“Canaan-Egypt Origin Gondaris”

By Mizigena A

ኢትዮጵያ የተለያዩ ህዝቦች የሚኖሩባት አገር ብትሆንም ስለህዝቦቿ ለረዥም ዘመናት በጽሀፈ-ትዕዛዝ ዲስኩረኞች፣በደብተራ ተራኪዎች የሚነገረውና በውጭ አገር ፀሀፍት ተውገርግሮ ሲላቁጥ የነበረው ‹ታሪክ መሰል› ነገር በአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ በመስረፅ በአጉል የበላይና የበታች የማንነት ቀውስ ውስጥ እንዲዘፈቁ አድርጓቸዋል፡፡ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ለዘመናዊ ትምህርትና ምርምር የነበረን ቅርበት እምብዛም በመሆኑ የውጭ አገር ታሪክ አዋቂ ተብየዎችና ሀይማኖታዊ ሚሸነሪዎች ለራሳቸው ተልዕኮ ማሰፈፀሚያ አጣመውና አወላግደው የሚነግሩንና የሚጽፉልንን ሁሉ ያለምንም መጠራጠር እንደወረደ እውነትና ቁም ነገር ያለው አድረገን በመውሰድና ይህን የተዛባ ታሪክ መሰል ሀሳዊ ጉዳይ ከትውልድ ትውለድ ስናስተላልፍ ዘመናት ተቆጥረዋል፤ ይህ አይነት አመለካከት ሙሉ በሙሉ ሳይቀረፍ ወደ 21ኛው ክፍለ-ዘመን ተሸጋግረናል፡፡
በዚህም የተነሳ “የኢትዮጵያ ምድር በእግዚአብሔር ለተመረጡት የሰም ወገን ነን ብለው ለሚያስቡ ህዝቦች ብቻ የተፈቀደች በማስመሰል እራሱን ኩሽና ናይሎቲክ ብሎ ለሚጠራው ኢትዮጵያዊ መኖሪያ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደችም” በማለት ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ጦርነት በተለይ በአገሪቱ የሰሜን ክፍል ተካሂዷል፡፡ የዚህ ጦርነት ውጤትም በአገሩ ላይ ተሸናፊው ‹ገባር‹ አሸናፋ ‹አስገባሪ› እንዲሆን በማድረግ በህዝቦች ዘንድ የመከራ ዘመን እንዲያሳልፉ ዳርጓቸዋል፡፡ የዚህ አይነት የተወላገደ አስተሳሰብ በዚሀም ብቻ አላቆመም፡፡ በአንዳንዶቹ ላይ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከናካቴው እንዳይሰማቸውና በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከወኑ ፖለቲካዊ፣አስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች ‹አይመለከተንም› እንዲሉና ለተፈቀደላቸው ለእነዚህ ራሳቸውን በሀሰት ‹የሴም ወገን› ብለው ለሚጠሩ ወገኖች ብቻ በምድርም በሰማይም የተተወ እስኪመስላቸው ድረስ እንዲያምኑ ተሰበከ፡፡ በዚህ ምክንያት የሰሜንና መካከለኛው ኢትዮጵያ ነባር ሕዝቦች የዚህ የማንነት ቀውስ የመጀመሪያው የአደጋው ሰለባ እንዲሆኑ ተዳርገዋል፡፡
አገዛዛቸውን ዘላለማዊ ለማድረግ የሄዱበት ሌላኛው መንገድ በህዝቦች ላይ ‹መጤ› የሚል ስም በመለጠፍ ከቀያቸው በማሳደድና መሬታቸውን በመንጠቅ መተዳደሪያ አልባ ማድረግ ነበር፡፡ የዚህ አስተሰብ የመጀመሪያ ገፈት ቀማሾች ከአገው ወገን የሚመደቡት የቅማንትና በተለምዶ ቤተ አስራኤል (ወይንም እነሱ ያወጡላቸውን ስም ለመጠቀም ፈላሻ) ነገዶች ነበሩ፡፡
በተለይ እነዚህ ብዙ ጽሐፊዎች እንደሚሉት የአገው ወይም የJew ዘሮች፡ የአብርሀም እምነት የሆነውን ህገ-ልቦና (worship of Abraham) አጠንክረው ሲከተሉ ስለነበር በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የክርስትና እምነት በቀላሉ ሊቀበሉ አልቻሉም ነበር፡፡ በቅማንትና በቤተእሰራኤላዊያን መካከል የሚታየው ልዩነት በኦሪት እምነትና በቅማንቶች ህገ-ልቦና ይዘው በመቀጠላቸው ምክንያት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት የህዝብ ከመሆኑ በፊት የቤተ-መንግስት እምነት ስለነበር ህዝቦችን አስገድዶ ወደ ክርስትና የመቀየሩ ሂደት ተጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ይሁንእንጅ በተለይ ‹ቤተ-አስራኤላዊያን› እምነታቸውን በቀላሉ ሊተው ባለመቻላቸው የሀይማኖት ጦርነት ዋና ሰለባዎች ሆኑ፡፡ በዚህ የተነሳ ቤተ አስራኤላዊያን ከእሰራኤል የፈለሱና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ተደርጎ በክርስትና እምነት አራማጆች በመሰበኩ ባይተዋርነት እንዲሰማቸው መንገዱ ተከፈተ፡፡ የሚያሳዝነው ነገር ግን ከእስራኤል መጡ የተባሉ ህዝቦች ‹‹ከሰለሞን የተወለድኩ ነኝ›› የሚለው የገዢው መደብ የራሱን ወገን (በሀሰትም ቢሆን) በጠላትነት የመፈረጁ ምክንያ የጉዳዩን ግርንቢጥነት (መጣረስ) ቁልጭ አድርጎ ያመለክታል፡፡ በመቀጠልም ‹የተጠመቀ ይድናል› የሚለው ሀይማኖታዊ ስብከት ቀርቶ ‹ያልተጠመቀ ከመሬቱ ይነቀላል› በሚለው ፖለቲካንና ሀይማኖትን አጣምሮ በያዘው ‹ሰሎሞናዊ ዳይነስቲ› ክርስትናን እንዲቀበሉ ተገደዱ፡፡ በአብዛኛው የኦሪት እምነታቸውን በመምረጣቸው ከመሬታቸው እንዲፈልሱ (evacute) በመደረጋቸው ‹ፈላሻ› የሚል ሥም በመስጠት እንዲሳደዱና መሬታቸው እንዲቀማ ተደርገ፡፡ በመጨረሻም ኢትዮጵያን ትተው እንዲሄዱ ተደረገ፡፡
በተመሳሳይ መንገድ እንዲታዩ የተደረጉት ሌሎች የአገው ህዝቦች ደግሞ ቅማንቶች ነበሩ፡፡ ቅማንቶች እንደቤተአስራኤል ሁሉ እምነታቸው ህገ-አብራሀም በመሆኑ ለክርስትና ሀይማኖት ከፍተኛ ተቃውሞ ያሳዩ ነበሩ፡፡ ይሁን እንጅ ከቤተስራኤላዊያን ለየት የሚያደርጋቸው ክርስትና እምነትን ‹አንቀበልም› በሚል ጦርነት አላወጁም፡፡ ይልቅ ክርስትናን በመቀበል ሁለቱን እምነት(የራሳቸውን ጨምሮ) ጎን ለጎን በማስኬዳቸው እንደቤተ እስራኤላዊ ወንድሞቻቸው ከመሬታቸው ሙሉ በሙሉ ተነቅለው አንዲፈልሱ አልተደረጉም፡፡ እምነቱን የተቀበሉ ቅማንቶች ራሳቸውን ‹አማራ› ብለው በመጥራት የአጥማቂው አካል ተደርገው በመቆጠራቸው በመሬታቸው ላይ እንዲቀጥሉ ተደርገዋል፡፡ እነዚህ ህዝቦች በአሁኑ ሰዓት በደንቢያ በአለፋ በቋራና ወገራ ያሉ ህዝቦች ክርስትናን ቀድመው በመቀበላቸው ምክንያት አማራ ተበለው እንዲጠሩ የተደረጉ የቅማንት አካል ናቸው፡፡ የክርስትና እምንትን ‹አንቀበልም› ባሉ ቅማንቶች ግን ፖለቲካዊና ሀይማኖታዊ በደሎችን አላስተናገዱም ለማለት አይደለም፡፡ እነዚህ በማንነታቸውና በዕምነታቸው ጠንተው የቀሩ የቅማንት ህዝቦች እንደቤተኢሰራኤላዊያን ወገኖቻቸው ኢትዮጵያ የምትባል አገር ‹የእኔ ናት› የሚል ስሜት እንዳይሰማቸውና መጤ ነን ብለው እንዲያስቡ ለማድረግ የውሸት ማንነት ላያቸው ላይ በተለያየ መንገድ እንዲለጠፍ ተደረጓል፡፡ ከእነዚህ የሀሰት ዲስኩሮች መካከል ‹‹ቅማንቶች የመጡት ከግብጥ ነው›› የሚል ነበር፡፡ ለዚህ ተረት ተረት አባባል መነሻ የሆነው በዋናነት በአፈታሪክ ተደጋግሞ የሚነገረው አባባል ነበር፡፡ ተረቱም በክበረ-ነግስት መጽሀፍ እንዲህ ተብሎ ተቀምጧል ‹‹ ካም ከእስያ በባበለመንደብ ተሻግሮ መጥቶ ወደ ኢትዮጵያ ገባ፡፡ ይህም የሆነው በ2787 ዓ.ዓለም 2713 ዓመት ከጌታችን ከየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት ነው›› ይላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በቅማንት አባቶች የሚነገረው ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኘው የከነአን ምድር በርሀብ በተመታች ጊዜ የቅማንት አባት የሆነው አነይር ከሚስቱና ከልጆቸ ጋር በመሆን በግብጥ በኩል አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደደ›› ይላሉ፡፡ አለቃ ታየ ደግሞ ‹የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ,1958› በሚለው መጽሀፋቸው ‹‹በነገድ ካም ዘመን ሦስት ነገዶች በየጊዜው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፡፡ እነርሱም ነገደ ሻንቅላ ነገደ ቅማንትና ነገደ ወይጦ ናቸው›› ይላሉ፡፡ ለዚህ ሁሉ የታሪክ መዛባት ምንጩ ክብረ-ነግስት የተባለው የውሽት ክምር ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ህዝቦች ከተባለው ቦታ ሰለመምጣታቸው የሚያሳይ ምንም አይነት የአንትሮፖሎጅ፣የሥነ-ልሳን፣ የፖሌእነቶሎጅ እና ሌሎች መረጃዎቸን መሰረት በማድረግ የተጠቀሱ አልነበሩምና፡፡
በዚህም ምክንያት ‹‹ቅማንቶች ግብጣዊ ናቸው፣ አንድ ቀን እንደ ቤተ እስራኤላዊያን ኢትዮጵያን ለቀው ወደ መጡበት ግብጥ ይሄዳሉ›› የሚሉ ተረት ተረት ማደናገሪያዎች በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሀይማኖት መሪዎች ጭምር ሆን ተብሎ በመሰበኩ የቅማንት ህዝብና ሌላው የጎንደር ህዝብ የዚህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ሰለባ እንዲሆን ተደረገ፡፡ በመሆኑም ለዘመናት የቅማንቶች መሬት በግፍ እንዲወረርና የመሬት ባለቤት እንዳይሆኑ ለማድረግ ከተከናወኑ ተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ የ1966 ዓ.ም አብዮትና የ1967 ዓ.ም የመሬት ላራሹ አዋጅ ሙሉ በሙሉ ከዚህ አደጋ የቅማንትን ህዝብ ታድጎታል፡፡ በእርግጥ በዚህ ሁሉ ሂደት ‹መሬትክን አምጣ አላመጣም፣ በትወለዳለህ አትወለድም› በሚል ሰበብ አስከ ዘመነ ኃይለስላሴ ድረስ የቅማንት ህዝብ ከባድ መከራን አሳልፏል፡፡ በሰሜኑ የአገራችን ህዝቦች ዘንድ በመሬት ስሬት በኩል የነበረውን ማንም የታሪክ ፀሀፊ ለማስቀመጥ አልደፈሩም፡፡ ከመሬታቸው ተነጥቀው ገባር ተደርገው የነበሩት የደቡብ ህዝቦች የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ከእነሱ በፊት የአገው ህዘብ በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ ቅማንትና ቤተእስራኤል ከባዱን ግፍ ተጎንጭቷል፡፡
ይሁእንጅ የዚያ የተበላሸ አስተሳሰብ የዞረ ድምር በቅማንት ህዝብ ላይ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል ማለት አይቻልም፡፡ በቅማንት ህዝብ ላይ በ12ኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረው አስገድዶ ማንነትንና አምነትን የማስቀየር ድርጊት አስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን በመዝለቅ ችግሩ ዛሬም ሙሉ በሙሉ አልጠፋም፡፡
የፌደራል ሥርዓቱ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ጥሩ ነገር አመጣም አላመጣም ቢያንስ ህዝቦች በእውነተኛ ስማቸው እንዲጠሩ አድርጓቸዋል፡፡ ዉጤቱ ለኢትዮጵያ ይበጃትም ያጥፋትም ህዝቦች ቋንቋቸውን እንዲያሳድጉ መሰረት ጥሎላቸዋል፡፡ ይህ እየተደረገ ባለበት ሥርዓት ግን የቅማንት ህዝብ በግድ ማንነትክን ትተህ የሌላ ማንነት መጎናጸፊያ ካልደረብክ እነሱ መጣበት ወደሚሉት ‹‹የግብጥ ምድር ትመለሳለህ እየተባለ›› በአደበባይ እየተነገረው ይገኛል፡፡ የቅማንትን ህዝብ ቀደምትነትና ኢትዮጵያዊነት ለማደናገር የሚሞክሩ ሰዎች አንድም ከቅማንት አብራክ ወጥተው ራሳቸውን ወደሌላ ማንነት የቀየሩ አለያ ደግሞ በማንነት ቀውስ ዉስጥ የሚዳክሩ ቡድኖች ለመሆናቸው መጠራጠር የሌለበት ሀቅ ነው፡፡ ለቅማንት ኢትዮጰያዊነት የእነሜቴ አይከል አድባር ፣የጃን ተከል ዋርካና የፋሲል ግንብ ዛሬም ድረስ ቋሚ ምስክሮች ናቸወ፡፡
እጅግ የሚሰቀውና የሚያሳዝነው ድሮም ሲያደርጉት እንደነበሩት የዚህን ህዝብ መልካም ስም ለማጉደፍ ቅማንትን በኢትዮጵያ እድገት፣ አንድነትና ልማት መንገድ ላይ የቆመ በማስመሰል የሚያሰወሩት ወሬ አደገኛነቱ የከፋ ከመሆኑም በላይ በነገ አብሮነታችን ላይ የሚጥለው ጠባሳ ከባድ ነው፡፡ ቅማንት ራሱን አንድም ቀን ‹ግብጣዊ ነኝ› ብሎ ቆጥሮና አስቦ አያዉቅም ፤ግብጦችም ‹ ቅማንት የሚባል ህዝብ ጠፍቶብናልና አፋልጉን› ብለው የዓለምን ህብረተሰብ አልጠየቁም፡፡ የዚህ ሁሉ የወረደ አስተሳሰብ መሰረቱ ኢትዮጵያዊ ‹እኛና እኛ ብቻ› ከሚል የሚመነጭና ሌላው በባይተዋርነት ስሜት በአገሩ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ጉዳይ አያገባኝም ብሎ እንዲያስብና ትምህክት ቡድኖች ራሳቸውን ብቻ የአገሪቱ ብቸኛ ተዋናይ ለማድረግ ካላቸው ደብቅ ዓላማ የሚመነጭ መሆኑ ለማንም ግልጥ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት የቅማንት ህዝብ ማንነቱ ተሰርዞ በሌላ ማንነት ሲጠራ ‹ለምን ይህ ይሆናል? ብሎ በመጠየቁ ምክንያት ጎሰኛና ጠባብ የሚል ስም ተለጥፎለት በህገ-መነግሥታዊ መብቱ እንዳይገፋበት እየተደረገ ይገኛል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ የቅማንትን ማንነት ለመሰረዝ የሚያቀነቅኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች በሌላ በኩል የእነሱ ወገን በግዳጅ የሌላ ማንነት እንዲቀበል ተደርጓል፣ ወደሌላ ክልል እንዲከለል ተደርጓል እያሉ መንግሥትን እየወነጀሉና ይህንም ድርጊት በሀይል እናስመልሳለን እያሉ ባሉበት ወቅት ‹‹በአንተ ላይ እንዲፈጸም የማትፈልገውን በሌሎች ላይ አታድርግ›› የሚለውን ወርቃማ አባባል መርሳታቸው ነው፡፡
ይህን በግዛት አንድነት ሥም በቅማንት ህዝብ ላይ የተሸረበ ሤራ የማይገነዘቡ ጥቂት የቅማንት ልጆች በተለይ (ዉጭ አገር የሚኖሩ) ጭምር የዚህ አስተሳሰብ ሰለባ በመሆን ‹ቅማንት ነኝ ማለት የወያኔ የከፋፍለህ ግዛው መሳሪያ መሆን ነው› በማለት የቅማንት ማንነት ከኢትዮጵያ ምድረ ገፅ እንዲጠፋ ለማድረግ ከሌሎች ጋር ሲዶልቱ ይሰማሉ፡፡ ይሁንእንጅ የቅማንት ማንነትን እንዲጠፋ ሲመኙ በራሳቸው ላይ እየተሰላቁ እንደሆነና ለሌሎች በአሽከርነት እያገለገሉ ያሉ እነሱ መሆናቸውን የተገነዘቡት አይመስለኝም፡፡ምን አልባት ‹ቅማንት የለም› ብለው እንዲሰብኩ ያደረጓቸውን ጌቶቻቸውን ማንነት ቢጠይቋቸው በኩራት የሚመልሱትን መልስ የሚያዉቁት ይመስለኛል፡፡ ቅማንት ደግሞ ትናንት በኢህአዴግ የተፈጠረ ህዝብ ሳይሆን ነባር ኢትዮጵያዊ መሆኑን እየካዱት ያሉት ህዝቦችና የአማራ ክልል ሸመኞች ጭምር ያዉቁታል፡፡
ባለፈው ሁለት ወራት በፊት አንድ የፌደራል መንግሥት ቡደን በቅማንት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ዙሪያ ጥናት ለማድረግ ጎንደርና አካባቢው ተገኝቶ ነበር፡፡ ለእዚህ የጥናት ቡደን የተሰጠው የቡደን ውይይት መልስ እጅግ የሚያሳዝንና ኢትዮጵያን ለባሰ መከፋፈል የሚዳርግ ነበር፡፡ እነዚህ የቅማንትን ማንነት የማይፈልጉ ግለሰቦች የሰጡት መልስ ይህን ይመስላል፡፡ ‹ቅማንቶች ጎንደሬ አይደሉም የመጡትም ከግብጥ ነው ጎንደር ውስጥ ምንም አይነት ርዕስት የላቸውም ባለርዕስቶች እኛው ነን፡፡ ቅማንት ሆነው መኖር ከፈለጉ ወደመጡበት ግብጥ ሊመለሱ ይችላሉ› የሚል እጅግ አሳፋሪ መልስ ነበር፡፡ አጥኝ ቡድኑም የራሱን ትዝብት ይዞ ወደመጣበት ተመልሷል፡፡ እነዚህንና መሰል ግለሰቦች ናቸው ስለኢትዮጵያ አንድነት ሲሰብኩ የሚደመጡት፡፡ የኢትዮጵያዊያንን ኢትዮጵያዊ መሆን ያልተቀበለ ቡድን እንዴት ስለኢትዮጵያ አንድነት የመስበክ ሞራል ይነረዋል ተብሎ ይታሰባል? እነዚህ ቡድኖች ዛሬ በየቦታው የሚያቀነቅኑት እውነተኛ የኢትዮጵያ አንድነትን ለማምጣት ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ድሮው የብሔር ጭቆና የመመለስ አባዜ ለመሆኑ ለማንም የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት የሚረጋገጠው አንድን ህዝብ በሀይል የሌላ ማንት እንዲቀበል በማድረግ ሳይሆን ሁሉም በእኩል መንፈስ ተከባብሮ ሲኖር ነው፡፡ ይህ አይነት የወረደ አመለካከት ለኢትዮጵያ አንድነት እምቅ አደጋ መሆኑን እነዚህ አስገድዶ ማንነትን ለማስቀየር የሚተጉ ግለሰቦችና የአማራ ክልል አመራሮች ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል፡፡ የዚህ ሁሉ አስተሳሰብ መሰረቱ የአደግንበት የትምህክት አመለካከት ዉጤት ካልሆነ በስተቀር የቅማንት ህዝብ በህልሙም በእዉኑም ‹ግብጣዊ ነኝ› ብሎ አያውቅም፡፡ ቅማንት በንፁህ ኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ራሱን ከየትም ከምንም ጋር የማያላትም የኩሽ ዘር ነው፡፡

Advertisements
This entry was posted in Agaw Kemant. Bookmark the permalink.

4 Responses to “Canaan-Egypt Origin Gondaris”

 1. Kenaw T says:

  Hello Mizigena,

  Thank you for your continuous efforts to educate all of us about kemant people and the environment they lived, and about the current situations. All of your articles are carrying valuable messages to everybody either supporting kemants or opposing it. At this time, it does not matter what people think and want but the truth about kemants becomes apparent and the efforts from you and many of your colleagues correcting and transforming many of the hidden and distorted information though medias and it reached to the destinations safe and clear.

  Having said that, I would like to offer a personal opinion perhaps a suggestion about your article. Although I know you have a lot of good information and true facts, one needs to have an assurance for the information – the so called citation of the source of the information. I believe you had to read a handful historical papers and gather a lot of good information to put together your article but you didn’t have that cited as much as you could. In other words, where are the source of your good information?

  I want to suggest this because I don’t want someone to equate your information to the information circulated for several years and delivered nothing but political mess and false claims.

  Kenaw T.

  • Mizigena says:

   Dear Kenaw,
   Thanks a lot for your excellent and valuable comments. I will take care of that.
   Regards!
   Mizegana

 2. ayner kementi says:

  THANK U FOR WHAT U DID

 3. yohannes says:

  Thank you very much for your effort to boost the people of Ethiopia to know the real identity of them. True history is not only advantageous for Kimant but also for all of nations and Nationalities of Ethiopia and Ethiopia as a whole.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s