ethiopia. Have you heard professor Lapiso Delebo interview with Esat? Go youtube and he will tell you that you don’t EXIST at all.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s