Is There Actual Researcher of Gondar History, but Lacks Knowledge about Kemats: In Response to Addis Admas Publications

By Mizigena Adera
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የቕማንትን ህዝብና የጎንደርን ታሪክ በተመለከተ የብሔረሰቡ አባል ከሆኑ ግለሰብና አንድ የ‹‹ታሪክ ተማራማሪ››ን ቃል መጠየቅ በማድረግ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ለማስነበብ ሞክሯል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ቃለ-መጠየቅ የተለያዩ ወገኖችን ጠይቆ ስለቅማንት ብሔረሰብና ስለ ጎንደር አካባቢ በትንሹም ቢሆን በማስነበብ የተለያዩ አስተሳሰቦች እንዲንሸራሸሩ እድሉን የፈጠረውን የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛና በቃል ምልልሱ የተሳሰተፉትን አቶ ነጋ ጌጤንና አቶ ሲሳይ ሳህሌ የግሌን ሀሳብ እንድል መነሻ ሀሳቡን ስላጫሩብኝ በቅድሚያ ሁሉንም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
ይህን ጹህፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ‹‹የታሪክ ተመራማሪው›› የሰጡትን ቃለ-መጠየቅ መሰረት በማድረግና የጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ስሜት የተጫጫነው የመግቢያ ዓረፍተ-ነገርን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ቃለ-መጠይቁ በመግቢያው ላይ ‹‹ጎንደር የቅማንት ናት›› በማለት በአሁኑ ሰዓት በቅማንት ብሔረሰብ እየተነሳ ያለውን የራስ አስተዳደር ጥያቄ ያልተነሳ የቦታ ጉዳይ ጋር ለማላተም የተሞከረ ጥረት ይመስለኛል፡፡ ወደዚህ ግመታ የተመራሁት ከብሔረሰቡ የማንነትና የራስ አሰተዳደር ህገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ጉዳዩ የማይዋጥላቸው ግለሰቦችና የክልሉ አመራሮች ጭምር ያልተባለ ጉዳይ እያነሱ በተደጋጋሚ የጥያቄውን አቅጣጫ ለማሳት የሚያደርጉት ሙከራ በጋዜጠኛው እንደዋና የመግቢያ ርዕስ ሆኖ መነሳቱ ነው፡፡ አቶ ነጋ የሰጡትን ቃለ-ምልልስ ከ‹‹ተመራማሪው›› አቶ ሲሳይ ጋር እንዴት ማያያዝ እንደፈለጉ ማያያዣው አልታይህ አለኝ፡፡ የአቶ ሲሳይ ቃለ-ምልልስ ከምንም ጋር ሳይያያዝ ራሱን ችሎ መቅረብ የሚችል ጉዳይ ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮ ለምን ማያያዝ እንደፈለጉ የሚያውቀው ራሱ ጋዜጠኛው ነው፡፡
አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን የመሰለውን የግል አቋም መያዝ ግላዊ ወይም ቡድናዊ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን አንበቢያን የዚህ ጹህፍ ጸሀፊም የሚስማሙ ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን የሚሰነዘሩት የግል ሀሳቦች፣ በትዉፊትና በምርምር የተገኙ መረጃዎች ከስሜትና ከአድሎ በፀዳ መንገድ ቢሆኑ ታማኝነታቸው እጅግ የጎላ ከመሆኑም በላይ ለወደፊት ለሚደረግ የምርምር ሥራ ተጨባጭ ምንጭ በመሆን ቀጣዩ ትውልድ ያልተዛባ መረጃ እንዲኖረው ይረዳል፡፡ አስከዛሬ ድረስ ስናነበንባቸውና የታሪክ ማጣቀሻ አድርገን የምንጠቀምባቸው የኢትዮጵያና የኢትየጵያ ህዝቦች ታሪክ ምንጩ በአብዛኛው የተረት- ተረት ጥርቅምና በገዥ አወዳሽ ፀሀፈ-ትዛዝ የተጻፉ፣ አለፍም ሲል አንድን ህዝብ ከፍ ሌላውን ዝቅ በማድረግ ባድሎና በተራ ስሜት በተሞሉ ኢትዮጵያዊያንና የውጭ አገር ዜጎች ጭምር ተውገርግረው የተፃፉ ናቸው፡፡
የአንድን አገርና ህዝብ እውነተኛ ታሪክ ማንም በስሜት ተነሳስቶ በዘፈቀደ የሚጽፈው ሳይሆን ነባራዊ ሁኔታዎችን በመረጃ አስደግፎ በመተንተን ስላለፈው የምንማርበት፣ ያለንበትን ጊዜ የምናውቅበትና መፃዒ መንገዳችን የምንቀይስበት መሆን ግድ ይለዋል፡፡ ከዚህ ውጭ የሚፃፉ የታሪክና የምርምር ሥራዎች ውጤታቸው ከላይ ከተጠቀሱት በተቃራኒው ይሆንና የአንድን አገር ህዝብ በማንነት ቀውስ እንዲዘፈቅ ከማድረጉም በላይ ሁሉንም ነገር በመሰለን መንገድ እንድናወገረግረው በር ይከፈታል፡፡ ያ ደግሞ በአገር ግናባታና አበሮነት ላይ የሚኖረው አደጋ እጅግ የከፋ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ታሪኮች፣ ሀይማኖቶች ወግና ልምዶች ያሏቸው ህዝቦች ለዘመናት ተከባብረው አብረው የሚኖሩባት አገር ብትሆንም በየጊዜው የሚነሱ ገዥዎች ስልጣናቸውን ለማራዘም ሲሉ በህዝቦች መካከል ቅራኔ በመፍጠርና ጦርነትን በማካሄድ በህዝቦች መካከል ክፍፍልን ሲፈጥሩ ኑረዋል፡፡ የእነዚህ መንግሥታት ተከታይና አገልጋይ የነበሩ ፀሀፈ ትዕዛዛት አማካኝነት አንድን ህዝብ ሲፈልጉ ‹መጤ› በሌላ ጊዜ ደግሞ ‹ቦታ የለሽ› ለማስመሰል የተፃፉ የተረት ጹህፎችን እንደ እውነተኛ ታሪክ በመቁጠር ዛሬም ድረስ የተዛባ መረጃ ምንጭ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ ተመራማሪ ነን የሚሉ ግለሰቦችም ያን የተዛባ ታሪክ ሳያስተካክሉ ከባለፈው ስህተት በመጨመር ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህ የተዛባ ታሪክ ሰለባ የሆኑት አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች ቢሆኑም ዛሬም ድረስ ታሪኩ፣ ባህሉ፣ ቋንቋው፣ ወግና ልምዱ ጎልቶ እንዳይወጣ በአማራ መንግሥት(ከጥንት አስከዛሬ ድረስ) ብሎም በተለያየ ጊዜ በምርምርና በተመራማሪ ሥም ከባድ ዘመቻ እየተካሄደበት ያለው የአገው ህዝብ አካል የሆነው የቅማንት ህዝብ ነው፡፡ ስለቅማንት ህዝብ በዚህ ጹህፌ ምንም ማለት ባልችልም ትንቢቱ ደረሰ የተባለ ጸኃፊ ‹‹የኢትዮጵያ የፌደራ ሥርዓትና የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወዴት›› በሚል በ2005 ዓ.ም ባሰተሙት መጽሀፍ ላይ ያሉትን የተወሰነች ዓ.ነገር ጠቅሼ ልለፍ፡፡ ጸሀፊው እንዲህ ይላሉ ‹‹የቅማንት ህዝብ የህዝቦችን ማንነት ለማስጣልና ለመግፈፍ በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ በተደረገው የረዥም ዘመናት መከራ ሌሎች ህዝቦች በዘመቻ የደረሰባቸውን የግፍ ፅዋ ከምንጩ የተጎነጨ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም›› ይላሉ፡፡ ይህ ህዝብ ከባለፈው አድሏዊ አገዛዝና ‹‹የምርምር ሥራ›› ተብየ በታሪኩ፣ በማንነቱና በአካባቢው ጉዳይ ‹‹ያገባኛል›› እና ‹‹የእኔ›› እንዳይል አሁንም ድረስ በዚህ ህዝብ ላይ ዘመቻው አልተቋረጠም፡፡
ወደ ጹህፌ መነሻ ምክንያት ወደሆነው አቶ ሲሣይ ሳህሌ ወደሰጡት ሀሳብ ልግባ፡፡ ጋዜጠኛ አለማየሁ በመግቢያው አቶ ነጋ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ‹‹ጎንደር የቅማንቶች ናት›› አሉ የሚል የግለ ስሜት የታከለበት ዓ.ነገር ምን ለማጫር ተፈልጎ እንደተባለ ለዚህ ጹሀፍ ፀኃፊም ሆነ ለመላው የቅማንት ህዝበ ከጀርባው ያዘለውን መልዕክት በግልፅ ይረዳል፡፡ በቀጥታ ንግግር ለመናገር ግን የጎንደር ቤተ-መንግሥታት የተመሰረተበት ምድር አንጡራ የቅማንት ምድር ለመሆኑ ምንም ማስረጃ ማፈላለግ አያስፈልገውም፡፡ በጎንደርና አካባቢው ከቅማንትና ከሌሎች የአገው ህዝቦች አካል ከሆነው በተለምዶ ቤተ ኢስራኤል (ፈላሻ) ተብሎ ከሚጠሩት ህዝቦች ውጭ ‹‹እገሌ የሚባል ህዝብ ነው›› የነበረ የሚል የታሪክ ተመራማሪ ካለ በመረጃ በማስደገፍ ማሰረዳት ይችላል፡፡ ይህ ለሁላችንም ቢሆን ተጨማሪ እውቀትን ስለሚቸረን እንፈልገዋልን፡፡ ከዚያ ባለፈ የሚነገር ከሆነ ግን ከተራ ወሬነትና ተረተ-ረት ከመሆን አያልፍም፡፡
‹‹የታሪክ ተመራማሪው›› ሲሣይ ሳህሌ ስለጎንደር ታሪክ ሲናገሩና በጎንደር አካባቢ ስለሚኖሩ ህዝቦች ሲያብራሩ በቁጥር ከቅማንት የሚያንሱትን ቤተ-ኢስራኤሎችን፣ የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን፣ አልፎም የውጭ አገር የሆኑ ቱርኮችን ሲጠቅሱ ‹‹ቅማንት›› የሚባልን ህዝብ ለመጥራት አልደፈሩም፡፡ ‹‹ተመራማሪው›› ማንን ማለት እንደፈለጉ በግለጽ ባላውቅም ‹‹የባህላዊ ዕምነት ተከታዮች›› ብለው በደምሳሳው ማለፍ ፈልገዋል፡፡ ጎንደር ከተማን እንደቀለበት ዙሪያውን ከቦ የሚኖረው ጎንደር በመንግሥት መቀመጫነት ከመቀርቆሯ በፊትና እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ የቅማንት ህዝብ ነው፡፡ ‹‹ተመራማሪው›› ይህን የማያውቁ ሆነው ሳይሆን በጎንደር ታሪክና በጎንደር ዙሪያ የቅማንትን ህዝብ አርቆ ለማስፈርና አካባቢውን ለሌላ ለማውረስ ካላቸው ደብቅ ዓላማ የሚመነጭ አሰተሳሰብ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በአንድ አካባቢ የሚገኝን ህዝብ በትክክል የማያውቁ ሰው የተማራማሪነት ማዕረግ ሊቸራቸው አይገባም፡፡ ምን አልባት የባህላዊ ዕምነት ተከታዮች ብለው ለመጥቀስ የፈለጉት የቅማንትን ህዝብ ለማለት ፈልገው ከሆነ አሁንም ተሳስተዋል ባይ ነኝ፡፡ ሀይማኖትን እንደዘር ካልቆጠሩት በስተቀር በጎንደር አካባቢ የሚገኙ ቅማንቶች በዚያን ሰዓትም ቢሆን የክርስትና፣ የዕስልምና ዕምነት ተከታዮች እንዲሁም ሀገ-ኦሪትን ዕምነት ተከታዮች ነበሩ፡፡ ምን አልባት ‹‹ ተመራማሪው›› ከፈቀዱልኝ ዕምነት ‹ባህላዊና ዘመናዊ› ተብሎ አይፈረጅም፡፡ ዕምነት ዕምነት ነው፡፡ እምነነትን ማዘመን አይቻልም፡፡ ምን አልባት በሳቸው አተያይ ከወጭ የመጣ ሀይማኖት ሁሉ የዘመናዊነት መለኪያ አድርገው ወስደውት ከሆነ ስህተት ነው እላለሁ፡፡ በጎንደርና በአካባቢው የሚኖሩ ቅማንቶች ተገደው ክርስቲያን ከመሆናቸው በፊት ለአብርሀም ዓምላክ ለሆነው እግዚአብሄር በእነሱ ቋንቋ ‹‹አደራ›› ብለው ለሚጠሩት ዓምላካቸው በድግና (በጫካ) በተከበበ ሥፍራ በመሄድ ምስጋናቸው ያቀርቡ ነበር፡፡ ያ እምነት ደግሞ አንዳንዶቹ እንደሚሉት ለጫካ ዛፍ ወይም ለተራራ የሚደረግ ምስጋና ሳይሆን ለአብርሃም አምላክ ለሆነው ለእግዚአብረሔር (አደራ) ነው፡፡ ዛሬ የጎንደር አብያተ-ክርስቲያን የተተከሉባቸው ቦታዎች በሙሉ ቅማንቶች የኅገ-ልቦና ዕምነታቸው መፀለያ ቦታ ነበር፡፡ በጎንደር እና አካባቢው የተተከሉ የኦርቶዶክስ አድባራት የቅማንት ህዝብ የመፀለያ ቦታዎች ነበሩ፡፡ ይህን ማጥናት ለሚፈልግ አካል መረጃውን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡
“የሰሎሞናዊው” ዳይናስቲ ከመመስረቱ በፊትና ከተመሰረተም በኋላ ቅማንቶች በጎንደርና በአካባቢው የፖለቲካና የዕምነት መሪ በሚመራው ተቋም በወንበር ሥርዓት የቅማንት ህዝብ ይተዳደር ነበር፡፡ እንደ ኦረሞዎች የገዳ ሥርዓት ማለት ነው፡፡ ይህ የወንበር ሥርዓት ዋናውና የበላይ መሪ የሚሆነው ጎንደር አካባቢ የሚገኘው ሲሆን ሌላኛው ጭልጋ አካባቢ ሚገኘው ነበር፡፡ ለዚያም ነው ጎንደር የሚለው ቃል በቅማንትኛ ‹‹የጌታ መነሻ›› የሚል ትርጉም የተቸረው፡፡ አጤ ፋሲል በ1630ዎቹ አካባቢ ቤተ-መንግሥታቸውን በጎንደር ሲመሰርቱ ከነዚህ የቅማንት ወንበሮች ጋር በመደራደርና ሥልጣን በማጋራት ነበር፡፡
“ተመራማሪው” ጎንደር ለሚለው ሥም ቃሉን የቅማነተኛ ላለማድረግ ብዙ ዳር ዙረዋል፡፡ ስለ ጎንደር የዳቦ ስም ለማውጣት ከአሁን በፊት ብዙ ብዙ ተብሏል፤ ተጽፏል፡፡ ጭራሽ ንጉሱ ከባህታዊ አስከ ጠንቋይ ድረስ ከኳተኑ በኋላ ነው ‹ጎ› የሚል ስም ያሰወጡት የሚል መላ መት ከመምታት ይልቅ ወደ እወነቱ ለምን መጠጋት አልፈለጉም፡፡ ለንጉሱ የመጀመሪያ ፊደሏ ‹ጎ› በሚባል ቦታ ላይ ቤተመንግሳቸውን እንደሚሰሩ በራይ ያዩ ባህታዊው ሶስቱን ፊደላት ማለትም ‹ንደር› ከማየተቸው በፊት ነግቶባቸው ነው የቦታውን ሙሉ ቃል ‹‹ጎንደር›› ሳይሉ ከጎርጎራ አስከጎጃም የምንግሥታቸው መቆርቆሪያ ቦታ ለማግኘት ያንከራተቷቸው? የሚገርመው ግን ለጎንደር ስም አወጡ ተብሎ የተነገራለቸው ሰዎች አማርኛ የማይችሉ ከሰሜን አካባቢ የመጡ ግለሰቦች ናቸው ተብሎ ሺ ጊዜ ተነግሯል፤ ተፅፏል፡፡ መረጃ የሚሉት ይህን ከሆነ እውነትም ‹‹ተመራማሪ›› ናቸው፡፡ ለታሪክ ተመራማሪው አንድ ጥያቄ ላቀርብላቸው እወዳለሁ፡፡ እውነተኛ የታሪክ ተመራማሪ ከሆኑ ለምርምር የሚያግዛቸው ሀሳብ ላጭርላቸው፡፡ ከቋራ እስከ ጃንአሞራ፣ ከወልቃይት አሰከ ፀለምት በለሳ- አብናት፣ ከርብ አስከ አንገረብ ዙሪያ ገባ ያሉ የቦታና የወንዝ ስሞች በማን ቋንቋ እንደሚጠሩ ለምን አይመራመሩምባቸውምና የፍልስፍና ዶክተሬታቸውን አይዙም? አንድም ቦታ በአማርኛ ወይም በሌላ ቦታ የሚጠራ ሊያገኙ አይቸሉም፡፡ ይህ እውነት ምድር ላይ ባለበት አገር የጎንደርን ሥም የከመንትነይ (ቅማንተኛ) ስም አይደለም ማለት ነገሩን ምርምር አያስመስለውም፡፡ በእርግጥ ‹‹ተመራማሪው›› በግልፅ ይህን ባይሉም የጎንደር ስም ቅማንትኛ ለመሆኑ መጠራጠር አልነበረባቸውም፡፡
ጎንደር በከተማነት ከመቆርቆሯ በፊት እነማን ይኖሩበት እንደነበረ ማወቅ ከፈለጉ የቅማንት ባላባቶችን ጠጋ ብለው ይጠይቁ፡፡ ቤተ መንግሥቱ የሰፈረበትና ዙሪያው እነማን ጤፍና ስንዴ ያምርቱበት እንደነበር ዝርዝር መረጃ ያገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንና የመንግሥት ቁርኝት እጅግ እጅና ጓንት እየሆነ ሲመጣ ቤተ-ክረስቲያኗ በጎንድር አካባቢ የሚገኙ የቅማንት መሬቶችን በመንጠቅ ለዕምነቱ ተከታዮቿ፣ ለዕመነቱ መሪዎች ቤተሰቦች ከሌላ አካባቢ እያመጡ እንዲሰፍሩ ተደርገዋል፡፡ ለአብነት ያክል ‹ብላጅግ› በሚባል ቀበሌ ከጎንደር ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በግምት በ7 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኙ ሰፋሪዎች ከሌላ ቦታ መጥተው የተቀመጡ ናቸው፡፡ ለዚህ ምስክርነት ራሳቸው ሰፋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ታዲያ ይህ ጥሬ ሀቅ ባለበት አገር ቅማንትን ጎንደሬ ላለማድረግና አርቆ ለማሰፈር ከዚሀ አለፍም ሲል ‹‹መጤ›› ለማለት የሚሞክሩ ግለሰቦች እጅግ ያሳዝኑኛል፡፡ ይህን ስል ግን በአሁኑ ሰዓተ ከሌላ አካባቢ እየመጡ መደበኛ ጎንደሬ የሆኑ የሌላ አካባቢ ተወላጆች ጎንደርና አካባቢው የሉም ለማት አይደለም፡፡
‹ተመራማሪው› በነካ ምርምራቸው ስለ ጃንተከል ዋርካ እንዲያስረዱ በጋዜጠኛው ተጠይቀው ሲመልሱ ‹‹አጼ ፋሲል ተከሉት ተብሎ ስለሚገመት ስሙም ‹ጃንተከል› ማለትም ‹ንጉሱ የተከሉት ነው› ተብሎ ይገመታል›› ብለዋል፡፡ መልካም ነው፤መገመት አይከለከልም፡፡ ግን በዚህ አካባቢ ቀደምት ነዋሪዎች ቅማንተኛ ተናጋሪ የሆኑ የአገው ህዝቦች ብቻ ናቸው፡፡ ምን አልባት ቃሉ ‹‹ቅማንትኛ ይሆን?›› ብለው መላ መት ቢመቱ ትክክለኛ ስሙ ምን ማለት እንደሆነ ማግኘት ይችሉ ነበር፡፡ ጃን ተከል ዋርካ ‹‹ጃን ተከል›› የተባለው አጤው የተከሉት ነው ብለን እንቀበልና ይህ ከሆነ በነካ የግምት ምርመራቸው የሚከተሉትን ቦታዎች ስም ትርጉም ይገምቱልን፤ ጃንፈንቀራ፣ ጃንአሞራ፣ ጃንሆይ፣ ጃንዋራ፣ ጃንቫርታ፣ጃንሜዳ፣ ጃንከው… ልቀጥል? በቅማንትኛ ‹ጃን› ማለት ትልቅነትን፣ ግዙፍነት የሚገልጽ የስም ገልጭ ቅጥያ ነው፡፡
የአንድ ዋርካ ዛፍ አማካኝ እደሜው ከ1500 አስከ 2000 ዓመት ይደርሳል፡፡ ምን አልባት የጃንተከል ዋርካም አጤ ፋሲል ከነገሱበት ዘመን እጅግ ርቆ እንደሚበልጥ አያጠራጥርም፡፡ የዛፉን እድሜ ለመገመት የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት ሊያድርጉበት ይችላሉ፡፡ በጎንደር አካባቢ በዚህ ዋርካ አማካኝነተ ትንቢት መሰል ንግግር ይነገርበታል፤ ጃን ተከል ዋርካ መሬት ሲነካ——–!
በዚህ ዛፍ ሥር ጥንት ቅማንትና ሌሎች የአገው ህዝቦች በራሳቸው ቋንቋ ገበያ ያካሂዱበት ነበር፡፡ አለፍም ሲል የሚገመት መላ መት አለ፡፡ ዋርካው የቅማንት ባላባቶች የመቃብር ሥፍራ እንደሆነም ይነገራል፡፡
በመጨረሻ የምለው ነገር ስለጎንደር እና አካባቢው ትክክለኛ ታሪክ ለማወቅ የፈለገ ተመራማሪ ወይም ፀኃፊ ከቅማንት ህዝብና ከቅማንትኛ ቋንቋ የተገነጠለ ጹህፍና ምርምር ቢያካሂድ ከተረት ተረት ያለፈ አይሆንም፡፡
እውነተኛ ኢትዮጵያን ለማወቅ እውነተኛ ምርምር ያስፈልጋል!

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

One Response to Is There Actual Researcher of Gondar History, but Lacks Knowledge about Kemats: In Response to Addis Admas Publications

  1. gashaye melese says:

    amahara leaders are not history makers,they are history snatchers

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s